Get Mystery Box with random crypto!

ሰዋስው/@zsewasw

የቴሌግራም ቻናል አርማ zsewasw — ሰዋስው/@zsewasw
የቴሌግራም ቻናል አርማ zsewasw — ሰዋስው/@zsewasw
የሰርጥ አድራሻ: @zsewasw
ምድቦች: ቋንቋዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.05K
የሰርጥ መግለጫ

ሰዋስው
# ሰዋስው ማለት መሰላል ነው።
መሰላል የማይደርሱበት ነገር ተጠቅመው እንዲቻል እንደሚያደርጉት ሁሉ በዚህም ቻናል ችግር የሚባል ነገርን አስወግዳችሁ ወደ መልካም ነገር የምትወጡበትን ትምህርት ታገኛላችሁ።
እኔን ለማግኘት የሚፈልግ ሁሉ
251934636523

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-08 07:57:25 አክሊል ዘሰዋስው
@zsewasw
726 viewsሰዋስው, 04:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 13:05:17
313 viewsሰዋስው, 10:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 08:33:19 Address
@akli3
0934636523
367 viewsሰዋስው, 05:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 08:20:15
ወዳጄ!!

ጥዋት ስትነሳ ብዙ ጊዜ ያለህ ሰማይን መጨበጥ ፣የምትችል ነው የሚመስልህ፣ነገር ግን ማታ ስትቀመጥ ምንም እንዳላደረክ ስታስብ ቀኖችህ በከንቱ እንደባከኑ ሲገባህ እጂግ በጣም ታዝናለህ።ወዳጄ ይሄውልህ ጥዋት፣ለአንተ የወጣትነትህ ጊዜ ነው።ማታ ደግሞ የእርጂናህ ጊዜ ነው። ታዲያ ወዳጄ ጥዋት፣ወጣትነተህ ብዙ ጊዜ ያለህ ነገሮችን ቀስ ብለህ ማድረግ ያለብህ እየመሰለክ ጊዜህን ሳታውቀው ማታ ላይ ይደርሳል እርጂና ይመጣል።ያኔ ምነው ነገሮችን ጥዋት ባደርጋቸው እንዳትል በሕይወት ዘመንህ አምላክህ ለአንተ መመሪያ ይሆን ዘንድ፣ቀንና ማታ አድረጎ ፈጥሮልሃል።ቀን፣ጥዋት ስትነሳ ማታ እንደሚመጣ አስብ ወጣት ሳለህ እርጂና እንደሚመጣ አስተውል።ያኔ በሕይወት ዘመንህ ምን ማድረግ እንዳለብህ ወዴት እንደምትሄድ ስለምታውቅ ወጣትነትህ ጥዋትህ ትጠቀማለህ።
ሰናይ ጥዋት ተመኘሁ

@Zsewasw

አክሊል ዘሰዋስው
1.1K viewsሰዋስው, 05:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 15:28:41
ወዳጄ!!

የአንተን ወርቅ ለመፈለግ መሰደድ አይጠበቅብህም።ብዙ ሰው የእሱ የሆነ ወርቅ ሌላ ቦታ ያለ ነው የሚመስለው ወዳጄ የአንተ ወርቅ ከአንተ ጋር ነው።
ቁልፉ ከቤት ጠፍቶት ውጪ እንደፈለገው ሰው አትሁን።የእራስህን ዓለም አስፈሪና ጨለማ አድረገህ አትሳለው፣አንተ ብርሃናዊ ሕይወት አለው የምትለው ሰው ብርሃናዊ ሕይወት ከመኖሩ በፊት ጨለማ ያደረከውን ሕይወት ተጋፍጧል።
ብዙዎች የእራሳቸውን ወርቅ ለመፈለግ ሲሉ ወደውጭ ወጥተው ይቀራሉ። ነገር ግን ወርቃቸው ከእነሱ ጋር እንጂ ሌላ ቦታ አይደለም።ወርቅህን ሌላ ቦታ ለመፈለግ አትሰደድ .............

