Get Mystery Box with random crypto!

Ethiomedia

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiomedia2 — Ethiomedia E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiomedia2 — Ethiomedia
የሰርጥ አድራሻ: @ethiomedia2
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.14K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል ወቅታዊ፣ አዳዲስ እና እውነተኛ መረጃዎችን የሚያገኙበት ቻናል ነው።
አባል ለመሆን ይህንን ሊንክ ይጫኑ 👉 https://t.me/ethiomedia2

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-08-28 21:19:55
ሰበር ዜና!

ዋጃ ከተማ በጥምር ጦሩ ቁጥጥር ስር ዋለች።ዋጃ ከቆቦ ቀጥላ የምትገኝ ከተማ ነች። መከላከያው አሁን ወደ አላማጣ እየገሰገሰ ይገኛል። የስንቅናየትጥቅ ድጋፋችን ተጠናክሮ ይቀጥል!

የግንባር ዜና  የሚቀርብበት ቻናል ልጠቁማችሁ

===========

ለቴሌግራም  ይህንን @ethiomedia2
@ethiomedia2
@ethiomedia2
398 viewsedited  18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 21:12:19
መረጃ

የሀገር መከታ የሆነው ጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን በባድመ በኩል ጠላትን አይቀጦ ቅጣት እየቀጣ ድርብ ድል እያስመዘገበ ይገኛል።

በጀግናው አየር ሃይል የታገዘው የባድመ ግምባር ውጊያ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን። ጁንታው ቆቦን እንደተቆጣጠረ ያስደነገጠውና ደስታቸውን ወደ ሃዘን የቀየረው ይሄ መረጃ ነው።

======
ትክክለኛ መረጃ  ይህንን ይጫኑ @ethiomedia2
@ethiomedia2
@ethiomedia2
368 viewsedited  18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 19:56:26
ጦራችን ዛሬ በሰራው ኦፕሬሽን በሺዎች የህውሃት ታጣቂ ሲደመሰስ ከ600 በላይ ተማርኳል። ሙሉው መረጃ በመንግሥት በኩል ይፋ ይሆናል።

===========
ለቪድዮ ይህንን http://bit.ly/ethiomedia1

ለቴሌግራም  ይህንን https://t.me/ethiomedia2
318 viewsedited  16:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 21:06:26
ያኔ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ትግራይ ውስጥ ጄኖሳይድ ፈፅሟል ሲሉ ነበር። ወያኔ የሰውን ልጅ በዚህ መልኩ ቪድዮ እየቀረፀ ሲያርድ አለም አቀፍ ሚዲያው ምን ይል ይሆን??
===
የኤርትራ ወንድሞቻችንን እረዱ ሲል ይሰማል ሲቀጥል ሰውን በህይወት አናቱን በጥይት ይመታሉ። ድሮም የመከላከያ ልብስ ለብሰው የትግራይን ልጆች ለፕሮፖጋንዳ ገድለዋል ዛሬ ደግሞ በአደባባይ የሰውን ልጅ በዚህ መልኩ እየገደሉ እንደ ጀግንነት ይሸልላሉ
615 viewsedited  18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 22:03:58 ከነ ዶክተር ደብረጽዮን ጀርባ ያለው ሀቅ
.
የአማራና የኤርትራ ሀይሎች ብልፅግና ሆነው ከበውናል። እኛ ከሰሜን ሸዋ የተመለስነው ምናልባት የዲፕሎማሲያዊ መንገድን ይመርጣሉ ብለን ነበር። የትግራይ ህዝብ ተከቧል። በረሀብ ውስጥ ነው ያለው። ስለዚህ ከከበባ ለመውጣት ሁሉንም አማራጮች እንጠቀማለን።

