Get Mystery Box with random crypto!

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

የሰርጥ አድራሻ: @esat_tv1
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 245.32K
የሰርጥ መግለጫ

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-06-17 08:31:50
መንግሥት ባለፈው ሳምንት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረበው "የንብረት ማስመለስ" አዋጅ፣ ከውጭ በተላከላቸው ገንዘብ ሃብት ያፈሩ ዜጎች ገንዘቡን የተረከቡበትን ደረሰኝ ለፍርድ ቤት አቅርበው ካላረጋገጡ መንግሥት ንብረታቸው እንዲወረስ ሥልጣን የሚሰጥ እንደኾነ ሪፖርተር ዘግቧል

ማንኛውም ሰው ሊታወቅ ከሚችል ገቢው በላይ ሃብት አፍርቶ የምንጩን ሕጋዊነት ማረጋገጥ ካልቻለ፣ መንግሥት ንብረቱን የመውረስ ሥልጣን እንዳለው ረቂቅ አዋጁ እንደሚደነግግ ዘገባው አመልክቷል። ዓቃቤ ሕግ ምንጩ አይታወቅም ብሎ ለሚጠረጥረው 5 ሚሊዮን ብር ለሚገመት ንብረት 10 ዓመት ወደኋላ ሂዶ ክስ ማቅረብ እንደሚችልም ረቂቅ አዋጁ ይፈቅዳል ተብሏል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
8.1K views05:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-17 08:04:53 ​​በሳዑዲ አረቢያ በተመዘገበ ከፍተኛ መቀት ቢያንስ የ14 ሀጅ ተጓዦች ህይወት አለፈ

በሳዑዲ አረቢያ በሃጅ ጉዞ ወቅት ቢያንስ 14 የዮርዳኖስ ዜጎች በሃይለኛ ሙቀት የተነሳ ህይወታቸው ማለፉን የመንግስት ባለስልጣናት አስታውቀዋል። የዮርዳኖስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው 14 ዜጎቹ በከፍተኛ ሙቀት በፀሃይ ግለት ሕይወታቸውን አጥተዋል ያለ ሲሆን በተጨማሪ 17 የዮርዳኖስ ዜጎች የደረሱበት አልታወቀም። አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው ደግሞ የኢራን ቀይ ጨረቃ አምስት ኢራናውያን ህይወታቸውን ማጣታቸውን አረጋግጧል፤ ነገር ግን እንዴት እንደሞቱ አልገለፀም።

የዮርዳኖስ ባለስልጣናት የጠፉትን ዜጎቹን ፍለጋ መቀጠሉን ተናግረዋል። የዮርዳኖስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ የሟቾችን አስከሬን ለመቅበር ወይም ለማጓጓዝ ከሳውዲ ባለስልጣናት ጋር በቤተሰቦቻቸው ፍላጎት መሰረት በማስተባበር ላይ መሆኑን ገልጿል። ሐጅ በዓለም ላይ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በአንድነት ከሚያሰባስቡ መንፈሳዊ ስነ ስርዓቶች መካከል አንዱ ነው። በዚህ አመት ከ1 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ሀጃጆች በመሳተፍ ላይ መሆናቸውን የሳዑዲ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

ነገር ግን የድንኳን ቃጠሎን ጨምሮ ገዳይ አደጋዎች ተደቅነዋል። ዋናው ፈተና ከፍተኛ ሙቀት ነው። በዚህ ሳምንት የሙቀት መጠኑ ከ 46 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ በልጧል። ከቤት ውጭ እና በእግር የሚደረጉ የአምልኮ ሥርዓቶች በተለይ ለአረጋውያን ፈታኝ አድርጓል። የሳዑዲ ብሄራዊ የሚቲዎሮሎጂ ማዕከል ኃላፊ አይማን ጉላም ባለፈው ሳምንት ከፍተኛ ሙቁት ስለመኖሩ አስጠንቅቀው ነበር። በዚህ አመት ለሀጅ ተብሎ የሚጠበቀው የአየር ንብረት በመካ እና በመዲና ከመደበኛው በላይ ከ1.5 እስከ 2 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ያህል የሙቀት መጠኑ ጨምሯል።

