Get Mystery Box with random crypto!

Ethiomedia

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiomedia2 — Ethiomedia E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiomedia2 — Ethiomedia
የሰርጥ አድራሻ: @ethiomedia2
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.14K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል ወቅታዊ፣ አዳዲስ እና እውነተኛ መረጃዎችን የሚያገኙበት ቻናል ነው።
አባል ለመሆን ይህንን ሊንክ ይጫኑ 👉 https://t.me/ethiomedia2

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-05-02 21:48:33 #ዛሬ_መስቀል_አደባባይ_ችግር_የፈጠሩ_በቁጥጥር_ስር_ዋሉ
========================================
በሁከትና ብጥብጥ በግንባር ቀደምትነት የተሳተፉ 76 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ።

1 ሺህ 443ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በአዲስ አበባ በሰፊ ፕሮግራም ታጅቦ በሰላማዊ ሁኔታ የተከናወነ ሲሆን ነገር ግን ጥቂት ከሀይማኖታዊ ሥርዓቱ ውጭ ሌላ የሁከትና ብጥብጥ ዓላማ ያላቸው ግለሰቦችና ቡድኖች ለብጥብጥ መነሻ በማይሆን ምክንያት ከስታዲየም ውጭ በተለምዶ የቀይ ሽብር ሰማዕታት መታሰቢያ ሙዚየም አጠገብ ሆነው ባስነሱት ረብሻና ብጥብጥ በጸጥታ ኃይሎችና በንብረት ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን 76 ግንባር ቀደም ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል።

የጋራ ግብረ ኃይሉ የኢድ አልፈጥርን በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት አድርጎ ወደ ስምሪት መግባቱ ይታወቃል፡፡

በዓሉን ለማክበር ከወትሮው በተለየ መልኩ ህዝበ ሙስሊሙ በነቂስ ወደ በዓሉ ስፍራ በመሄድ የስግደት ስነ ስርዓቱ እንደ ተጀመረ ሁከትና ግርግር የተፈጠረ ሲሆን የፀጥታና ደህንነት ግብረ ሀይሉ መንስኤውን እያጣራ እንደሚገኝና ውጤቱንም ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ገልጿል፡፡

የጋራ ግብረ ኃይሉ ባደረገው ክትትልና ግምገማ አብዛኛው የበዓሉ ታዳሚ ስግደቱን ፈፅሞ የበዓሉን በረከት በመቋደስ ወደ ቤቱ ለመመለስ አስቦ የመጣ ቢሆንም፥ አንዳንድ ግለሰቦችና ቡድኖች በቀልና ጥላቻን ቋጥረው እንዲሁም ከውስጥና ከውጭ ጠላቶቻችን ስውር ተልዕኮ ወስደው ሀገራችን የምትታወቅበትን የሀይማኖት መቻቻል በመናድ ህዝቡን በሀይማኖት በመከፋፈልና በመለያየት ሀገራችንን ለማፍረስ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች ግጭት በማባባስ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ ብሏል።

እነዚህ ፀረ-ሰላም ግለሰቦችና ቡድኖች ሀይማኖትን ሽፋን በማድረግ ተደራጅተው በአንዳንድ አካባቢዎች ስለታማ ነገሮችን፣ የውጭ ሀገር አክራሪዎችን አርማና የተለያዩ ግጭት ቀስቃሽ ጽሁፎችን በመያዝ ጥቃትና በቀል ለመፈፀም ወደ በዓሉ ስፍራ መምጣታቸውን ግብረ ኃይሉ በቁጥጥር ስር ካዋላቸው ፀረ-ሰላም ኃይሎች እጅ መያዙን ገልጿል።

የፈጠሩትን ሁከትና ግርግር ተጠቅመው ከውስጥና ከውጭ ጠላቶቻችን የተቀበሉትን ስውር ተልዕኮ ለመፈፀም ጥረት አድርገዋልም ብሏል ግብረ ኃይሉ።

በዚህ የተነሳ የጸጥታ አካላት ላይ የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን በህዝብና በመንግስት ተቋማት ላይም ጉዳት መድረሱ ታውቋል።