ጌታቸው ረዳ፣ ሻዕቢያና የአማራ ሀይል ( በሱ አነጋገር የአማራ ተስፋፊዎች ) ካልተደመሰሱ የትግራይ ህዝብ ህልውናው አደጋ ላይ መውደ አይቀርም። ቢያን መተንፈስ አለባቸው አለ።
.
ይሄንን ንግግር የተናገሩት ከሦስት ሳምንት በፊት ሁለቱም መሪዎች በህዝብ መድረክ ላይ ነው። የህዝብ መድረክ ላይ ይሄንን ካሉ በኋላ በኤርትራ ላይ ቀጥታ ጦርነት ከፍተዋል። አሁንም ድረስ የሽምቅ ውጊያ እያደረጉ ነው። ደደቢት ሚዲያ ትግራይ ያለ ኤርትራ አገር መሆን አትችልም እያለ ነው። የኤርትራን ግማሹን ክፍል ይዘው ኤርትራ የምትባል አገርን ፍቀው አጋዚ የሚባል አገር ለመመሰረት ነው ከኤርትራ ተቃዋሚ ሀይሎች ጋር እየሰሩ ያሉት። ይሄንን ጉዳይ ግብፆችና የቱኒዚያ ፖለቲከኞች ከወራት በፊት አሜሪካ ምስራቅ አፍሪካ ውስጥ አዲስ አገር ለመመስረት እየሰራች ነው ሲሉ ሰምቸ ብዙም አልገረመኝም ነበር። አሁን ግን ህወሓት በተራበው የትግራይ ህዝብ ስም ፖለቲካ ሲሰራ ከርሞ መልሶ ወረራ ለመፈጸም እየተዋጋ ነው።
.
ለመሆኑ ህወሓት ለምን ውጊያውን መረጠ
.
ኤርትራ ከአሜሪካ ጋር ጠብ መሆኗና የኢሳያስ አልበገበር ባይነት ተጨምሮበት ኤርትራ ለምዕራባውያን የማትላላክ አገር በመሆኗ ቂም ስለተያዘባት፣ አገሪቱ ፈርሳ እንደገና ለአሜሪካ አመች በሆነ መንገድ መሰራት አለባት በሚል ሀሳብ ህወሓትና
ሳአይኤና ሞሳድ ተስማምተዋል።

ኢትዮጵያን አንኮትኩቶ ያልተረጋጋች ምስራቅ አፍሪካን መመሰረት። የአፍሪቃ ህብረትን ከአዲስ አበባ ወደ ኬኒያ መውሰድ። አጠቃላይ ኢትዮጵያን ከሚዛን ጠባቂነት አውርዶ እንደ ሚጥጥየዋ ጅቡቲ ተሰሚነት ማሳጣት። የተፈጥሮ ሀብቷን እንዳታለማ በማድረግ ደሀ ኢትዮጵያን በማቆየት የአፍሪካን የነፃነት እንቅስቃሴ መስበር ይፈልጋሉ። ይህ ፖሊሲ መንግስቱ ሀይለማርያምን ከስልጣን አስነስቶታል። ከተቀረፀም ቆየት ያለ ፖሊሲ ነው።

ሦስተኛ የአረቦችን ፍላጎት ማሳካት ነው። አረቦች የሚመኙትን የናይልን ወንዝ ለብቻ በመቆጣጠር የወደፊቱን ህልውናቸውን ማረጋገጥ እንዲችሉ ይጠቅማቸው። አጠቃላይ ህወሓት ከደም አፋሳሽ ውጊያው ጀርባ እነዚህን ተልዕኮችን ይዞ ነው ህዝብ እያስጨረሰ ያለው። እኛ በቃ የምንለውን ጦርነት ምንም ጥቅም የለውም ተብሎ ሁሌም ለሰላም የሚዘመርለት የእርስበርስ ውጊያ በዚህ ሴራ ውስጥ የተደበቀ ጥሬ ሀቅ ነው።

ከዚህ አንፃር ኢትዮጵያና ኤርትራ ተገደው እንደ ሀገር ለመቆየት የገቡበት ጦርነት ነው ማለት ነው። ህወሓት ግን አሁንም ይሁን ወደፊት ጉልበት ካገኘ አጋዚ የሚባል አዲስ አገር መስርቶ ኤርትራውያንን በእምነት አጨፋጭፎ የቀረውን ለአፋር አስረክቦ የራሱን አገር ይመሰርታል። የነሱ ህልም ይሄ ነው። በ7 አመት ውጊያ ይሄንን እቅድ ለማሳከት ነው እየተዋጉ ያሉት። ይሄንን ሀቅ
ኢትዮጵያም ኤርትራም ያቁታል።

