Get Mystery Box with random crypto!

ይሄ ነው ሐበሻ!

የቴሌግራም ቻናል አርማ yihenewhabesha — ይሄ ነው ሐበሻ!
የቴሌግራም ቻናል አርማ yihenewhabesha — ይሄ ነው ሐበሻ!
የሰርጥ አድራሻ: @yihenewhabesha
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 193
የሰርጥ መግለጫ

@ይሄ ነው ሐበሻ!

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-20 10:13:27 በዚምባብዌ በአንድ ወቅት በተፈፀመ የባንክ ዘረፋ ጭምብል አጥልቀው የመጡ የዘራፊዎቹ መሪ "እንዳትንቀሳቀሱ #ገንዘቡ_የሀገሪቱ ነው #ነፍሳችሁ ደግሞ #የግላችሁ ነች" በማለት አስጠነቀቀ..!!!

በባንኩ የሚገኝ ሁሉም ሰው መሬት ላይ ተደፋ። ይህ "#Mind_Changing_concept" ይባላል። የሰዎችን አእምሮ የሚያስብቡበትን መንገድ ማስለወጥ ነው።

አንዲት ለግላጋ ሴት ጠረጴዛው ላይ ስትንጋለል አንደኛው ዘራፊ "እባክሽ እንደ #ሰለጠነ ሰው ሁኚ። ለዘረፋ እንጂ ሴት ለመድፈር አልመጣንም!" ብሎ ጮኸባት።

ይህ ደግሞ "#Being_Professional" ተብሎ ይጠራል። የሰለጠንክበትን አጀንዳ ብቻ ማስፈፀም። ከዛ ውጭ ልታተኩርበት የሚገባ ነገር ካለ #ዓላማህን መሳት ነው።

የዘራፊዎቹ ቡድን ወደ ቤታቸው ከተመለሱ ቡኃላ በዕድሜ አነስ የሚለው ማስትሬት ዲግሪ ያለው ብልህ ብላቴና በዕድሜ ትልቁን ዘራፊ (6ኛ ክፍል ብቻ ያጠናቀቀውን ጎልማሳ) "ታላቅ ወንድሜ ያገኘነውን ገንዘብ እንቁጠረው።" አለው።

ትልቁ ሌባ "ሞኝ ነህ እንዴ? የዘረፍነው ገንዘብ እኮ እጅግ ብዙ ነው ይሄን ሁሉ ስንቆጥር ቀናትም አይበቃንም። ማታ በTV የዘሩፍነው ገንዘብ መጠን በዜና ይገለፅ የለ እንዴ?" አለው

ይህ "#Experience" የምንለው ነው። ዛሬ ዛሬ ከወረቀት ማስረጃ ይልቅ #ልምድ ቦታ የሚሰጥበት አጋጣሚዎች አሉ።

ዘራፊዎቹ ከባንኩ እንደወጡ የባንከ ማናጀር ለሱፐርቫይዘሩ "በል በቶሎ ለፖሊስ ደውልና ዘረፋውን በአስቸኳይ አሳውቅ።" አለው። ሱፐርቫይዘሩ ግን "ቆይ ከካዝናው ውስጥ 10 ሚሊዮን ብር ለራሳችን እናውጣና ሌቦቹ ከወሰዱት 70 ሚሊዮን ብር ላይ ጨምረን ሪፖርት ብናደርግ ይሻላል።" አለ።

ይህ ደግሞ "#Swim_with_the_tide" ይባላል። የማይመቹ አጋጣሚዎችን ለራስህ #አድቫንቴጅ በመውሰድ ራስህን መጥቀም ነው።

ሱፐርቫይዘሩ በአጋጣሚው ያገኙትን ሀብት ሲመለከት "ኧረ እንደውም በየወሩ ባንክ ቢዘረፍ አሪፍ ነው።" አለ

ይህ ደግሞ "#Killing_Bordem" ይባላል። ባልተጠበቁ አጋጣሚዎች ከአቅምህ በላይ የሆኑ ነገሮች ሲከሰቱ ከሙያህና ከስራህ ይልቅ #ለግል_ደስታህ ቅድሚያ መስጠት ነው።

