Get Mystery Box with random crypto!

#ጠቋቁሩ_ክረምት?? ============= ለ 3 ወራት የሚቆየው የኢትዮጵያ ክረምት ሊጀምር ተንደ | Ethiomedia

#ጠቋቁሩ_ክረምት??
=============

ለ 3 ወራት የሚቆየው የኢትዮጵያ ክረምት ሊጀምር ተንደርድሮ የ 45 ቀናት ዕድሜ ብቻ ቀርተውታል።

የዚህ ክረምት ጥቁረቱ ምንያክል እንደሆነ በመንግሥትና በብዙዎቻችን የተረሣ ይመሥላል። እንዳው ግምት ብቻ ሆኖ ቢቀር ጥሩ ነበር ነገር ግን ከወደ ሰሜን ድለቃው ከወዲሁ አሥፈሪ ነው። ትላንት በደብረጽዮን ለተመድ ዋና ጸሐፊ የተላከው ደብዳቤ ማዕከላዊ መንግሥትን በቀላሉ መቆናጠጥ እንደሚችሉ የሚገልጽ ጭምር ነው። አፍቃሪዎቹ ሊንዳ ቶማሥ እና ፕላውት ተንኮል ያረገዘ ትዊት እየለቀቁ ነው።

ምዕራባውያን ወዳጆቹ ህውሓት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ዳግመኛ የማዕከላዊ መንግሥትን ሥልጣን እንዲቆናጠጥ ሥራቸውን በማገባደድ ላይ ናቸው። በዚህም ነጻ ሀገር ትግራይን መሥርቶ በአፍሪካ ቀንድ የእነሡ በጥባጭ ተወካይ እንዲሆን ቋምጠዋል። ነጻ ትግራይ ሢባል ደግሞ ከወልቃይት-ጠገዴ-ሠቲትሁመራን ይዘው እንደሆነ እርገጠኛ እንሁን።

የትግራዩ ገዢ ህውሓት ለዚህ ዓላማው የትግሬ ረሐብን እና ባለፈው ጦርነት የደረሠበትን ሠብዓዊ ቀውሥ በአግባቡ እየተጠቀመበት ነው። አሁን ላይ በጣም መራቡን ለማሣየት ለዕርዳታ መጓጓዝ በማለት ከአፋር የወጣ ቢሆንም አንዳንድ ትንታኔዎች እንደሚያሣዩት ክረምቱ መግባት ሢጀምር ተመልሶ ዕርዳታ እንዳይገባ ለማድረግ ጦርነት እንደሚጀምር ይታሠባል። ይህንንም ማደናቀፍ በተለይ የአማራ ልዩ ኃይልና ፋኖ ብሎም መከላከያ ተርበን እንድናልቅ ዕርዳታ ዘጉብን በማለት ከምዕራባውያን አፍቃሪዎቹ ጋር በመሆን የተዛቡ መረጃዎችን ለማሠራጨት የታለመ ነው። በዚህ መነሻ በአማራ ድንበሮች ላይ በተለይ በወልቃይት ከፍተኛ ማጥቃት ይጀምራል ብለን ብናሥብ ለምን ታሠበ የሚል አይመጣም።

በዚህ ወቅት መገንዘብ ያለብን መገግሥት ልክ በዚህ ባለፈው ህዳርና ታህሣሥ ላይ የነበረውን ዓይነት የአየር ኃይልና የድሮን የበላይነት በጨለማው ክረምት የሚታሠብ አይሆንም። ሥለዚህ ጦርነቱ በእግረኞች የበላይነት ያለው አሸናፊ ይሆናል ማለት ነው። የእግረኞች ጦርነት ደግሞ ሠፊ ዝግጅት ፣ ጠንካራ ቅንጅትና መዋሃድ የሚጠይቅ ነው። በዚህ ረገድ ህውሓት መ/ቤት፣ ት/ቤት ፣ ሁሉንም ዕለታዊ ሥራዎች ጠርቅማ ዘግታ የወረራና የጦርነት ዝግጅት ላይ መሆኗ ለሁላችንም የተደበቀ ጉዳይ አይደለም። እንዳውም የአሁኑ ማጥቃት የመጨረሻና አንድም ተጋሩ የማያፈገፍግበት በማለት በወታደር ደረጃ ብቻ አንድ ሚሊየን የሚሆን ሠሬዊት እንዳዘጋጁ ይሠማል። በእኛ በኩልሥ ምን ዝግጅት አለ ለሚለው ጥያቄ ባላየ ልለፈው።