ምንጭ:-ሱሌማን አብደላ
Ethiomedia

-------------------------
ይህንን ተጭነው ቪድዮውን ይመልከቱ



ይህንን ተጭነው ከቴሌግራም መረጃ ያግኙ https://t.me/ethiomedia2
809 views19:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-09 21:46:37
ኢትዮጵያ በአለም የመጨረሻ ቴክኖሎጂ የሆነውን 5G ዛሬ በይፋ አስጀመረች
======================================
በአፍሪካ ቀዳሚ የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ የሆነው ኢትዮቴሌኮም የወቅቱን የዓለማችንን የመጨረሻውን የኔትዎርክ ትውልድ 5ጂን የቅድመ-ገበያ የሙከራ አገልግሎት የአፍሪካ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ በዛሬው ዕለት በስድስት ጣቢያዎች አስጀመረ!
ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን በማድረግ በጣም አስፈላጊ እንደሆነ ተስፋ የተጣለበት ዋናው ሴክተር ቴሌኮም እንደሆነ ይነገራል። ይህ ቴክኖሎጂ በሰከንድ 10GB ዳታ የማስተላለፍ አቅም ያለው በጣም ከፍተኛ ፍጥነት ያለው ሲሆን። ከዚህ በፊት በነበሩት 3G እና 4G ዳታ የማስተላለፍ መዘግየትን (Ultra low latency) እጅግ በላቀ ሁኔታ የሚቀንስ፣ በርካታ ዲቫይሶችን በአንድ ጊዜ በማገናኘት ለአይ.ኦ.ቲ (Internet of Things) ሲሆን በተለይም ለማምረቻ ፋብሪካዎች፣ ግብርና፣ ህክምና፣ ለመሳሰሉ ኢንዱስትሪዎች ስራቸውን ለማቀላጠፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው። ከነዚህም በተጨማሪ አሽከርካሪ-አልባ ተሽከርካሪዎች (self-driving vehicles) የመሳሰሉ ቴክኖሎጂዎችን እውን ለማድረግ 5G የማይተካ ሚና አለው። በአለም ላይ በውስን ሃገራት ብቻ የተሞከረውን የ5G አገልግሎት በአፍሪካ አምስት ሀገራት ብቻ ሲሆኑ ኢትዮጵያ ስድስተኛው በመሆን ቴክኖሎጂውን ተቀላቅላለች።
ይህ አገልግሎት ተግባራዊ የተደረገው በአዲስ አበባ በውስን ቦታዎች በቀጣይ የአገልግሎት ፍላጎትን መሠረት ባደረገ መልኩ ማስፋፊያዎች እንደሚደረ የተቋሙ ስራ አስኪያጅ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ ገልፀዋል።

Ethiomedia
--------
ለቪድዮ ይህንን http://bit.ly/ethiomedia1

ለቴሌግራም ይህንን https://t.me/ethiomedia2
878 views18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 23:32:54

902 views20:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 15:56:24
#ህዝቡን_የሚያሰቅዩ_ጫኝ_እና_አውራጅ_ላይ_እርምጃ_እንወስዳለን።
================================
በአዲስ አበባ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች በሚገኙ እና በአውራጅ ስም ተደራጅተው ነዋሪዎች ላይ ጉዳት በሚያደርሱ ግለሰቦች ላይ እርምጃ መውሰድ እንደሚጀምር የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ። በተለያዩ ጊዜያት ህዝቡን በማስገደድ ከአቅም በላይ የሆነ ክፍያ የሚጠይቁ እና ዜጎች ከተከራዩበት ቤት ሌላ ቤት በሚቀይሩበት ወቅት የራሳቸው እቃ እንዳይወርድ በመከልከል ከፍተኛ የሆነ ክፍያ በመጠየቅ የሚያሰቃዩ ሲሆን ያንን የማይከፍሉ ከሆነ የድብደባ ሌሎችም መሰል ጥቃት እንደሚያደርሱ ከዚህ በፊት ለጸጥታ አካላች ህዝቡ አቤት ማለቱ ይታወሳል። ያንን ተከትሉ ሰሞኑን አዲስ አበባ መስተዳድር በዚህ ጉዳይ ስብሰባ ያደረግ ሲሆን በጫኝ እና አውራች ስም የተደራጁ እና ህብረተሰቡን የሚያሰቃዩ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።
-------------------------
ይህንን ተጭነው ቪድዮውን ይመልከቱ



ይህንን ተጭነው ከቴሌግራም መረጃ ያግኙ https://t.me/ethiomedia2
628 views12:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 14:31:06
#ሰበር_መረጃ
#breakingnews
ሰሞኑን በወልቃይት በኩል ጥቃት ለመሰንዘር ከፍተኛ ሰራዊት እያስጠጋ እንደሆነ የሚነገረው አሸባሪው ወያኔ በመቀሌ የሚገኙ መጋዘኖችን እየዞሩ ጣራዎቻቸው ላይ "UN" የሚል ቃል እየፃፉባቸው ነው"
በእነዚህ UN ተብለው የሚጻፍባቸው መጋዘኖች ውስጥ የጦር ተሽከርካሪዎችን እና የጦር መሳሪያዎችን እየደበቁባቸው እንደሆነ ነው መረጃዎች የሚያመለክቱት። HR6600 በተመለከተ በአሜርካ በኩል በጉጉት ሲጠብቁት የነበሩ ቢሆንም አሜርካ ከኢትዮጵያ ጋር የተለሳለሰ አቋም መያዟን ተከትሉ በትግራይ በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎችም መጠነ ሰፊ የሆነ የቁፋሮ ስራዎች እና መሳሪያ የማውጣት ስራ ምንጮች ያመለክታሉ።

