2022-08-29 21:02:38
ወልቃይት!!
**
ከወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳደር የፀጥታ ምክርቤት በወቅታዊ ጉዳይ የተሰጠ መግለጫ።
እንደሚታወቀው ሀገራችን ኢትዮጵያ ፈተናዎችን በድልና በብቃት፣ በብልሃት እና በጥበብ አሸባሪውን ትህነግ እና ታሪካዊ ጠላቶቻችንን እያሸነፈች የምትሻገር እንጂ በፈተናዎች ብዛት ተደናቅፈን የምንወድቅ ኢትዮጵያውያን አይደለንም። ምክንያቱም እኛ ኢትዮጵያውያን ለሰላም የሚዘረጉ እጆች ያለን እንጂ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚመጣ ማንኛውም የሰማይም ይሁን የምድር ኀይል ሽንፈትና ውርደት ተከናንቦ የሚመልስ ታሪክ ያለን ሕዝቦች መሆናችንን የአደባባይ ምስጢር ነው።
ስለሆነም ኢትዮጵያዊነት የአሸናፊነት ምልክት በመሆኑ አሁናዊ የአሸባሪው ትህነግ ሦስተኛው የጦርነት ትንኮሳ የመጨረሻው የመሞቻው ጊዜ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያውያን የድልና የትንሣኤ ጊዜ ነው።
ስለዚህ ወራሪው ቡድን የተሰጠውን የሰላም አማራጮችን እያጨናገፈና እያፈረሰ በትግራይ ሕዝብ ጫንቃ ላይ ተጣብቆ ደሙን እየመጠጠ እና በውር ድንብር ጉዞ ለመኖር አማራና አፋር ክልሎችን በመውረርና በማዋረድ ኢትዮጵያን ማፍረስ የሚል ሰይጣናዊ ግቡን ለማሳካት በሕዝባችን ያልፈነቀለው የሴራ ድንጋይና ያልፈፀመው ደባ የለም።
ይሁን እንጂ መላው ኢትዮጵያውያን ይህንን ወራሪ ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ እስከወዲያኛው እንዲያሸልብ ከወትሮው በተለየ ኢትዮጵያዊነታችንን አጠናክረን እንደ አንድ ሰው አስበን እንደ አንድ ቃል ተናግረን ለታሪካዊ ጠላቶቻችንን ውርደት አከናንበን በዲፕሎማሲው ተሰሚነቷ የገነነች፣ በኢኮኖሚው ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆነች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ መላው ሕዝባችን ድካ የለሽ እንቅስቃሴ እንዲያደርግ ታሪካዊ ጥሪ ስናቀርብለት ትልቅ ኩራት ይሰማናል።
ስለሆነም የተከበራችሁ የፀጥታ ጥምር ኀይሎች፣ የፖለቲካ አመራሮችና መላው ሕዝባችን ዛሬም እንደትላንቱ የማያዳግም እርምጃ በአሸባሪው ትህነግ እና በታሪካዊ ጠላቶቻችን የመረረ ጥላቻ ይዘን የመረረ ምት አሳርፈንና አሳፍረን በሁለንተናዊ የተከበረችና የተፈራች ሀገር ለመገንባት ትግላችን ከውስጥ ባንዳ እስከ ውጭ ባንዳ ያለውን ሀገር የማፍረስ ቅንጅት አፍርሰንና ደርምሰን በሁለንተናዊ የበለፀገች ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ የሚከተሉትን ተግባራት እንድንሠራ።
1.ሁሉም ወረዳዎችና ከተሞች ከመንግስት ተሽከርካሪዎች ውጭ የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ከጧቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽት 1 ሰዓት ብቻ እንዲሆን የወሰነ መሆኑ ታውቆ ይህን ተላልፎ የተገኘ የተሽከርካሪ ባለ ንብረትና አሽከርካሪ ህጋዊ እርምጃ የሚሰድ ይሆናል!!
