Get Mystery Box with random crypto!

✿✟ የ҈ ዳ҈ ዊ҈ ት҈ ዜ҈ ማ҈ ✟✿

የቴሌግራም ቻናል አርማ zemaryan — ✿✟ የ҈ ዳ҈ ዊ҈ ት҈ ዜ҈ ማ҈ ✟✿
የቴሌግራም ቻናል አርማ zemaryan — ✿✟ የ҈ ዳ҈ ዊ҈ ት҈ ዜ҈ ማ҈ ✟✿
የሰርጥ አድራሻ: @zemaryan
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 15.48K
የሰርጥ መግለጫ

╭━─━─━─≪✠≫─━─━─━╮╭━─━─━─
ገና እንዘምራለን
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን ወረባቶችን ከነዜማቸው ለማግኘት @Zemaryan
╰━─━─━─≪✠≫─━─━─━╯╰━─━─━─
ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት ጥያቄ> creator ለማግኝት @kidanemiherat_bot
@yita21
@Binyam
https://youtu.be/Fz4JARE6-DI

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-06-10 17:57:33 በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ በል

    

    
በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ በል
ክብርህም በምድር ይነገራል
ዘመን የሚዋጅ አለን ምስጋና
መድኃኔዓለም ስምህ ገናና

.ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉን
╔═★══════════ ══╗
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
╚══ ══════════★═╝
         ʟɪɴᴋ ᴛᴀʙ . sʜᴀʀᴇ
1.4K viewsBezi, edited  14:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 07:39:51 የልጅሽ ቸርነት

የልጅሽ ቸርነት ያንቺ ማማለድ
ድንግል ቃልኪዳንሽ የርሱ ሰው መውደድ
አወጣኝ ከክፉ አዳነኝ ከሞት

ባርኪኝ የአምላክ እናት ይራቅ ጉስቁልናዬ
አፌን በሳቅ ሙይው እንዲታበስ እንባዬ
እኔ ወዳንቺ ልጠጋ ልማልድ ከፊትሽ
አንገትን አያስቀልስም እናቴ ልመናሽ

ሰርጉን እንዳልገባ ልብሴን አሳድፌያለው
በምልጃሽ በማመን ላንቺ አሳስባለው
በሥላሴ ፊት ስምሽ በእውነት ሰልጥኗልና
ይታረቃል እግዚአብሔር ድንግል ባንቺ ልመና

ነግረሽው ነውና ልጅሽ የታገሰኝ
እንደ ኃጢያቴ ብዛት ፈጥኖ ያላጠፋኝ
እውነተኛ መዝገቤ ነሽ ድህነት ያገኘሁብሽ
ወደቤ ነሽ እመቤቴ በሰላም ያረፍኩብሽ

ኃጥአን እንዲጸድቁ ምክንያት አድርጎሻል
ከሞት ወደ ሕይወት አዳም ተሻግሮብሻል
በጌታ ፊት በወረደ በመረረ እንባሽ
የአባቴ ብሩካን ብሎ ይቀበለኝ ልጅሽ

....ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉን
╔═★══════════ ══╗
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
╚══ ══════════★═╝
         ʟɪɴᴋ ᴛᴀʙ . sʜᴀʀᴇ
1.7K viewsBezi, edited  04:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-07 18:44:52 በአንተ ጨለማዬ በራ
ዘማሪ ገብረአምላክ ደሳለኝ


በአንተ ጨለማዬ በራ(2)
ተከፈተልኝ መንገዴ
ዋጋ አለው አንተን መውደዴ
አቀርባለሁኝ መዝሙር አቀርባለሁኝ ሽብሸባ
የክብር ንጉስ ሲመለክ የሰላም ንጉስ ሲገባ (2)

በሞት ጥላ በድቅድቅ ዓለም ኮብልዬ
ድምፁን ሰማሁ ልጄ ሆይ ሲለኝ ጌታዬ
እጁን ሳየው ይላወስ ጀመር አንጀቴ
የህማም ሰው ተስሎ ቀርቷል ከፊቴ