ሁለቱ ከተሞች ለአምስት ቀናት በሚቆየው የሃጅ ጉዞ ማዕከል ናቸው። የዘንድሮ የሐጅ ጉዞው እሮብ ይጠናቀቃል። የሳዑዲ ባለስልጣናት ለሙቀት ቅነሳ የደህንነት እርምጃዎችን ይፋ ከማድረግ ባለፈ በርካታ የአየር ንብረት ቁጥጥር ቦታዎችን አቋቁመዋል። ውሃ በማከፋፈል ሀጃጆች እራሳቸውን ከፀሀይ እንዴት መጠበቅ እንደሚችሉ ምክር በመስጠት ላይ ይገኛሉ። የሳዑዲ ጤና ሚኒስቴር ሀጃጆች ውሃ እንዲጠጡ በቀኑ ክፍለ ጊዜ በጣም ሞቃታማ በመሆነ ከቤት ውጭ እንዳያሳልፉ አስጠንቅቀዋል። ባለፈው አመት ቢያንስ 240 ሰዎች በሙቀት የተነሳ ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
10.0K views05:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-17 08:04:52
ገንዘብዎ ዋጋ የሚያገኝበት ትልቁ ስፍራ!

አያት አክስዮን ማህበር በ2015 ዓ.ም 51% ትርፍ /dividend/ ለባላክሲዮኖች አከፋፍሏል

የ8 ድርጅት ባለቤት ይሁኑ


የ 1 ሚሊዮን ብር አክሲዮን የነበራቸው ባለአክሲዮኖች 510ሺ ብር ትርፍ/Dividend/ አግኝተዋል

የ 5 ሚሊዮን ብር የገዙ 2.5 ሚሊዮን ብር አትርፈዋል

የአንድ አክሲዮን ዋጋ 100 ብር ነው

ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው የአክሲዮን መጠን 2500 ነው

ዝቅተኛ የአክሲዮን ዋጋ 262,500 ብር ፣ 5% የአገልግሎት ክፍያን ጨምሮ

112,500 ብር ከፍለው ቀሪውን በሶስት ዓመት መጨረስ ይችላሉ

ከፍተኛ አክሲዮን ገደብ የለውም

አክሲዮኑን ከገዙ ከአንደኛው ወር ጀምሮ የትርፍ ተካፋይ ይሆናሉ

ለበለጠ መረጃ: በ 0910798353/ 0926692990 ይደውሉ ( ቀጥታ ወይም Whatsapp) @ABTrealtor
8.8K views05:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-17 08:04:46
መኪና ለመግዛት ወይም ለመሸጥ ከፈለጉ ያለምንም ክፍያ
ይህንን የቴሌግራም መተግበሪያ ይቀላቀላሉ።

https://t.me/Poppycarmarket

0911407105   ይደውሉልን
7.4K views05:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-17 08:04:38
የጥርስ , የእግር ና የአፍንጫ
           ማስተካከያ

የጥርስ
በአበቃቀል የተዛባ ጥርስ ማስተካከያ በአበቃቀል የተዛባ ጥርስ
ለላይኛው እና ለታችኛው እኩል የሚያስተካክል
 
የአፍንጫ ማስተካከያ
በአጭር ጊዜ በተፈጥሮ እና በአደጋ ለተዛባ አፍንጫ ውበትን ያላብሳል

የአውራ ጣት
ከጫማ ጋር የሚደረግ 
በአጭር ግዜ ያስተካክላል
አንዱ ለሁለቱም እግር የሚሆን

ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
የአጠቃቀም Video እንልክልዎታለን

Price #1500 birr ብቻ
ያሉበት ቦታ ድረስ በነፃ እናደርሳለን (free delivery)

0942163022

አድራሻ ► ቦሌ
8.5K views05:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-16 18:49:29
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ነቀምቴ በረራውን በይፋ ጀምሯል

የነቀምቴ ጉዲና ቱምሳ አውሮፕላን ማረፊያ የበረራ ማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓት በዛሬ እለት ተከናውኗል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
24.9K views15:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-16 12:50:08
በመዲናዋ ዋና መንገዶች ላይ የሚገኙ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ክፍት እንዲሆኑ ተወሰነ

የኮሪደር ልማት በሚከናወንባቸው አካባቢዎችና በከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች ላይ የሚገኙ የንግድና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ከተለመደው የሥራ ሠዓት በተጨማሪ ቢያንስ እስከ ምሽቱ 3 ሰአት ድረስ ክፍት በማድረግ የንግድና የአገልግሎት ስራዎች እንዲካሄዱ መወሰኑ ተገልጿል።