ይህንን እኩይ ተግባር ሲፈፅሙ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ ሁከቱን በትዕግስት በመከታተልና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በህዝበ ሙስሊሙ በተለይም በሴቶች፣ ህፃናትና በሰላማዊ የሀይማኖቱ ተከታዮች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ብርቱ ጥረትና ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርጓልም ነው ያለው፡፡

ከዚህ ሁከትና ብጥብጥ ጋር በተያያዘ በግንባር ቀደምትነት የተሳተፉ 76 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ያዋለ ሲሆን በቀጣይም ጉዳዩን በማጣራት ሌሎች የድርጊቱ ተሳታፊዎችን አድኖ በመያዝ ለህግ እንደሚያቀርብ ግብረ ኃይሉ አስታውቋል።

ግብረ ኃይሉ ክቡር የሰው ልጅ ህይወት እንዳይጠፋና የአካል ጉዳት እንዳይደርስ ከሰላም ወዳዱ የሙስሊም ህብረተሰብ ጋር በመሆን ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍሎ መቆጣጠር የቻለ ሲሆን በበዓሉ ታዳሚዎች ላይ የሞትም ሆነ የአካል ጉዳት እንዳልደረሰ አረጋግጧል።

ይህ ደግሞ የሀገራችን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ ጥንካሬና ብቃት እንዲሁም ለህዝቡ ያለውን ወገንተኝነት ያረጋገጠ ነው ሲል ግብረ ኃይሉ ገልጿል፡፡
ምንጭ:- ፋብኮ

-------------------------
ለቪድዮ ይህንን http://bit.ly/ethiomedia1

ለቴሌግራም ይህንን https://t.me/ethiomedia2
536 views18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-02 12:41:30

493 views09:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 09:49:38 #ጠቋቁሩ_ክረምት??
=============

ለ 3 ወራት የሚቆየው የኢትዮጵያ ክረምት ሊጀምር ተንደርድሮ የ 45 ቀናት ዕድሜ ብቻ ቀርተውታል።

የዚህ ክረምት ጥቁረቱ ምንያክል እንደሆነ በመንግሥትና በብዙዎቻችን የተረሣ ይመሥላል። እንዳው ግምት ብቻ ሆኖ ቢቀር ጥሩ ነበር ነገር ግን ከወደ ሰሜን ድለቃው ከወዲሁ አሥፈሪ ነው። ትላንት በደብረጽዮን ለተመድ ዋና ጸሐፊ የተላከው ደብዳቤ ማዕከላዊ መንግሥትን በቀላሉ መቆናጠጥ እንደሚችሉ የሚገልጽ ጭምር ነው። አፍቃሪዎቹ ሊንዳ ቶማሥ እና ፕላውት ተንኮል ያረገዘ ትዊት እየለቀቁ ነው።

ምዕራባውያን ወዳጆቹ ህውሓት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ዳግመኛ የማዕከላዊ መንግሥትን ሥልጣን እንዲቆናጠጥ ሥራቸውን በማገባደድ ላይ ናቸው። በዚህም ነጻ ሀገር ትግራይን መሥርቶ በአፍሪካ ቀንድ የእነሡ በጥባጭ ተወካይ እንዲሆን ቋምጠዋል። ነጻ ትግራይ ሢባል ደግሞ ከወልቃይት-ጠገዴ-ሠቲትሁመራን ይዘው እንደሆነ እርገጠኛ እንሁን።