ሰናይ ጊዜ ተመኘሁ
@zsewasw
አክሊል ዘሰዋስው
1.2K viewsሰዋስው, 12:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 07:44:31 ወዳጄ

#ከማን_ጋር_ነህ

'ሁልጊዜ ከሁለት ነገሮች በስተቀር በአምስት አመት ውስጥም ልክ እንደዛሬው ነህ’ ይላል፡፡”

“ሁለቱ ነገሮችማ የምታገኛቸው ሰዎችና የምታነባቸው መጻህፍት ናቸው፡፡ አስበው እኛ ያለን እውቀትና አብረናቸው የምንሆናቸው ሰዎች ድምር ውጤት ነን፡፡ ከጋዜጣ በስተቀር ምንም ነገር የማታነብ ከሆነ፣ የምታውቀው ያንን ብቻ ይሆናል፡፡ የምታነበው የታላላቅ ሰዎችን የህይወት ታሪክና መንፈስን የሚቀሰቅሱ መፃህፍትን ከሆነ የምታውቀው ያንን ብቻ ይሆናል፡፡” 

‘በተመራማሪዎች ዙሪያ ስትሆን የተሻለ ተመራማሪ ትሆናለህ፡፡ በአሸናፊዎች ዙሪያ ስትሆን የተሻለ አሸናፊ ትሆናለህ፡፡ በሚያማርሩና ችክ ባሉ ሰዎች ዙሪያ ስትሆን የተሻለ አማራሪና ችክ ያልክ ትሆናለህ’ ይላል፡፡”

           
. እያንዳንዱን ቀን በድፍረት ኑር
. በምትሰራው ነገር ኩራ፡፡
. ሁልጊዜ የጀመርከውን ጨርስ፡፡
. መሰራት ያለበትን ስራ
. ጠንካራ ግን ጨዋ ሁን፡፡
. ቃል ከገባህ ቃልህን ጠብቅ፡፡
. ቃል በገባኸው ተልዕኮ ላይ ሂድ፡፡
. ትንሽ አውራ ብዙ አትናገር፡፡
. አንዳንድ ነገሮች የማይሸጡ መሆናቸውን አስታውስ።
. መስመሩን  የት ማስመር እንዳለብህ እወቅ፡፡
          
453 viewsሰዋስው, edited  04:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 12:33:06 ወዳጄ

#መዘግየት፥

የሕይወትህ ግቦች ላይ እንዳትደርስ የሚያደርግህ በመሆኑ ከህይወትህ ሙሉ በሙሉ መወገድ ያለበት ብቸኛው ውጫዊ እንቅፋት ነው። ስለዚህ ከዛሬ ጀምሮ ለአላማህ መስራት ጀምር። የመጀመሪያውን እርምጃ ውሰድ፥ ከዚያ በጭራሽ ሳታቆም ወደ ህልምህ መጓዝህን ቀጥል። ምንም ነገር ዘግይቶ አያውቅም፨ የማያቋርጥ ጥረት ለስኬትና ለአዎንታዊ ሕይወት ብቸኛው ቁልፍ ነው፨
@zsewasw
1.2K viewsሰዋስው, 09:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 12:52:19
ወዳጄ!!

ትዝብት

የሶሻል ሚዲያ ተጽዕኖና ፕሮግራሚንግ።
አሁን አሁን ሶሻል ሚዲያ ሰውን ከሰው ከማገናኘት አልፎ ፣የመረጃ መለዋወጫ ከሆነ ሰነባብቷል።ማንም ቢሆን እሱን ከመጠቀም የሚያርፍ የለም።እና ሰዎች ብዙ ጊዜ የሚገቡት ዛሬ ምን ተወራና ምን አደጋ ደረሰ ፣የሰው ምስል like ለማድረግ ነው። ታዲያ በዚህ ቤት የሚጠቅም ነገር post ከተደረገው ይልቅ የማይጠቅመው ነገር በጣም ኃይል ኑሮት ታያለችሁ።ይህ ነገር  የመጣው ከፕሮግራሚንግ ነው።አዕምሮ ሁሌም ከአስለመድከው ውጭ መስማት፣ ማየት አይፈልግም። ሁሌም ቢሆን መልካም ልምድ ከሌለህ መልካም ነገር መስማት አያስደስትህም።አዕምሮህ የለመደው ይህን አይደማ፣ ሶሻል ሚዲያ ደግሞ አሁን ላይ የመልካም ነገሮች ይልቅ መጥፎ ነገሮች የሚበዙበት ሁኗል።መልካም ነገሮች ብዙ ጊዜ ትኩረት አይሰጣቸውም።ዛሬ ወደን ፈቅደን ወደ አዕምሮችን የምንዘራው ዘር በኃላ ላይ ፍሬ ሁኖ ይበቅላል። ሁሉም የዘራውን ያጭዳልና። ተክል ያለ ዘር እንደማይበቅል ሁሉ፣የሰውም እያንዳንዱ ድርጊት ከተደበቀው የሃሳብ ዘር ይመነጫል። በሕይወትህ አንተ ከምታስባቼው ሃሳቦች ውጭ ነገሮች አይከሰቱም፣አስበህም አቅደህም ከምታደርጋቼውና ድንገት ከሚከሰቱት ጀምሮ እያንዳንዱ ነገሮች ከዚህ በፊት ስታስባቼው የነበሩ የሃሳቦችህ ውጤቶች ናቸው። ወዳጄ፣ ድርጊት የሃሳብ ችግኝ ነው፣ደስታና ስቃይም የሃሳብ ፍሬዎች ናቸው።እናም መልካም ነገሮችን post እናድርግ መልካም ነገሮችን እንልቀቅ። ለመልካም ነገሮች ትኩረት፣ መልካም ዘር እንዝራ።

