Get Mystery Box with random crypto!

አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ከሥልጣናቸው ለቀቁ። ===================== ላለፉት ሰላሳ ሰባት | Ethiomedia

አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ከሥልጣናቸው ለቀቁ።
=====================
ላለፉት ሰላሳ ሰባት ዓመታት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ያገለገሉት አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ከጤናቸው ጋር በተገናኘ በይፋዊ መንገድ ከኃላፊነታቸው በገዛ ፍቃዳቸው መልቀቃቸውን ኢትዮ ንግድና ኢንስትመንት መድረክ ዘግቧል።
በገዘ ፍቃዳቸው ከኃላፊነታቸው የለቀቁት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተወልደ ገ/ማርያም ከስድስት ወራት ላለፈ ጊዜ ህክምናቸውን በአሜሪካ እየተከታተሉ እንደሚገኙም ተገልጿል፡፡
አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ላለፉት 11 ዓመታት የኢትዮጵያ አየር መንገድን በዋና ሥራ አስፈፃሚ አሥፈፃሚነት የመሩ ሲሆን፤ ለ37 ዓመታት አየር መንገዱን አገልግለዋል፡፡
ምንጭ፦ ኢትዮ ንግድና ኢንስትመንት መድረክ