Get Mystery Box with random crypto!

ወዳጄ!! 'ኢይጻዓ ዓቢይ ነገር እምአፉክሙ' ታላቅ ነገር ከአፋችሁ አይውጣ ብዙ ጊዜ አንድ ሰ | ሰዋስው/@zsewasw

ወዳጄ!!

"ኢይጻዓ ዓቢይ ነገር እምአፉክሙ"


ታላቅ ነገር ከአፋችሁ አይውጣ
ብዙ ጊዜ አንድ ሰው ሳያውቅ ለምዶበት ከአንደበቱ የሚያወጣው ቃል ሌሎችን ከማስቀየም ባለፈ እራሱን ሲከነክነው ይኖራል። በሕይወት ስትኖር ሳታውቅ በስሕተት፣ እያወቅ በድፍረት የምትሰራው ክፉ ነገር በወደፊት ሕይወትህ ትልቅ ተጽዕኖ ይፍጥራል።ሰው የዘራውን ያጭዳል፣መልካም ነገር ከዘራህ መልካም ነገር፣ክፉ ነገር ከዘራህ ክፉ፣ ታጭዳለህ።ታዲያ የዚህ ሁሉ ነገር መነሻ ሃሳብ ነው።ተክል ያለ ዘር እንደማይበቅል ሁሉ፣የሰውም እያንዳንዱ ድርጊት ከተደበቀው የሃሳብ ዘር ይመነጫል። በሕይወትህ አንተ ከምታስባቼው ሃሳቦች ውጭ ነገሮች አይከሰቱም፣አስበህም አቅደህም ከምታደርጋቼውና ድንገት ከሚከሰቱት ጀምሮ እያንዳንዱ ነገሮች ከዚህ በፊት ስታስባቼው የነበሩ የሃሳቦችህ ውጤቶች ናቸው። ወዳጄ፣ ድርጊት የሃሳብ ችግኝ ነው፣ደስታና ስቃይም የሃሳብ ፍሬዎች ናቸው።
ለዛም ነው መጽሐፍ "መልካም ሰው ከመልካም መዝገብ ልቡ መልካም ነገር ይናገራል፣ ክፉ ሰው ከክፉ መዝገብ ልቡ ክፉ ነገር ይናገራል።

ድንቅ ጊዜ
የእናተው ታናሽ አክሊል ዘሰዋስው
@zsewasw