Get Mystery Box with random crypto!

የልጅሽ ቸርነት የልጅሽ ቸርነት ያንቺ ማማለድ ድንግል ቃልኪዳንሽ የርሱ ሰው መውደድ አወጣኝ ከክ | ✿✟ የ҈ ዳ҈ ዊ҈ ት҈ ዜ҈ ማ҈ ✟✿

የልጅሽ ቸርነት

የልጅሽ ቸርነት ያንቺ ማማለድ
ድንግል ቃልኪዳንሽ የርሱ ሰው መውደድ
አወጣኝ ከክፉ አዳነኝ ከሞት

ባርኪኝ የአምላክ እናት ይራቅ ጉስቁልናዬ
አፌን በሳቅ ሙይው እንዲታበስ እንባዬ
እኔ ወዳንቺ ልጠጋ ልማልድ ከፊትሽ
አንገትን አያስቀልስም እናቴ ልመናሽ

ሰርጉን እንዳልገባ ልብሴን አሳድፌያለው
በምልጃሽ በማመን ላንቺ አሳስባለው
በሥላሴ ፊት ስምሽ በእውነት ሰልጥኗልና
ይታረቃል እግዚአብሔር ድንግል ባንቺ ልመና

ነግረሽው ነውና ልጅሽ የታገሰኝ
እንደ ኃጢያቴ ብዛት ፈጥኖ ያላጠፋኝ
እውነተኛ መዝገቤ ነሽ ድህነት ያገኘሁብሽ
ወደቤ ነሽ እመቤቴ በሰላም ያረፍኩብሽ

ኃጥአን እንዲጸድቁ ምክንያት አድርጎሻል
ከሞት ወደ ሕይወት አዳም ተሻግሮብሻል
በጌታ ፊት በወረደ በመረረ እንባሽ
የአባቴ ብሩካን ብሎ ይቀበለኝ ልጅሽ

....ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉን
╔═★══════════ ══╗
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
╚══ ══════════★═╝
         ʟɪɴᴋ ᴛᴀʙ . sʜᴀʀᴇ