የትግራዩ ገዢ ህውሓት ለዚህ ዓላማው የትግሬ ረሐብን እና ባለፈው ጦርነት የደረሠበትን ሠብዓዊ ቀውሥ በአግባቡ እየተጠቀመበት ነው። አሁን ላይ በጣም መራቡን ለማሣየት ለዕርዳታ መጓጓዝ በማለት ከአፋር የወጣ ቢሆንም አንዳንድ ትንታኔዎች እንደሚያሣዩት ክረምቱ መግባት ሢጀምር ተመልሶ ዕርዳታ እንዳይገባ ለማድረግ ጦርነት እንደሚጀምር ይታሠባል። ይህንንም ማደናቀፍ በተለይ የአማራ ልዩ ኃይልና ፋኖ ብሎም መከላከያ ተርበን እንድናልቅ ዕርዳታ ዘጉብን በማለት ከምዕራባውያን አፍቃሪዎቹ ጋር በመሆን የተዛቡ መረጃዎችን ለማሠራጨት የታለመ ነው። በዚህ መነሻ በአማራ ድንበሮች ላይ በተለይ በወልቃይት ከፍተኛ ማጥቃት ይጀምራል ብለን ብናሥብ ለምን ታሠበ የሚል አይመጣም።

በዚህ ወቅት መገንዘብ ያለብን መገግሥት ልክ በዚህ ባለፈው ህዳርና ታህሣሥ ላይ የነበረውን ዓይነት የአየር ኃይልና የድሮን የበላይነት በጨለማው ክረምት የሚታሠብ አይሆንም። ሥለዚህ ጦርነቱ በእግረኞች የበላይነት ያለው አሸናፊ ይሆናል ማለት ነው። የእግረኞች ጦርነት ደግሞ ሠፊ ዝግጅት ፣ ጠንካራ ቅንጅትና መዋሃድ የሚጠይቅ ነው። በዚህ ረገድ ህውሓት መ/ቤት፣ ት/ቤት ፣ ሁሉንም ዕለታዊ ሥራዎች ጠርቅማ ዘግታ የወረራና የጦርነት ዝግጅት ላይ መሆኗ ለሁላችንም የተደበቀ ጉዳይ አይደለም። እንዳውም የአሁኑ ማጥቃት የመጨረሻና አንድም ተጋሩ የማያፈገፍግበት በማለት በወታደር ደረጃ ብቻ አንድ ሚሊየን የሚሆን ሠሬዊት እንዳዘጋጁ ይሠማል። በእኛ በኩልሥ ምን ዝግጅት አለ ለሚለው ጥያቄ ባላየ ልለፈው።

አሜሪካ ደግሞ ልክ የኢትዮጵያ መከላከያ፣ የአማራና የአፋር ልዩ ኃይል እና ፋኖ የህውሓትን ወረራ ለመመከት ሢሞክር ወይም በዝግጅት ላይ እያለ HR6600 እና S3199 የተባለውን ማዕቀብ ያጸድቁታል። ይህንን አፈጻጸሙን በሚመለከት ዶ/ር ሣጥናኤል አድሃኖም አሜሪካ ድረሥ በመሄድ ከአፈጉባኤዋ ጀምሮ እሥከ ሶማሊያዊቷ የኮንግረሥ አባል ኢልሐን ዑመር ጋር ጊዜ ሠጥቶ ተወያይቶበት ተሠልሷል።

HR6600 እና S3199 ማዕቀቦች ኢትዮጵያና ኤርትራ የጦር መሣሪያ እንዳይገዙ፣ እንዳያጓጉዙ የሚያደርግ ነው። በሀገር ደረጃ የምታመርተው እንኳን እንዳይኖር የጥሬ ዕቃ ግዥ እንድትፈጽም የሚያሥችል ብድርና ዕርዳታ እንዳታገኝ ብሎም ዜጎችህ ጭምር ከሚልኩት Remittanc እንዳታገኝ የሚያደርግ ክፉ ማዕቀብ ነው። ማዕቀቡ አሁን ላይ በዜጎች ላይ የተከሠተውን የኑሩ ውድነት ብሎም የገንዘብ ግሽበት በከፍተኛ ደረጃ ያንረዋል። ሀገራችን በባለፈው ጦርነት በዋናነት የረዳትን ድሮን እንኳን ለመግዛትና ለማጓጓዝ የሚያሥችል ሌላ ሀብት አይኖራትም። ይህንን ማዕቀብ ለማጽደቅ ያለፈው የ HRW እና Amnesty ሪፖርት ቀሽበው እንደገና ያቀርቡታል። ከዚህ በተጨማሪም በቅርብ ቀናት ውሥጥ የሚገቡት 3ቱ በትግራይ የሠብዓዊ መብት አጣሪ ኮሚሽን ባልደረባዎች ተጨማሪ አደናቋሪና የሐሠት መረጃ አቀባዮች ይሆናሉ።