በቀጣዩ ቀን በሀገሪቱ ብሔራዊ የTV ጣብያ ዜና ላይ ከባንኩ 100 ሚሊዮን መዘረፉ ተነገረ። ዘራፊዎቹ በተደጋጋሚ ቢቆጥሩ ቢቆጥሩ 20 ሚሊዮን ብር ብቻ ሆነ የዘረፉት። በጣም ተናደዱ እጅግ ተበሳጩ። "እኛ ሕይወታችንን ነፍሳችንን አደጋ ላይ ጥለን የዘረፍነው 20 ሚሊዮን ብር ብቻ ነው። የባንክ ማናጀሩ ግን 80 ሚሊዮን ብር በኛ ስም በነፃነት በእጆቹ ወሰደ። ሌባ ከመሆንማ መማር የተማረ መሆን ይሻላል" አሉ።

ይህ ደግሞ "Knowledge is worth as much as Gold" #እውቀት እንደ ወርቅ ውድ መሆኑን የምታውቅበት ነጥብ ነው።

በመጨረሻ የባንክ ማናጀሩ እና ሱፐርቫይዘሩ #ደስተኞች እና #ሳቂታዎች ነበሩ።



ከላይ ካሉት ከ6 ነጥቦች የትኛው ይበልጥ #አስፈላጊ ነው?

bini_girmachew
@ይሄ ነው ሐበሻ!
https://t.me/yihenewhabesha
16 viewsNebiይ, 07:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 11:12:51 #​​ቡሄ_በሉ

ቡሄ በሉ (፪) - - ሆ ልጆች ሁሉ - - ሆ
የኛማ ጌታ - - ሆ የዓለም ፈጣሪ - - ሆ
የሰላም አምላክ - -ሆ ትሁት መሀሪ -ሆ
በደብረ ታቦር - - ሆ የተገለጠው - ሆ
ፊቱ እንደ ፀሐይ - ሆ በርቶ የታየው -ሆ
ልብሱ እንደብርሃን -ሆ ያንፀባረቀው -ሆ

ድምጽህን ሰማና በብህሩ ደመና(፪)
የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን(፪)

ያዕቆብ ዮሐንስ-ሆ እንዲሁም ጴጥሮስ-ሆ
አምላክን አዩት - - ሆ ሙሴ ኤልያስ - ሆ
አባቱም አለ - - ሆ ልጄን ስሙት - - ሆ
ቃሌ ነውና - - ሆ የወለድኩት - - ሆ
አዝ======
ታቦር አርሞንኤም-ሆ ብርሃን ታየባቸው ሆ
ከቅዱስ ተራራ ሆ ስምህ ደስ አላቸው- ሆ
ሰላም ሰላም - - ሆ የታቦር ተራራ - - ሆ
ብርሀነ መለኮት - ሆ ባንቺ ላይ አበራ -ሆ
አዝ======
በተዋህዶ - - ሆ ወልድ የከበረው - ሆ
የእግዚአብሔር አብ ልጅ - - ሆ ወልደማርያም ነው - -ሆ
ቡሄ በሉ - - ሆ ቡሄ በሉ - - ሆ
የአዳም ልጆች - - ሆ ብርሃንን - - ሆ ተቀበሉ - -ሆ
አዝ======
አባቴ ቤት - - ሆ አለኝ ለከት - - ሆ
እናቴ ቤት - - ሆ አለኝ ለከት - - ሆ
ከአጎቴም ቤት - - - ሆ አለኝ ለከት - ሆ
ተከምሯል - - ሆ እንደ ኩበት - - ሆ
አዝ======
የዓመት ልምዳችን - - ሆ ከጥንት የመጣው - - ሆ
ከተከመረው - ሆ ከመሶቡ ይውጣ - ሆ
ከደብረ ታቦር - - ሆ ጌታ ሰለመጣ - ሆ
የተጋገረው - ሆ ሙልሙሉ ይምጣ - ሆ
አዝ======
ኢትዮጵያውያን - -ሆ ታሪክ ያላችሁ - ሆ
ባህላችሁን - ሆ ያዙ አጥብቃችሁ - ሆ
ችቦውን አብሩት -ሆ እንዳባቶቻችሁ -ሆ
ምስጢር ስላለው -ሆ ደስ ይበላችሁ -ሆ
አዝ======
አባቶቻችን - - ሆ ያወረሱን - - ሆ
የቡሄን ትርጉም - - ሆ ያሳወቁን - - ሆ
እንድንጠብቀው - ሆ ለእኛ የሰጡን - ሆ
ይህን ነውና - - ሆ ያስረከቡን - - ሆ
አዝ======
ለድንግል ማርያም ሆ አሥራት የሆንሽ ሆ
ቅዱሳን ጻድቃን - - ሆ የሞሉብሽ - - ሆ
በረከታቸው - - ሆ ያደረብሽ - - ሆ
ሁሌም እንግዶች - ሆ የሚያርፉብሽ -ሆ
ሀገረ እግዚአብሔር -ሆ ኢትዮጵያ ነሽ ሆ
አዝ======
ለሐዋርያት - - ሆ የላከ መንፈስ - - ሆ
ዛሬም ለኢትዮጵያ -ሆ ጸጋውን ያፍስስ ሆ
በበጎ ምግባር - ሆ እንድንታነጽ - - ሆ
በቅን ልቦና - ሆ በጥሩ መንፈስ - - ሆ
በረከተ ቡሄ - ሆ ለሁላችን ይድረስ - ሆ
= = = = = =
ዓመት ዓውዳመት ድገም እና ዓመት ድገም እና
በጋሽዬ ቤ ድገም እና ዓመት ድገም እና
ያውርድ በረከት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ወርቅ ይፍሰስበት ድገም እና ዓመት ድገም እና
በእማምዬ ቤት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ይግባ በረከት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ማርና ወተት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ይትረፍረፍ በእውነት ድገም እና ዓመት ድገም እና
= = = = = =