እውነተኛ ሀሰት የሌለው አዋጅ
መስቀሉ ላይ እዩት በደልን ሲዋጅ
ደሙ ነክቶህ ተከፍሎልሀል ተብዬ
ሰላም ገባሁ መድኃኒት ሆኖኝ ጌታዬ

ማምለጫዬ የተረፍኩብህ ከሞት
ማዕረጌ አጌጥኩኝ በአንተ ፍቅር
ፈላጊዬ ያኖረኝ በትከሻው
በጎ እድል ነው ለሰው ልጅ መጨረሻው


....ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉን
╔═★══════════ ══╗
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
╚══ ══════════★═╝
         ʟɪɴᴋ ᴛᴀʙ . sʜᴀʀᴇ
1.8K viewsBezi, edited  15:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 15:00:48 መድኃኔአለም

መድኃኔዓለም የለም የሚሳነው
አማኑኤል የለም የሚሳነው
እርሱ ቃል ሲናገር ተራራው ሜዳ ነው
መድኃኔዓለም የለም የሚሳነው

አላስብም ነበር አልፈዋለሁ ብዬ
ጉንጭ አልፎ ትራሴን እያጠበ እንባዬን
እየተፈጸመ ኃይሉ በድካሜ
ማእበሉን አለፍኩኝ ቀለለልኝ ሸክሜ
#አዝ
የቤቴ እራስ ነው የእቅዴ መሪ
በክፉም በደጉም ነፍሴን አስተማሪ
ፈጥሮ የማይረሳኝ ቤዛዬ ደረሰ
ቤቴን ደስታ ሞላው እንባዬ ታበሰ
#አዝ
ትናንት ባዶ ነበር የለኝ የሚሰፈር
አንዳች አልነበረኝ የሚታይ የሚቆጠር
ከርሱ የተነሳ ዛሬ ግን ሙሉ ነኝ
ክብር ለእርሱ ይሁን አለ የማይተወኝ
#አዝ
እየከለከለ ለእኔ ማይጠቅመኝን
በጊዜ እየሰጠ ደግሞ የሚረባኝን
ሁሉ በእርሱ ሆኗል አልሆነም ያለ እርሱ
ውዳሴ ምስጋና ይድረስ ለንጉሱ

....ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉን
╔═★══════════ ══╗
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
╚══ ══════════★═╝
         ʟɪɴᴋ ᴛᴀʙ . sʜᴀʀᴇ
2.0K viewsBezi, edited  12:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 09:59:13 ጾመ ሐዋርያት

በወርኃ ሰኔ የሚጾም በመሆኑ ይህ ጾም በተለምዶ የሰኔ ጾም በመባል ይታወቃል፡፡ ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ለስብከተ ወንጌል ከመሰማራታቸው በፊት የጾሙት ጾም ነው፡፡ ጾመ ሐዋርያትን ለመጀመሪያ ጊዜ የጾሙት ቅዱሳን ሐዋርያት ሲሆኑ የጾሙበትም ዋና ምክንያት በሃምሳኛው ቀን ሀብተ መንፈስ ቅዱስ ስለተቀበሉና እግዚአብሔር ስላደረገላቸው መልካም ነገር ለማዘከር ነው፡፡

ጾመ ሐዋርያት በዓለ ጰራቅሊጦስ በመጀመሪያው ሰኞ ይውላል፡፡ ጌታችን አምላካችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው ደቀ መዛሙርቱን ይህን ጾም እንደሚጾሙት እንዲህ ተናግሮ ነበር፡፡ ‹‹በዚያን ጊዜ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው። ‹‹እኛና ፈሪሳውያን፥ ብዙ እንጾማለን፥ ደቀ መዛሙርትህስ ለምን አይጾሙም? አሉት፡፡›› (ማቴ.፱፥፲፬)  ደቀ መዛሙርቱ ይህንን በጠየቁት ጊዜ ጌታችን እንዲህ ብሎ መልሶላቸው ነበር፡፡ ‹‹ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ የሙሽራው ሚዜዎች ሙሽራው  ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ አይችሉም፤ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፤ ያንጊዜም ይጾማሉ፡፡›› (ማቴ.፱፥፲፭)
 