አሜሪካ ደግሞ ልክ የኢትዮጵያ መከላከያ፣ የአማራና የአፋር ልዩ ኃይል እና ፋኖ የህውሓትን ወረራ ለመመከት ሢሞክር ወይም በዝግጅት ላይ እያለ HR6600 እና S3199 የተባለውን ማዕቀብ ያጸድቁታል። ይህንን አፈጻጸሙን በሚመለከት ዶ/ር ሣጥናኤል አድሃኖም አሜሪካ ድረሥ በመሄድ ከአፈጉባኤዋ ጀምሮ እሥከ ሶማሊያዊቷ የኮንግረሥ አባል ኢልሐን ዑመር ጋር ጊዜ ሠጥቶ ተወያይቶበት ተሠልሷል።

HR6600 እና S3199 ማዕቀቦች ኢትዮጵያና ኤርትራ የጦር መሣሪያ እንዳይገዙ፣ እንዳያጓጉዙ የሚያደርግ ነው። በሀገር ደረጃ የምታመርተው እንኳን እንዳይኖር የጥሬ ዕቃ ግዥ እንድትፈጽም የሚያሥችል ብድርና ዕርዳታ እንዳታገኝ ብሎም ዜጎችህ ጭምር ከሚልኩት Remittanc እንዳታገኝ የሚያደርግ ክፉ ማዕቀብ ነው። ማዕቀቡ አሁን ላይ በዜጎች ላይ የተከሠተውን የኑሩ ውድነት ብሎም የገንዘብ ግሽበት በከፍተኛ ደረጃ ያንረዋል። ሀገራችን በባለፈው ጦርነት በዋናነት የረዳትን ድሮን እንኳን ለመግዛትና ለማጓጓዝ የሚያሥችል ሌላ ሀብት አይኖራትም። ይህንን ማዕቀብ ለማጽደቅ ያለፈው የ HRW እና Amnesty ሪፖርት ቀሽበው እንደገና ያቀርቡታል። ከዚህ በተጨማሪም በቅርብ ቀናት ውሥጥ የሚገቡት 3ቱ በትግራይ የሠብዓዊ መብት አጣሪ ኮሚሽን ባልደረባዎች ተጨማሪ አደናቋሪና የሐሠት መረጃ አቀባዮች ይሆናሉ።

በመጨረሻም የኢትዮጵያ መንግሥት ፣ በተለይ የአማራ ክልል እና የአፋር ክልል የጸጥታ ኃይሎች በቀሪዋ ግዜ ትኩረታቸውን በክረምት ሊከሠት የሚችሉ ግጭቶችን ለመመከት ጠንካራ ዝግጅት ማድረግ የግድ ይላቸዋል። ልዩነቶችን ለጊዜው ወደ ጎን ትተን መደራጀት፣ ሐቅም ግንባታ፣ ሥልጠና፣ ማከማቸት እና መቀናጀት ላይ focus አድርገን ቢሠራ መልካም ነው። የሌሎች ሴክተር ሠራተኞች ካለፈው በበለጠ ዕገዛ እንድናደርግ አሥተባባሪዎች መዘጋጀት ይኖርበታል። ጎበዝ እንነሣ !!!

------------------
ለቪድዮ ይህንን http://bit.ly/ethiomedia1

ለቴሌግራም ይህንን https://t.me/ethiomedia2