ከአዲስ አበባ ከተማአስተዳደር ንግድ ቢሮ በትላንትናው ዕለት (ሰኔ 7፣ 2016 ዓ.ም) ተፈርሞ የወጣውና ለአሥራ አንዱም ክፍለ ከተሞች የተጻፈው ደብዳቤ ክፍለ-ከተሞች ይህንኑ ውሳኔ ለንግዱ ማህበረሰብ በአግባቡ እንዲያስገነዝቡ ያዛል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
31.6K views09:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-15 13:49:18 ​​ነገ አዲስ አበባ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆነዋል

የ1445ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል ነገ ይከበራል።

የኢድል አል አድሃ (አረፋ) በዓል ሶላት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅም ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

የሶላት ስነስርዓቱ የሚካሄደው በአዲስ አበባ ስታዲዮምና በዙሪያው በሚገኙ ዋና ዋና መንገዶች ላይ ነው።

ይህ ተከትሎ ከለሊቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ የሶላት ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።

በዚህም መሰረት ፦

- ከፒያሳ በቸርችል ጎዳና ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ ላይ

- ከጎተራ ማሳለጫ ወደ ስታዲዮም የሚወስደው አጎና ሲኒማ ላይ

- ከሜክሲኮ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ሜክሲኮ አደባባይ ላይ

- ከብሔራዊ ቤ/መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ፓርላማ መብራት ላይ

- ከኦሎሚፒያ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ

- ከመገናኛ ወደ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ 22 መስቀለኛ መንገዱ አካባቢ

- ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ለገሀር የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ ሼል አጠገብ

- ከሲግናል እና ከአቧሬ ወደ ካዛንቺስ የሚመጣው መንገድ አቧሬ ሴቶች አደባባይ ላይ

- ከመስቀል ፍላወር ወደ መስቀል አደባባይ የሚመጣው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ

- ከቄራ በአዲሱ መንገድ ወደ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መገንጠያ ላይ

- ከጌጃ ሰፈር በሰንጋተራ ወደ ለገሐር ለሚመጡ አሽከርካሪዎች ሰንጋ ተራ 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት አካባቢ

- ከአብነት በጌጃ ሰፈር ወደ ብሔራዊ ቴአትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ አጠገብ

- ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በሜትሮሎጂ ወደ ብሔራዊ ቴአትር ሜትሮሎጂ መ/ቤት ላይ

- ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የኋላ በር ወደ ብሔራዊ ቴአትር ለሚሄዱ ጥቁር አንበሳ ሼል ድሬንስ አካባቢ

- ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በጎላ ሚካኤል ውስጥ ለውስጥ ወደ ለገሐር ለሚሄዱ ጎላ ሚካኤል መስቀለኛው ላይ

ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ከለሊቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።

ህብረተሰቡ ይህን ተገንዝቦ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀም ጥሪ ቀርቧል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
37.7K views10:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-15 13:09:06 ​​የጋራ ግብረ ሃይሉ ለአረፋ በዓል አከባበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ

ለኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል አከባበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ተግባር መግባቱን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሃይል አስታወቀ፡፡

1 ሺህ 445ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል ሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ይከበራል፡፡

በዓሉን ምክንያት በማድረግም በአዲስ አበባ ስታዲየምና በዙሪያው እንዲሁም በአቃቂ ቃሊቲ አና በሌሎች ክ/ከተሞች ላይ በሚገኙ መስጂዶች ለሚከናወነው የኢድ ሶላት ስነ-ስርዓት የፀጥታ አካላት ለሚያከናውኑት የፀጥታ ስራ ምዕመናኑ ተባባሪ እንዲሆን ግብረ ሃይሉ ጠይቋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው÷ የፀጥታ ኃይሉን ቅድመ ዝግጅት አስመልክቶ በተደረገው ውይይት እንደ ከዚህ ቀደሙ የህዝቡን አቅም በተገቢው መጠቀም እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ በሰጡት የስራ መመሪያ በህብረተሰቡ ውስጥ ተመሳስለው የሚገኙትን ፀረ-ሰላም ኃይሎች የመመንጠሩ ስራ እንዲሁም በዘረፋ፣ በሌብነት እና በሌሎች ወንጀሎች ላይ የተሰማሩ ህገ-ወጦች ላይ የተጀመረው ኦፕሬሽን ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በዓሉ በሰላም እንዲከበር ሁሉም በተሰማራበት የፀጥታ ስራ ኃላፊነቱን እንዲወጣም ጥብቅ የስራ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በበኩላቸው መላው የከተማዋ ነዋሪዎች የፀጥታውን ስራ በመደገፍ በኩል እያበረከቱ ያሉትን አስተዋፅኦ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የሰላም ሰራዊት አባላት ለከተማችን ሰላም እየተወጡት ያለውን ድርሻ በማጎልበት ለበዓሉ ሰላማዊነት ከፀጥታ አካሉ ጋር ተቀናጅተው እንዲሰሩ አቅጣጫ ተሰጥቷል ብለዋል፡፡