በመጨረሻም የኢትዮጵያ መንግሥት ፣ በተለይ የአማራ ክልል እና የአፋር ክልል የጸጥታ ኃይሎች በቀሪዋ ግዜ ትኩረታቸውን በክረምት ሊከሠት የሚችሉ ግጭቶችን ለመመከት ጠንካራ ዝግጅት ማድረግ የግድ ይላቸዋል። ልዩነቶችን ለጊዜው ወደ ጎን ትተን መደራጀት፣ ሐቅም ግንባታ፣ ሥልጠና፣ ማከማቸት እና መቀናጀት ላይ focus አድርገን ቢሠራ መልካም ነው። የሌሎች ሴክተር ሠራተኞች ካለፈው በበለጠ ዕገዛ እንድናደርግ አሥተባባሪዎች መዘጋጀት ይኖርበታል። ጎበዝ እንነሣ !!!

------------------
ለቪድዮ ይህንን http://bit.ly/ethiomedia1

ለቴሌግራም ይህንን https://t.me/ethiomedia2
1.2K views06:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-25 10:51:45
የመኖርያ ቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪንና ተከራዮችን ማስወጣትን ለመገደብ የወጣው ደንብ ለሚቀጥሉት ሶስት ወራት ተራዝሟል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዜጎችን ጥያቄና አገራዊ ሁኔታን ከግምት ውስጥ በማስገባት ከዚህ በፊት የመኖርያ ቤት ተከራዮችን ለማስለቀቅና የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ ለመገደብ ደንብ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡ ደንቡ ላለፉት ሶስት ወራትም እንዲራዘም ተደርጎ አንደነበርም አይዘነጋም፡፡

አሁንም ዜጎችን ከተለያዩ ጫናዎች ለመከላከል ሲባል ይህ ደንብ ለሚቀጥሉት ሶስት ወራት እንዲራዘም የከተማው አስተዳደር ወስኗል፡፡
ስለሆነም በዚሁ መሰረት በሚቀጥሉት ሶስት ወራት ተከራዮችን ማስለቀቅና እና የቤት ኪራይ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያስታውቃል፡፡

ኢትዮጵያዊ የመተሳሰብና የመተጋገዝ ባህላችንን በማሳደግ ፈታኝ ሁኔታዎች በጋራ ሆነን እንድንሻገር የከተማ አስተዳደሩ በዚህ አጋጣሚ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

ለቪድዮ ይህንን http://bit.ly/ethiomedia1

ለቴሌግራም ይህንን https://t.me/ethiomedia2
1.5K viewsedited  07:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-23 20:20:32
የ2013 ዓ.ም የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተናን አስመልከቶ በቀረበ ቅሬታና በተካሄደ ምርመራ መሰረት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

በሀገራችን መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መከበራቸውን ለመከታተል ይቻል ዘንድ የተለያዩ የዴሞክራሲ ተቋማት ተመስርተዋል፡፡ ከእነዚህ ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ዋና ተልዕኮው ህገ- መንግስታዊ መርሆች በትክክል እንዲተገበሩ፣ ግልጽ የሆነ መንግስታዊ አስራር እንዲኖር ፣ዜጎች የመብታቸው ተጠቃሚ እንዲሆኑና መልካም የመንግስት አስተዳደር እንዲሰፍን ማስቻል ነው፡፡