እንዲሁ እንዳላችሁ - -በፍቅር አይለያችሁ - - በፍቅር
ላመቱ በሰላም - - በፍቅር ያድርሳችሁ - - በፍቅር
ክርስቶስ በቀኙ - - በፍቅር ያቁማችሁ - - በፍቅር
የመንግስቱ ወራሽ - - በፍቅር ያድርጋችሁ - - በፍቅር
እንዲሁ እንዳለን - - በፍቅር አይለየን - - በፍቅር
ለዓመቱ በሰላም - - በፍቅር ያድርሰን - - በፍቅር
አማኑኤል በቀኙ - - በፍቅር ያቁመን - - በፍቅር
የመንግስቱ ወራሽ - - በፍቅር ያድርገን - - በፍቅር
= = = = = =

የቅዱሳን መላክት የፃድቃን ሰማዕታት
ረድኤት በረከት ይግባ በሁሉም ቤት
በሁሉም ቤት(፪) ይግባ በረከት(፪)
እንቁም በሃይማኖት ፀንተን በትጋት
የአስራት አገር የአበው ቀደምት
የቅዱሳን አባቶች ትውፊት
ይገባልና ልንጠብቅ በእውነት
ባህላችንን የአባቶች ትውፊት (፫)

መዝሙር በማኅበረ ፊልጶስ

ታቦርና አርሞንኤም #በስምህ ደስ ይላቸዋል
መዝ፹፰፥፲፪
@ይሄ ነው ሐበሻ!
https://t.me/yihenewhabesha
36 viewsNebiይ, 08:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 15:37:14 #ብንስማማስ ???!!!

እንዲህ የሚል ከጥንት ጀምሮ የሚታወቅ የአይሁዳውያን ተረት አለ፡-

አንዲት በጣም የተራበች ድመት ከአንድ ሱቅ ስጋ ሰረቀች፡፡ ያንን ሌብነቷን የተመለከተ አንድ ውሻ ነበረና እኩል ካላካፈልሽኝ አጋልጥሻለሁ አላት፡፡ ድመቷ መካፈል ስላልፈለገች መጣላት ጀመሩ፡፡ ሁለቱ በነበራቸው ጸብ ማንም ማሸነፍ ስላልቻለና ጸቡ ማቆሚያ ስላጣ የስጋው ሽታ ስቧት የመጣች በአካባቢው የነበረችን አንዲት ቀበሮ ጠሩና እንድትዳናኛቸው ጠየቋት፡፡