ድንቅ ጊዜ
አክሊል ዘሰዋስው
1.7K viewsሰዋስው, 09:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-15 10:57:26 ወዳጄ!!

"ኢይጻዓ ዓቢይ ነገር እምአፉክሙ"


ታላቅ ነገር ከአፋችሁ አይውጣ
ብዙ ጊዜ አንድ ሰው ሳያውቅ ለምዶበት ከአንደበቱ የሚያወጣው ቃል ሌሎችን ከማስቀየም ባለፈ እራሱን ሲከነክነው ይኖራል። በሕይወት ስትኖር ሳታውቅ በስሕተት፣ እያወቅ በድፍረት የምትሰራው ክፉ ነገር በወደፊት ሕይወትህ ትልቅ ተጽዕኖ ይፍጥራል።ሰው የዘራውን ያጭዳል፣መልካም ነገር ከዘራህ መልካም ነገር፣ክፉ ነገር ከዘራህ ክፉ፣ ታጭዳለህ።ታዲያ የዚህ ሁሉ ነገር መነሻ ሃሳብ ነው።ተክል ያለ ዘር እንደማይበቅል ሁሉ፣የሰውም እያንዳንዱ ድርጊት ከተደበቀው የሃሳብ ዘር ይመነጫል። በሕይወትህ አንተ ከምታስባቼው ሃሳቦች ውጭ ነገሮች አይከሰቱም፣አስበህም አቅደህም ከምታደርጋቼውና ድንገት ከሚከሰቱት ጀምሮ እያንዳንዱ ነገሮች ከዚህ በፊት ስታስባቼው የነበሩ የሃሳቦችህ ውጤቶች ናቸው። ወዳጄ፣ ድርጊት የሃሳብ ችግኝ ነው፣ደስታና ስቃይም የሃሳብ ፍሬዎች ናቸው።
ለዛም ነው መጽሐፍ "መልካም ሰው ከመልካም መዝገብ ልቡ መልካም ነገር ይናገራል፣ ክፉ ሰው ከክፉ መዝገብ ልቡ ክፉ ነገር ይናገራል።

ድንቅ ጊዜ
የእናተው ታናሽ አክሊል ዘሰዋስው
@zsewasw
2.0K viewsሰዋስው, edited  07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 14:27:37 ወዳጄ!!!

ሰው እራሱ ያሰበውን መሆን ይችላል። በሕይወትህ መሆን የምትፈለገውን ነው መሆን የምትችለው። እግዚአብሔር አምላክ የአንተን ሕይወት ቀርጾ አይሰጥም።አንተ እንጂ መቅርጽ የምትችለው። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ይላል"እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ሕይወትህ እንዲህ ይሆናል ብሎ አይወስንም የሰውን ሕይወት መቅረጽ የሚችለው እሱ እራሱ ነው" ይላል
እግዚአብሔር የሰውን ልጆች ሕይወት ያውቃል ማለት ይወስናል ማለት አይደለም። በወስንና በማወቅ ትልቅ ልዩነት አለ።አንድ ዶክተር ታማሚውን ዛሬ ትሞታለህ ቢለው ዶክተሩ ገደለው አይባልም።ዶክተሩ መሞቱን ቀድሞ አወቀ እንጂ።
እግዚአብሔር አምላክ የሰውን ሕይወት ቀድሞ ያውቃል ማለት ይወስናል ማለት አይደለም።
ቅዱስ አትናቴዎስ" ጻድቁን ጽድቅ ሳይሰራ ያውቀዋል፣ ኃጥኡንም ኃጢአት ሳይሰራ ያውቀዋል።

ድንቅ ጊዜ

አክሊል ዘሰዋስው
@zsewasw
1.9K viewsሰዋስው, 11:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