Get Mystery Box with random crypto!

ወዳጄ!! ትዝብት የሶሻል ሚዲያ ተጽዕኖና ፕሮግራሚንግ። አሁን አሁን ሶሻል ሚዲያ ሰውን ከሰው | ሰዋስው/@zsewasw

ወዳጄ!!

ትዝብት

የሶሻል ሚዲያ ተጽዕኖና ፕሮግራሚንግ።
አሁን አሁን ሶሻል ሚዲያ ሰውን ከሰው ከማገናኘት አልፎ ፣የመረጃ መለዋወጫ ከሆነ ሰነባብቷል።ማንም ቢሆን እሱን ከመጠቀም የሚያርፍ የለም።እና ሰዎች ብዙ ጊዜ የሚገቡት ዛሬ ምን ተወራና ምን አደጋ ደረሰ ፣የሰው ምስል like ለማድረግ ነው። ታዲያ በዚህ ቤት የሚጠቅም ነገር post ከተደረገው ይልቅ የማይጠቅመው ነገር በጣም ኃይል ኑሮት ታያለችሁ።ይህ ነገር  የመጣው ከፕሮግራሚንግ ነው።አዕምሮ ሁሌም ከአስለመድከው ውጭ መስማት፣ ማየት አይፈልግም። ሁሌም ቢሆን መልካም ልምድ ከሌለህ መልካም ነገር መስማት አያስደስትህም።አዕምሮህ የለመደው ይህን አይደማ፣ ሶሻል ሚዲያ ደግሞ አሁን ላይ የመልካም ነገሮች ይልቅ መጥፎ ነገሮች የሚበዙበት ሁኗል።መልካም ነገሮች ብዙ ጊዜ ትኩረት አይሰጣቸውም።ዛሬ ወደን ፈቅደን ወደ አዕምሮችን የምንዘራው ዘር በኃላ ላይ ፍሬ ሁኖ ይበቅላል። ሁሉም የዘራውን ያጭዳልና። ተክል ያለ ዘር እንደማይበቅል ሁሉ፣የሰውም እያንዳንዱ ድርጊት ከተደበቀው የሃሳብ ዘር ይመነጫል። በሕይወትህ አንተ ከምታስባቼው ሃሳቦች ውጭ ነገሮች አይከሰቱም፣አስበህም አቅደህም ከምታደርጋቼውና ድንገት ከሚከሰቱት ጀምሮ እያንዳንዱ ነገሮች ከዚህ በፊት ስታስባቼው የነበሩ የሃሳቦችህ ውጤቶች ናቸው። ወዳጄ፣ ድርጊት የሃሳብ ችግኝ ነው፣ደስታና ስቃይም የሃሳብ ፍሬዎች ናቸው።እናም መልካም ነገሮችን post እናድርግ መልካም ነገሮችን እንልቀቅ። ለመልካም ነገሮች ትኩረት፣ መልካም ዘር እንዝራ።

ድንቅ ጊዜ
አክሊል ዘሰዋስው