Get Mystery Box with random crypto!

ኢራን የመጀመርያ ደረጃ ሪፖርት ይፋ አደረገች የኢራን የጦር ኃይሎች፤ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ | ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

ኢራን የመጀመርያ ደረጃ ሪፖርት ይፋ አደረገች

የኢራን የጦር ኃይሎች፤ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲን ጨምሮ ከፍተኛ የሀገሪቱ ባለስልጣናትን አሳፍሮ በነበረ ሄሊኮፕተር ላይ የደረሰውን አደጋ በተመለከተ በትናንትናው ዕለት የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

በሪፖርቱ ከአደጋው ጋር የተያያዙ የቴክኒክና አጠቃላይ መረጃዎችና ግኝቶች እንደተሰበሰቡና እንደተመረመሩ ተገልጿል።

ለምርመራ ተጨማሪ ጊዜ የሚጠይቁ አንዳንድ መረጃዎች መኖራቸው በሪፖርቱ ተመላክቷል።

በቅድመ ምርመራው መሰረት ሄሊኮፕተሩ የበረራ መስመሩን ሳይቀይር አስቀድሞ በወሰነው መስመር መጓዙ ተጠቁሟል፡፡

የሄሊኮፕተር አብራሪ አደጋው ከመከሰቱ ከአንድ ደቂቃ ከሰላሳ ሰከንድ በፊት ከሌሎች ሁለት ሄሊኮፕተሮች አብራሪዎች ጋር ተገናኝቶ እንደነበር ተረጋግጧል።

በቀሪዎቹ የሄሊኮፕተሩ ክፍሎች በመሳርያ የመመታት ምልክትም ሆነ ተመሳሳይ ጉዳት እንዳልተገኘና ከአደጋው በኋላ ሄሊኮፕተሩ በእሳት እንደተያያዘ ዘገባው አመልክቷል።

አካባቢው ወጣ ገባ የሆነ የመሬት አቀማመጥ ያለው መሆኑ እንዲሁም ቀዝቃዛና ጭጋጋም የአየር ጸባይ የፍለጋ ሥራውን ከባድ አድርጎት እንደነበር ተመላክቷል።

የምርመራው የመጨረሻ ውጤት በቅርቡ ተጠናቆ ይፋ እንደሚደረግ መገለፁን አናዶሉ ኤጀንሲ ዘግቧል፡፡

የኢራኑ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ ባሳለፍነው እሁድ በሄሊኮፕተር አደጋ ሕይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።

በአደጋው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴይን አሚር አብዶላሂያን ጨምሮ ሌሎች ባለስልጣናት እና የሄሊኮፕተር በረራ ክፍል አባላት ህይወት አልፏል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1