Get Mystery Box with random crypto!

ወዳጄ #ከማን_ጋር_ነህ 'ሁልጊዜ ከሁለት ነገሮች በስተቀር በአምስት አመት ውስጥም ልክ እንደ | ሰዋስው/@zsewasw

ወዳጄ

#ከማን_ጋር_ነህ

'ሁልጊዜ ከሁለት ነገሮች በስተቀር በአምስት አመት ውስጥም ልክ እንደዛሬው ነህ’ ይላል፡፡”

“ሁለቱ ነገሮችማ የምታገኛቸው ሰዎችና የምታነባቸው መጻህፍት ናቸው፡፡ አስበው እኛ ያለን እውቀትና አብረናቸው የምንሆናቸው ሰዎች ድምር ውጤት ነን፡፡ ከጋዜጣ በስተቀር ምንም ነገር የማታነብ ከሆነ፣ የምታውቀው ያንን ብቻ ይሆናል፡፡ የምታነበው የታላላቅ ሰዎችን የህይወት ታሪክና መንፈስን የሚቀሰቅሱ መፃህፍትን ከሆነ የምታውቀው ያንን ብቻ ይሆናል፡፡” 

‘በተመራማሪዎች ዙሪያ ስትሆን የተሻለ ተመራማሪ ትሆናለህ፡፡ በአሸናፊዎች ዙሪያ ስትሆን የተሻለ አሸናፊ ትሆናለህ፡፡ በሚያማርሩና ችክ ባሉ ሰዎች ዙሪያ ስትሆን የተሻለ አማራሪና ችክ ያልክ ትሆናለህ’ ይላል፡፡”

           
. እያንዳንዱን ቀን በድፍረት ኑር
. በምትሰራው ነገር ኩራ፡፡
. ሁልጊዜ የጀመርከውን ጨርስ፡፡
. መሰራት ያለበትን ስራ
. ጠንካራ ግን ጨዋ ሁን፡፡
. ቃል ከገባህ ቃልህን ጠብቅ፡፡
. ቃል በገባኸው ተልዕኮ ላይ ሂድ፡፡
. ትንሽ አውራ ብዙ አትናገር፡፡
. አንዳንድ ነገሮች የማይሸጡ መሆናቸውን አስታውስ።
. መስመሩን  የት ማስመር እንዳለብህ እወቅ፡፡