ይህን መረጃ በቲውተር ገጽ በአንድ የወያኔ ሰው ሾልኮ ቢወጣም የቁፋሮ መረጃ ላይ የራሱን ሁለት ነጥቦች አስቀምጧል።
1- የተቀበረ መሳሪያ እያወጡ ሊሆን ይችላል።
......ካልሆነ ደግሞ
2- አዳዲስ ያስገቧቸውን መሳሪያዎች እየቀበሩም ሊሆን ይችላል ።
ብሏል።
-------------------------
ይህንን ተጭነው ቪድዮውን ይመልከቱ



ይህንን ተጭነው ከቴሌግራም መረጃ ያግኙ https://t.me/ethiomedia2
539 views11:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 09:29:22 #ወራቤ_ላይ_ሌላ_ትኩሳት
=================
የወራቤ ዩኒቨርስቲ ያወጣውን መግለጫ አነበብኩት ይዘቱ ትውልድ ከሚገነባና የእውቀት ማዕከል ከሆነ የፌደራል ዩኒቨርስቲ የመነጨ ነው ወይ የሚል ጥያቄ አጭሮብኛል? ከዚህ በላይ ደግሞ ዩኒቨርስቲው የሃሳብ ማንሸራሸርያ፣ የእውቀት መሰረት፣ የፍትሐዊነትና የትውልድ ግንባታ ተቋም መሆኑ ቀርቶ የዛቻ፣ የማስፈራሪያና የእገታ ተቋም መሆኑ ይበልጥ አስደንጋጭ ሆኖብኛል?!

የወራቤ ዩኒቨርስቲ በአደራ የተረከባቸውን ተማሪዎች በመግለጫ ምርኮኛ ሲያደርጎቸውና ለጥቃት አሳልፎ ሲሰጣቸው ትምህርት ሚኒስቴር ከወዴት አለሁ እያለ እንደሆነም ሊገለጽልኝ አልቻለም !! ክልሎችስ በአደራ ለዩኒቨርስቲዎች የሰጧቸው ልጆቻችን ሳይሸማቀቁና ሳይፈሩ ወደ ትውልድ ቀያቸው እንዲመለሱ ምን ጥረት እያደረጉ ነው የሚል ጥያቄ አጭሮብኛል? ክልሎች ልጆቻችንን በፍላጎታቸው መሰረት ትምህርት አቋርጠው በሰላም ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ ምን እያደረጋችሁ ነው?! ልጆቻችን ከሞታቸው አሟሟታቸው እንዳይሆን ምን ከለላ አላቸው?! ነግ በኔ ነውና እጠይቃለሁ?!

ለመግቢያዪ ምክንያት የሆነኝን የወራቤ ዮኒቨርስቲ መግለጫን ዝርዝሩን ትቼ በሁለት ጉዳዮች ላይ ብቻ በአደራ ልጆቻችንን የሰጣችሁ ክልሎችን ልጠይቅ ?!

አንደኛ

የወራቤ ዮኒቨርስቲ መግለጫ "ነገር ግን" ይላል "ያለ ዩኒቨርስቲው ፍቃድ ትምህርታችሁን አቋርጣችሁ የምትሄዱ ተማሪዎች "ለሚያጋጥማችሁ ችግር" ሁሉ ዩኒቨርሲቲው ሀላፊነት የማይወስድ መሆኑን ይገላፃል" ይላል

ሲጀመር ተማሪ በመገደሉ ምክንያት ስጋት ያደረባቸው ተማሪዎች ከወራቤ ዩኒቨርስቲ ትምህርት አቋርጠው ወደ ክልላቸው መመለስ መብታቸው ነው። መብታቸውን አክብሮ በሰላም ወደ መጡበት እንዲመለሱ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ደግሞ የዩኒቨርስቲውና የዞኑ ግዴታ ነው። ሀቁ ይህ ሆኖ እያለ ካለ እኔ ፈቃድ ትምህርት አቋርጣችሁ ስትሄዱ ችግር ከገጠማችሁ አያገባኝም ማለት ምን ማለት ነው?!