በቅዱሳን ሐዋርያት ላይ ያደረው ጸጋ መንፈስ ቅዱስና ሀብተ መንፈስ ቅዱስ በእኛም ላይ እንዲያድር፣ ከቅዱሳን ሐዋርያቱ በረከት እንድንሳተፍ፣ አገልግሎታችን በስኬት እንዲቃና እና ወርኃ ክረምቱ በሰላም ያልፍልን ዘንድ ጾመ ሐዋርያትን መጾም አስፈላጊ ነው፡፡ ከጸሎትና ምጽዋትን መንፈሳዊ እድገትን በጾም አስምረን ከራሳችንን እና ከእግዚአብሔር አምላካችን ጋር የምንታረቅበት እንዲሆንልን የቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያት በረከትና ጸሎትም አይለየን፡፡
 
የአምላካችን እግዚአብሔር ቸርነት፣ የቅድስት ድንግል ማርያም እና የቅዱሳን ሐዋርያት  አማላጅነትና ተራዳኢነት አይለየን፤ አሜን!
 

.....ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉን
╔═★══════════ ══╗
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
╚══ ══════════★═╝
         ʟɪɴᴋ ᴛᴀʙ . sʜᴀʀᴇ
2.1K views፲፱፰፯ყเƭαყαℓ የ҈ ተ҈ ዋ҈ ህ҈ ዶ҈ ል⃝ጅ Cinematographer }, edited  06:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-04 15:01:58


ጰራቅሊጦስ፦ ማለት መንጽሒ (የሚያነጻ)፣ መጽንዒ (የሚያጸና)፣ መስተፈሥሒ (ደስታን የሚሰጥ)፣ መስተሥርይ (ኃጢአትን ይቅር የሚል)፣ ናዛዚ (የሚያረጋጋ)፣ ከሣቲ (ምሥጢርን የሚገልጥ) የሚል ትርጉምን ይሰጣል መጻሕፍተ ሠለስቱ ሐዲሳት።


"ዐቢየ ተስፋ ዘአስፈዎሙ ይቤሎሙ ኢየሱስ ለአርዳኢሁ እስእሎ ለአቡየ ይፈኑ ለክሙ መንፈሰ ጽድቅ ጰራቅሊጦስ።"

ትርጉም፡-
ታላቅ ተስፋ ያደረገላቸው ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርቱን አባቴን እለምነዋለሁ እውነት መንፈስን ይልክላችኋል።
ሊቁ ቅዱስ ያሬድ።

"ወበ፶ ዕለት ፈነወ ሎሙ መንፈሰ ቅዱሰ ከመ ዘእሳት ወተናገሩ በነገረ ኵሉ በሐዉርት።"

ትርጉም፦
በሃምሳውም ቀን በእሳት አምሳል መንፈስ ቅዱስን ሰደደላቸው በአገሩ ሁሉ ቋንቋ ተናገሩ።

የቅዳሴ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ።

.....ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉን
╔═★══════════ ══╗
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
╚══ ══════════★═╝
         ʟɪɴᴋ ᴛᴀʙ . sʜᴀʀᴇ
2.2K views፲፱፰፯ყเƭαყαℓ የ҈ ተ҈ ዋ҈ ህ҈ ዶ҈ ል⃝ጅ Cinematographer }, edited  12:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-01 13:00:42 ተክለሃይማኖት ጸሐይ

ተክለሃይማኖት ጸሐይ የአምላክ አገልጋይ (፪)
ጸሐይ የአምላክ አገልጋይ(፪)

/አዝማች/

የኢትዮጲያን ምድር /የባረካት//፪/
አስተማሪዋ /የሆንክላት//፪/
ይህንን አውቃ /ትዘምራለች//፪/
ተክለሃይማኖት /ትጠራሃለች//፪/

