Get Mystery Box with random crypto!

ወዳጄ!!! ሰው እራሱ ያሰበውን መሆን ይችላል። በሕይወትህ መሆን የምትፈለገውን ነው መሆን የምትች | ሰዋስው/@zsewasw

ወዳጄ!!!

ሰው እራሱ ያሰበውን መሆን ይችላል። በሕይወትህ መሆን የምትፈለገውን ነው መሆን የምትችለው። እግዚአብሔር አምላክ የአንተን ሕይወት ቀርጾ አይሰጥም።አንተ እንጂ መቅርጽ የምትችለው። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ይላል"እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ሕይወትህ እንዲህ ይሆናል ብሎ አይወስንም የሰውን ሕይወት መቅረጽ የሚችለው እሱ እራሱ ነው" ይላል
እግዚአብሔር የሰውን ልጆች ሕይወት ያውቃል ማለት ይወስናል ማለት አይደለም። በወስንና በማወቅ ትልቅ ልዩነት አለ።አንድ ዶክተር ታማሚውን ዛሬ ትሞታለህ ቢለው ዶክተሩ ገደለው አይባልም።ዶክተሩ መሞቱን ቀድሞ አወቀ እንጂ።
እግዚአብሔር አምላክ የሰውን ሕይወት ቀድሞ ያውቃል ማለት ይወስናል ማለት አይደለም።
ቅዱስ አትናቴዎስ" ጻድቁን ጽድቅ ሳይሰራ ያውቀዋል፣ ኃጥኡንም ኃጢአት ሳይሰራ ያውቀዋል።

ድንቅ ጊዜ

አክሊል ዘሰዋስው
@zsewasw