2.መላው የዞናችን ሕዝብ ከዚህ በፊት በተደራጀበት የመንግስት አደረጃጀት መሠረት አካባቢውን ከሰር-ጎገብና ከውስጥ ባንዳ ያላለሰለሰ ትግል በማካሄግድ ከጠላት አስተሳሰብና ተግባር የፀዳ ከባቢ እንድታደርጉ ጥሪያችን እናቀርባለን!!
3.ማንኛውም ሀገሩን እንዳትፈርስና በጠላት እንዳትወረር የሚፈልግ ሰው ሁሉ (ተቆርቋሪ) ፀጉረ-ልውጥ ሲያገኝ በፍጥነት በአካቢው ለተሰማራው የፀጥታ መዋቅር የመጠቆምና የመያዝ ወደ ህግ አካላት እንዲያስረክቡ ጥሪያችንን እናቀርባለን!!
4.በወረዳ የቀበሌ ከተሞችን ጨምሮ ባለሆቴሎች ባለ ምግብ ቤቶች ማንነቱ/አድራሻው/ ያልታወቀ ሲያጋጥም ለሚመለከተው የፀጥታ አካል እንድታስረክቡ። ከዚህ ውጭ በመሆን ማንነቱ ያልታወቀ ሰው ያስጠጋ፣ ያሳደረ፣ ለጠላት ተባባሪ በሆነ አካል ላይ እርምጃ ይወሰዳል።
5.በተለይ በከተሞች አካባቢ ተከራይተውና አከራይተው የሚኖሩ ዜጎች በፍጥነት ተመዝግበው በአቅራቢያ ላለው የፀጥታ ተቋም ሪፖር እንድታደርጉ።
6.በዞናችን ጠላት የሚኖርባቸው አጎራባች ወይም አዋሳኝ ቦታዎች ቀይ መስመር መሆናቸውን ታውቆ በእነዚህ አካባቢ የእርሻና እርባታ ያላቹሁ አልሚዎቻችን ከጧቱ 12 ሰዓት እስከ ቀኑ 12 ሰዓት ብቻ እንቅስቃሴ የምታደርጉ መሆኑን እያሳሰብን ለጉልበት ሥራ የምትወስዷቸውን አካላት ማንነት በማረጋገጥ ለሚለከተው የፀጥታ አካል አስመዝግባቹሁ የምታሰሩ ሆኖ ይህን የተላለፈ ባለ ሃብትም ይሁን ወኪል በሕግ ይጠየቃል።
7.በዞናችን በሁሉም አካባቢዎች የሰው እንቅስቃሴ እስከ ምሸቱ 3 ሰዓት ብቻ መሆኑ ታውቆ እነዚህን ክልከላዎችን በሚተላለፍ አካል ላይ ሕግ እንዲያስከብር ለጸጥታ መዋቅሩ ትዛዝ ተሰጥቷል።
8.በሁሉም የዞናች አካባቢዎች አዲስ መታወቂያ እንዳይሰጥ ተከልክሏል።
9.በዞናችን ውስጥ ያለ የታጠቀ ኀይል በሙሉ ካለበት ወረዳ ከተማና ቀበሌ አስፈላጊውን ወታደራዊ ዝግጅት አድርጎ እንዲጠብቅ ታዟል።
10.መላው የዞናችን ሕዝብ ለፀጥታ ጥምር ኀይሎች የተለመደውን ደጀንነቱን በአስተማማኝነት እያጠናከረ እንዲሄድ ጥሪያችንን እናቀርባለን!!
በመጨረሻም በጠላት ላይ የመረረ ጥላቻ በመያዝ እና በመዋጋት ክብራችንን እና ነፃነታችንን እንጂ ከቀያችን ሸሽተንና ተፈናቅለን ህልውናችንን አናረጋግጥም እና መታገልና መደራጀት ብቻ ነው አማራጫችን!!
ኢትዮጵያ እያሸነፈች ትሻገራለች!!
ነሐሤ 23/2014 ዓ.ም
የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳደር የፀጥታ ምክርቤት
ሰቲት ሁመራ
326 viewsedited 18:02