ከዩኒቨርስቲው ውጭ አደጋ ሊያደርስባቸው ያቀደ የታጠቀና የሸመቀ ኋይል አለ ለማለት ነው?! ወይስ ከወገኑ፣ ከክልሉና ከቤተሰቡ የራቀን ተማሪ ለፖለቲካና ለሐይማኖት ፍጆታ ለማዋል በማሸማቀቅ ለማገት እየተሞከር ነው?! ዩኒቨርስቲውና ዞኑ በአደራ የተቀበሏቸው ተማሪዎች ጉዳይ አያገባኝም ካለ፣ ሌላ ማን የሚያገባው አለ ማለት ነው?! ሌላው ክልልም በተመሳሳይ ሁኔታ የተማሪዎች ደሕንነት እኔን አያገባኝም ቢል ምን ሊከሰት እንደሚችል ዩኒቨርስቲውና ዞኑ አስበብወበት ይሆን ይህ መግለጫው የወጣው?!

ዩኒቨርስቲው ከማንኛውም አደጋና ስጋት ጠብቆ እንዲያስተመርና እንዲያበቃ የተረከባቸው ተማሪዎች መማር አንፈልግም፣ በቃን፣ ስጋት አለብን ሲሉ በክብር ወደ መጡበት መሸኘት እንጂ አደጋ ቢደርስባችሁ አያገባኝም ማለትንስ ምን የሚሉት ቅብጥርጥር ነው?! ከዩኒቨርስቲው ቅጥር ጊቢ ውጭ ለአደራ ተማራዎች የሚበቃ አስተማመኝ ሰላም ከሌለና ስጋቱ በገደምዳሜ እየተገለጸ፣ ልጆቹን ለአንድም ቀን ቢሆን በዩኒቨርስቲው እንዲቆዩ የሚፈቅድ ቤተሰብ ይኖራል ብሎ መገመትስ አሳፋሪ አይደለም ወይ ?! ዛሬ ልጆቹ በዩኒቨርስቲ መግለጫ ታግተው እያለ ወደፊት ልጆቹን ወደ ወራቤ ዩኒቨርስቲ በአደራ የማልክ ቤተሰብ ይኖራል ብሎ ማሰብስ ንቀት አይሆንም።

እንቀጥል:-

"በወቅቱ በተከሰተው ሁኔታም ይላል የዩኒቨርስታው መግለጫ "የአንድ ተማሪያችን ህይወት ያለፈ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው ለተማሪው ቤተሰብ እና ጓደኞች በሙሉ መፅናናትን እየተመኘ ሌሎች ተማሪዎቻችን በዚህ ዓይነት አላስፈላጊ የሆነ ድርጊት ባለመሳተፍ የራሳቸሁን ደህንነት መጠበቅ እንዳላባችሁ በጥብቅ ዩኒቨርስቲው ያስገነዝባል፡፡" ይላልደ

ወራቤ ዩኒቨርስቲ ሟችን በሚመለከት ከገለልተኛ አካል የተጣራ መረጃ ሳያገኝና መንስኤውን ሳይታወቅ፣ ሟች የሞተው አላስፈላጊ ድርጊት ውስጥ በመሳተፉ ማለቱ ማለትስ ምን መልዕክት ለማስተላለፍ ተፈልጎ ይሆን። አላስፈላጊ ድርጊት ማለትስ ምን ማለት ነው?! አላስፈላጊ ድርጊት ውስጥ መገኘትስ ሕግ ፊት ያቀርባል እንጂ እንዴት ነፍስን ያሳጣል?! ያውም አዳጊ የአደራ ልጅን ያህል?!

"አላስፈላጊ ድርጊት" በሚል በጅምላ ክስ የተማሪ ሕይወት መጥፋቱ ሳያንስ ወደፊትም ሊጠፋ እንደሚቻል ዩኒቨርስቲው መግለጫ ማውጣቱስ ነውር አይደለም ወይ?! ተማሪዎች ትምሕርት አቋርጠው ከዩኒቨርስቲ ቅጥር ከወጡ ለአደጋ አጋልጧቸው ከማለትስ በምን ይለያል?! ይህንን ዓይነት መግለጫ ማውጣትስ ለአንድ ዞንና ዩኒቨርስቲ ብቻ በተለይ የተሰጠ መብት አድርጎ መውሰድስ ውሎ አድሮ ማጣፊያ አያሳጥርም ወይ ?! ሁሉም ነገር በጠገጉ በቦታውና በልኩ ሲሆን ያኗኑራልና፣ እረ እየተስተዋለ።

አቶ ሙሼ ሰሙ

Ethiomedia

-------------------------
ይህንን ተጭነው ቪድዮውን ይመልከቱ





ይህንን ተጭነው ከቴሌግራም መረጃ ያግኙ https://t.me/ethiomedia2
625 views06:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