/አዝማች/

አልጫው ጣፍጧል /በጸሎትህ//፪/
ብርሃን በርቷል /ለልጆችህ//፪/
በቃልኪዳንህ ፍጥረት /ጸደቀ//፪/
ተአምራትህም /በዓለም ታወቀ//፪/

/አዝማች/

ምስክርኽን /አምላክ ያከብራል//፪/
የነኩህንም እርሱ /ይጣላል//፪/
ፍርፋሪህን /ልቤ ናፈቀች//፪/
የአንተን በረከት /ስለወደደች//፪/

/አዝማች/

በእግዚአርያ በጸጋዘአብ ተማጽኛለሁ
ልቤን ለእጅህ /ሰጥቼኻለሁ//፪/
ከአንተ ጋር ልኑር /ለዘላለም//፪/
የሚለያየን /ማንም የለም//፪/።
✞┈┈┈┈┈•◦◈◎✥◎◈◦•┈┈┈┈┈✞

እንካን ለፃድቁ ለአባታችን ለተክለ ሐይማኖት ወርሀዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
------------
40 እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል።

41 ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል።
.....ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉን
╔═★══════════ ══╗
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
╚══ ══════════★═╝
         ʟɪɴᴋ ᴛᴀʙ . sʜᴀʀᴇ
2.8K viewsBezi, edited  10:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-01 08:15:49 በዘባነ ኪሩብ

.....ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉን
╔═★══════════ ══╗
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
╚══ ══════════★═╝
         ʟɪɴᴋ ᴛᴀʙ . sʜᴀʀᴇ
2.1K viewsBezi, edited  05:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-31 14:38:24 የመስቀሉ ፍቅር

የመስቀሉ ፍቅር ሲገባን (4)
እመቤታችንን እንወዳታለን
የመስቀሉ ፍቅር የገባቸው (4)
እመቤታችን አለች ከጎናቸው

አባ ሕርያቆስ አባታችን
የመስቀሉ ነገር ቢገባው
ልቤ አፈለቀ አለ መልካም ነገር
ከእመቤቴ ጋራ ሲነጋገር
ከድንግል ማርያም ጋር ሲነጋገር

ነይ ነይ እምዬ ማርያም
ነይ ነይ ቤዛዊት አለም
አንድ ወልዳ ስሙን አበዛችው (2)
አንዱ ሃገር ስትሄድ መድሃኒአለም አለችው
አንድ ወልዳ ስሙን አበዛችው (2)
አንዱ ሃገር ስትሄድ ኢየሱስ አለችው
አንድ ወልዳ ስሙን አበዛችው (2)
አንዱ ሃገር ስትሄድ ክርስቶስ አለችው
አንድ ወልዳ ስሙን አበዛችው (2)

ለመናኒው ፀሎት ልዩ እጣን
የዋሻው ሻማ ነሽ እመብሃን
መአዛሽ ሸተተኝ ከግሸን
ትናፍቂኛለሽ ምን ልሁን
ትርቢኝማለሽ ምን ልሁን

ዳዊት በመዝሙሩ ያነሳሻል
የያዕቆብ ድንኳን ነሽ ይልሻል
የእግዚአብሔር ሃገር የሚሉሽ
እመቤቴ ማርያም አንቺ ነሽ (2)

ቤተልሔም ስሄድ አይሻለሁ
ቀራኒዮ ስሄድ አይሻለሁ
ፍጹም አትለይም ከልጅሽ
የአንቺስ ልዩ ነው ፍቅርሽ (2)

.....ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉን
╔═★══════════ ══╗
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
╚══ ══════════★═╝
         ʟɪɴᴋ ᴛᴀʙ . sʜᴀʀᴇ
2.3K viewsBezi, edited  11:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-30 14:15:42 "ዑራኤል" ዘማሪት ሲስተር ሕይወት ተፈሪ

.....ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉን
╔═★══════════ ══╗
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
╚══ ══════════★═╝
         ʟɪɴᴋ ᴛᴀʙ . sʜᴀʀᴇ
2.2K viewsBezi, edited  11:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