ተቋሙም ይህንኑ ህገ- መንግስታዊ ተልዕኮ ለማሳካት ይችል ዘንድ በተሻሻለው የተቋሙ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1142/2011 ከተሰጠው ስልጣንና ተግባር መካከል አንዱ ዜጎች አስተዳደራዊ በደሎችን አስመልክተው የሚያቀርቧቸውን ቅሬታዎች ተቀብሎ በመመርመር የአስተዳደር ጥፋት የተፈጸመ መሆኑን ሲያረጋግጥ ተገቢውን የመፍትሄ ሀሳብ መስጠት ሲሆን አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ደግሞ በራስ ተነሳሽነት ምርመራ የማካሄድ ስልጣን እንዳለው አንቀጽ 7(2) ላይ በግልጽ ተደንግጓል፡፡

በዚህም መሰረት በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናን አስመልክቶ ለተቋሙ የቀረቡ ጥቆማዎች እና በተለያዩ ሚዲያዎች ጉዳዩን አስመልክቶ የቀረቡ ዘገባዎችን መነሻ በማድረግ ችግሮችን በምርመራ በመለየት ተገቢውን የመፍትሄ ሃሳብ ለመስጠት በተደረገ የራስ ተነሳሽነት ምርመራ ሪፖርት መሰረት ተቋሙ ተከታዩን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ለቪድዮ ይህንን http://bit.ly/ethiomedia1

ለቴሌግራም ይህንን https://t.me/ethiomedia2
771 viewsedited  17:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-23 18:10:16
“ስጋት ከተጋረጠብኝ ኒውክሌር ልጠቀም እችላለሁ”
ሩሲያ

ዩናይትድ ስቴትስ ኒውክሌርን በተመለከተ ሩሲያ የምታራምደውን አቋም አወገዘች፡፡

ፔንታጎን ሩሲያ ኒውክሌርን ጥቅም ላይ ለማዋል ፍላጎት ማሳየቷን አጣጥሏል ፡፡
አደገኛ ጉዳይ ነው ብሎታል ፡፡
የክሪሚሊን ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ የሰጡትን አስተያየት ተከትሎ ነው ከነጩ ቤተ መንግስት በኩል ስጋት አለን የሚል አስተያየት እየተሰነዘረ ያለው ፡፡

ቃል አቀባዩ እንደሚሉት ሩሲያ ስጋት የተጋረጠባት መስሎ ከታየት እንዲህ አይነቱን የጦር ማሳሪያ ልትጠቀመው ትችላለች ፡፡

ሩሲያ በዓለም ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኒውክሌር አረር ያላት አገር ከመሆኗም ባሻገር ብሄራዊ ስጋት ከተጋረጠብኝ አደርገዋለሁ ማለቷ የዋሽንግተንን ፖለቲከኞች አስደንግጧል፡፡

የዩናይትድ ስቴትሱ የመከላከያ ቃል አቀባይ ጆን ኪርቢ ሁኔታው አደገኛ መሆኑን አልሸሸጉም ፡፡

ኃላፊነት የሚሰማው ኒውክሌር የተጠቀ ኃይል በዚህ መንገድ መታየት እና እንቅስቃሴ ማድረግ ባልኖረበትም ይላሉ፡፡

ፔንታጎን ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለው ነው ተብሏል ፡፡

ሞስኮ ኒውክሌር ለመጠቀም የሚያደርስ ስጋት አይጋረጥባትም ፤ ወደ ኒውክሌር ጦርነት ትገባለች ተብሎም አይታሰብም የሚሉ ተንታኞች ይኑሩ እንጂ ፑቲን ቀደም ሲል የኒውክሌር ኃይሉን ነቅተህ ጠብቅ ማለታቸው የሚዘነጋ አይደለም ፡፡

