Get Mystery Box with random crypto!

ወዳጄ!! ጥዋት ስትነሳ ብዙ ጊዜ ያለህ ሰማይን መጨበጥ ፣የምትችል ነው የሚመስልህ፣ነገር ግን ማታ | ሰዋስው/@zsewasw

ወዳጄ!!

ጥዋት ስትነሳ ብዙ ጊዜ ያለህ ሰማይን መጨበጥ ፣የምትችል ነው የሚመስልህ፣ነገር ግን ማታ ስትቀመጥ ምንም እንዳላደረክ ስታስብ ቀኖችህ በከንቱ እንደባከኑ ሲገባህ እጂግ በጣም ታዝናለህ።ወዳጄ ይሄውልህ ጥዋት፣ለአንተ የወጣትነትህ ጊዜ ነው።ማታ ደግሞ የእርጂናህ ጊዜ ነው። ታዲያ ወዳጄ ጥዋት፣ወጣትነተህ ብዙ ጊዜ ያለህ ነገሮችን ቀስ ብለህ ማድረግ ያለብህ እየመሰለክ ጊዜህን ሳታውቀው ማታ ላይ ይደርሳል እርጂና ይመጣል።ያኔ ምነው ነገሮችን ጥዋት ባደርጋቸው እንዳትል በሕይወት ዘመንህ አምላክህ ለአንተ መመሪያ ይሆን ዘንድ፣ቀንና ማታ አድረጎ ፈጥሮልሃል።ቀን፣ጥዋት ስትነሳ ማታ እንደሚመጣ አስብ ወጣት ሳለህ እርጂና እንደሚመጣ አስተውል።ያኔ በሕይወት ዘመንህ ምን ማድረግ እንዳለብህ ወዴት እንደምትሄድ ስለምታውቅ ወጣትነትህ ጥዋትህ ትጠቀማለህ።
ሰናይ ጥዋት ተመኘሁ

@Zsewasw

አክሊል ዘሰዋስው