Get Mystery Box with random crypto!

መድኃኔአለም መድኃኔዓለም የለም የሚሳነው አማኑኤል የለም የሚሳነው እርሱ ቃል ሲናገር ተራራው | ✿✟ የ҈ ዳ҈ ዊ҈ ት҈ ዜ҈ ማ҈ ✟✿

መድኃኔአለም

መድኃኔዓለም የለም የሚሳነው
አማኑኤል የለም የሚሳነው
እርሱ ቃል ሲናገር ተራራው ሜዳ ነው
መድኃኔዓለም የለም የሚሳነው

አላስብም ነበር አልፈዋለሁ ብዬ
ጉንጭ አልፎ ትራሴን እያጠበ እንባዬን
እየተፈጸመ ኃይሉ በድካሜ
ማእበሉን አለፍኩኝ ቀለለልኝ ሸክሜ
#አዝ
የቤቴ እራስ ነው የእቅዴ መሪ
በክፉም በደጉም ነፍሴን አስተማሪ
ፈጥሮ የማይረሳኝ ቤዛዬ ደረሰ
ቤቴን ደስታ ሞላው እንባዬ ታበሰ
#አዝ
ትናንት ባዶ ነበር የለኝ የሚሰፈር
አንዳች አልነበረኝ የሚታይ የሚቆጠር
ከርሱ የተነሳ ዛሬ ግን ሙሉ ነኝ
ክብር ለእርሱ ይሁን አለ የማይተወኝ
#አዝ
እየከለከለ ለእኔ ማይጠቅመኝን
በጊዜ እየሰጠ ደግሞ የሚረባኝን
ሁሉ በእርሱ ሆኗል አልሆነም ያለ እርሱ
ውዳሴ ምስጋና ይድረስ ለንጉሱ

....ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉን
╔═★══════════ ══╗
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
╚══ ══════════★═╝
         ʟɪɴᴋ ᴛᴀʙ . sʜᴀʀᴇ