ለቪድዮ ይህንን http://bit.ly/ethiomedia1

ለቴሌግራም ይህንን https://t.me/ethiomedia2
652 viewsedited  15:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-23 17:27:23
አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ከሥልጣናቸው ለቀቁ።
=====================
ላለፉት ሰላሳ ሰባት ዓመታት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ያገለገሉት አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ከጤናቸው ጋር በተገናኘ በይፋዊ መንገድ ከኃላፊነታቸው በገዛ ፍቃዳቸው መልቀቃቸውን ኢትዮ ንግድና ኢንስትመንት መድረክ ዘግቧል።
በገዘ ፍቃዳቸው ከኃላፊነታቸው የለቀቁት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተወልደ ገ/ማርያም ከስድስት ወራት ላለፈ ጊዜ ህክምናቸውን በአሜሪካ እየተከታተሉ እንደሚገኙም ተገልጿል፡፡
አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ላለፉት 11 ዓመታት የኢትዮጵያ አየር መንገድን በዋና ሥራ አስፈፃሚ አሥፈፃሚነት የመሩ ሲሆን፤ ለ37 ዓመታት አየር መንገዱን አገልግለዋል፡፡
ምንጭ፦ ኢትዮ ንግድና ኢንስትመንት መድረክ
532 views14:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-15 08:48:38 #ለትግራይ_እርዳታ_ይድረስ
===================
አለም አቀፍ ሚዲያዎች ስለ ትግራይ እርዳታ ይግባ ብለው አብዝተው ሚጮሁ ከሆነ ህውሃት መሳሪያ አልቆበታል ማለት ነው። ልክ የዛሬ አመት በዚህ ሰአት ህውሃት አከርካሪው ሲመታ እርዳታ፣ አክሰስ፣ ሚዲያ ይግባ ብለው ጮሀው ጮሀው ገብተው። ህውሃትን፣ በመሳሪያ፣ በሳተላይት፣ እና በሎጄስቲክስ እገዛ ሰጥተው ከጫካ ያስወጡት። ህውሃት አማራ ና አፋር ክልል በወረረበት ወቅት ብዛት ያለውን መሳሪያ እና የሎጄስቲክስ መኪና አጥቷል። አሁን በእጁ ያሉ መሳሪያ እና የኮሙኒኬሽን እቃ እንዲሁም የሊጄስቲክስ መኪኖች ውስን ናቸው። ህውሃትን ከሞት ታድገው ምስራቅ አፍሪካ ላይ የነሱ ተወካይ ማድረግ ሚፈልጉ ምእራባውያን እና አሜርካ ዛሬ ያንን አቅርቦት ሊረዱ ሚዲያቸው በሙሉ በትግራይ እርዳታ የለም፣ ኢንተርኔት ይከፈት፣ እያሉ ነው። እውነታው ግን ህውሃት ከ40 ሚልዮን አማራ ህዝብ የዘረፈው ንብረት ለ5ሚልዮን ህዝብ ቢያንስ አምስት አመት ይቀልባል። ትራንስፖርት የለም ይላሉ ከወልዲያ ዲፖ ብቻ የዘረፉት 5አመት ያደርሳል። ታዲያ ጩሀት ለምን በዛ ሚስጢሩ በእርዳታ ሰበብ መሳሪያ እና ወታደር ማጓጓዣ መኪና መስጠት ፈልገው ነው ምክንያቱም አብዛኞቹ ወታደር ማጓጓዣ መኪና በድሮን ተቃጥሎባቸዋል። የእነ CNN ዘመቻ በእርዳታ ሰበብ ህውሃትን ድጋሚ አስታጥቀው ድጋሚ ለማስወረር በእስትራቴጂ ሚሰራ እንጂ ትግራይ ውስጥ ረሃብ የለም።

ለቪድዮ ይህንን http://bit.ly/ethiomedia1

ለቴሌግራም ይህንን https://t.me/ethiomedia2
1.3K viewsedited  05:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-14 20:24:25 ውድ የቻናላችን ተከታታዮች ከዚህ በፊት በዚህ ቻናል በየቀኑ ይቀርብ የነበረው ዜና የተቋረጠው በአንዳንድ የውስጥ ጉዳይ ስለተፈጠረው የመረጃ ክፍተት ይቅርታ እንጠይቃለን!
#Ethiomedia
1.0K viewsedited  17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-07 19:04:01
#BREAKING NEWS

የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ከእስር መፈታታቸውን ፓርቲው አሳውቋል።

-------------------------
ለቪድዮ ይህንን http://bit.ly/ethiomedia1

ለቴሌግራም ይህንን https://t.me/ethiomedia2
1.4K viewsedited  16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