Get Mystery Box with random crypto!

በእሳት አደጋ የፕላስቲክ ፋብሪካ በከፊል ወደመ አዲስ ከተማ ክፍለ-ከተማ ወረዳ አራት 18 ማዞሪ | ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

በእሳት አደጋ የፕላስቲክ ፋብሪካ በከፊል ወደመ

አዲስ ከተማ ክፍለ-ከተማ ወረዳ አራት 18 ማዞሪያ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ትናንት ከሌሊቱ 10:10 ሰዓት አቡኒ የፕላስቲክ ዉጤቶች ማምረቻ ፋብሪካ ላይ ተነስቶ በነበረዉ የእሳት አደጋ ፋብሪካዉ በከፊል መውደሙን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳወቀ።

የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለኢፕድ በሰጡት መረጃ እንዳሉት የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር ስምንት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪና ሁለት የዉሀ ቦታ ከ56 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር ተሰማርቷል።

ባለሙያው የእሳት አደጋዉ በአቅራቢያዉ ባሉ መኖሪያ ቤቶች ላይ ተዛምቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳይደርስ መቆጣጠር ተችሏል ብለዋል።

በአደጋዉ ለመልሶ መጠቀም ግልጋሎት የሚዉሉ ጥሬ ዕቃዎች እና ማሽነሪዎች ላይ ከባድ ጉዳት በመድረሱ ፋብሪካዉ በከፊል ወድሟል።

በፋብሪካዉ የአደጋ ደህንነትን መስፈርት ያልጠበቁ ያገለገሉ የፕላስቲክ ዉጤቶች ክምችት እንዲሁም ስፍራዉ የአደጋ መቆጣጠር ተሽርከርካሪውችን የማያስገባ መሆኑ ለአደጋዉ መስፋፋት አስተዋጾኦ አድርጓል።

የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር ሁለት ሰዓት የፈጀ ሲሆን በአደጋዉ በሰዉ ላይ የደረሰ ጉዳት የለም ተብሏል።
(ኢ ፕ ድ)

@Esat_tv1
@Esat_tv1