በያዝነው ዓመት በአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ በስፋት ወደ አደባባይ በመውጣት ያከበራቸው ኃይማኖታዊና ብሔራዊ በዓላት ካለምንም የፀጥታ ችግር መከበራቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው አስታውሰዋል፡፡

ይህ ውጤት የተገኘው የፀጥታው ኃይሉ ከህብረተሰብ ጋር ተቀናጅቶ በመስራቱ እንደሆነም ጠቅሰዋል፡፡

ከህብረተሰቡ ጋር በመስራታችን ወንጀልን ለመከላከል እና አጥፊዎችን ህግ ፊት ለማቀርብ እያገዘን ስለሆነ የህብረተሰቡ እና የፀጥታ አካላት ጥምረት እንዲጎለብት ትኩረት ተሰጥቶበት እየተሰራ መሆኑንም ኮሚሽነሩ ገልፀዋል፡፡

በአዲስ አበባ ስታዲየምና በልዩ ልዩ መስጂዶች ከሚደረገው የሶላት ስነ-ስርዓት በተጨማሪ በክፍለ ከተሞች ለሚከናወነው የኢድ ሶላት የሚመጡ ምዕመናን ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻ ስለሚኖር ህብረተሰቡ ይህንን ተገንዝቦ የተለመደ ትብብሩ እንዲያደርግ መልዕክቱን ያስተላለፈው የጋራ ግብረ ሃይሉ፤ ለመላው የእምነቱ ተከታዮችም በዓሉ የሰላምና የደስታ እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡

ለስራው ስኬታማነት ህብረተሰቡ እያደረገ ላለው ትብብር ግብረ ኃይሉ ምስጋናውን አቅርቦ ጥቆማ ለመስጠትም ይሁን የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘት በስልክ ቁጥር፡-
• 011-5-52-63-03
• 011-5-52-40-77 መጠቀም እንደሚቻል የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ጠቁሟል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
36.5K views10:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-15 11:28:56
መንግስት የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ የባንክ አካዉንት እንዲታገድ አደረገ

ተቋሙ በምን ምንክንያት እንደሆነ በማናዉቅበት ምክንያት በአንድ ዓመት ዉስጥ ለ 3ኛ ጊዜ የባንክ አካዉንቱ ሙሉ በሙሉ እንዲታገድ መደረጉን አስታዉቋል ።

ፐርፐዝ ብላክ ባለፉት ሳምንታት ተቋሙን ህልዉና ዉስጥ የሚከተዉ ችግሮች እንደገጠመው አስታዉቋል።

ላለፉት ሶስት ሳምንታት የተቋሙ አካዉንት ሙሉ በሙሉ እንዲዘጋ ከመደረጉ በተጨማሪ የዋና ስራ አስፈጻሚዉ ፍስሃ እሸቱ ( ዶ/ር) አካዉንት ጨምር ተመሳሳይ እጣ ፈንታ መድረሱ ተገልጿል።

ደመወዝ መክፈል የማንችልበት ደረጃ ላይ ደርሰናል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው የቢሮ ኪራይን ጨምሮ የፕሮጀክቶች ስራዎች እንዲቆሙ መደረጉ ስራ አስፈፃሚው በሰጠዉ መግለጫ ገልጿል ።

ከ20 ሺህ በላይ ባለአክሲዮኖች እንዳሉት እና ከ 1 ሺህ በላይ ቋሚ ሰራተኞች ያሉት ተቋሙ አሁን ላይ ካፒታሉ 2.4 ቢሊዮን ብር መድረሱን አስታዉቋል ።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
34.7K views08:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