ቀበሮዋ፣ “ከምትጣሉ ስጋውን እኩል ተካፈሉ” የሚልን ቀላል ምክር ለገሰቻቸው፡፡ በምክሩ ሁለቱም በመስማማታቸው ድመት ስጋውን ለሁለት ቆርጣ ለውሻ አካፈለች፡፡ ሆኖም ውሻው፣ የተሰጠው ድርሻ አናሳ እንደሆነ በማሰብ ጸቡን አላበርድ አለ፡፡ በዚያን ጊዜ ቀበሮ የስጋውን መጠን በማስተካከል ሰበብ ከድመት ድርሻ ላይ ደህና አድርጎ በመቦጨቅ ዋጥ በማድረግ ውሻን አስደሰተና ለማስተካከል ሞከረ፡፡

አሁን ደግሞ ድመት የእሷ በመቀነሱ ምክንያት፣ “የውሻ ድርሻ በዝቷል” በማለት ጸቡን አላበርድ አለች፡፡ አሁንም ቀበሮ ድመትን ለማስደሰት በሚል ሰበብ ከውሻው ድርሻ ላይ ጠቀም ያለ መጠን ቦጨቅ በማድረግ ዋጥ አደረገ፡፡ አሁን ደግሞ ውሻ እንደገና የእሱ ማነሱን ሲያይ የድመት በዝቷል፣ ከዚያም ቀበሮ ድርጊቱን ሲደጋግም ድመት ደግሞ የውሻ በዝቷል ሲባባሉ፣ ቀበሮ ከዚህም ከዚያም ሲቀናንስ ስጋውን ጨረሰውና ድመትና ውሻ ምንም ሳይደርሳቸው ባዶ ቀሩ ይባላል፡፡

ተጣልተን ሁሉን ከምናጣ #ተስማምተን ግማሽ ማግኘቱና አብሮ መኖሩ አይሻለንም?
@ይሄ ነው ሐበሻ!
https://t.me/yihenewhabesha
37 viewsNebiይ, 12:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 18:23:36 #What_killed_the_frog?

Put a #frog into a vessel filled with water and start heating the water. As the temperature of the water begins to #rise, the #frog adjusts its body temperature accordingly. The #frog keeps adjusting its body temperature with the increasing temperature of the water. Just when the water is about to reach #boiling point, the #frog can not adjust any more. At this point, the #frog decides to jump out. The #frog tries to jump but it is unable to do so because it has lost all its #strength in adjusting to the #rising water temperature. Very soon the #frog dies.

#What_killed#the_frog?


Think about it! I know many of us will say the #boiling water. But the truth about what killed the #frog was its own inability to #decide when to #jump out.

We all need to #adjust to people and situations, but we need to be sure when we need to #adjust and when we need to move on.

There are #times when we need to face the situation and take #appropriate_actions. If we allow people to exploit us physically, emotionally, financially, spiritually, or mentally they will continue to do so.

Let us decide when to #jump!

Lets #jump while we still have #strength.


#What_killed_the_frog?
@ይሄ ነው ሐበሻ!
https://t.me/yihenewhabesha
56 viewsNebiይ, 15:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 09:14:48 Are you making your contribution to making the world a #better_place?

One thing that the world needs the most, and everyone has it is #love. If each one of us spread even a little #love and positivity, we would turn the world into a beautiful place for every being.

Most people are either filled with envy, resentment or enmity or suffering from depression, sadness and loneliness. Spreading #love can help both. #Love can pacify anger and even lift up someone from their lows. #Love can create joy and bring people together. #Love can heal and make one feel at ease.

Always spread #love. Talk good about others, respect everyone's opinion, and be empathetic and inclusive. Encourage people, so it creates a strong connection between them. It is the strong connection that can keep us all together.
@ይሄ ነው ሐበሻ!
https://t.me/yihenewhabesha
56 viewsNebiይ, 06:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 20:34:03 + #የአንድ_ሰው_ውሎና_አመሻሽ +

ይህ እስካሁን ምንጩን ያላገኘሁት አንድ ወንድሜ የላከልኝ በፈረንጅ አፍ የተጻፈ የቆየ የአንድ ሰው ገጠመኝ ነው :-

አንድ ወንድም #ስልኩን ድምፅ አልባ ማድረግ ረስቶ ወደ #ቤተ_ክርስቲያን ገብቶ ስብከት ይማራል:: በዚህ መካከል ስልኩ ይጮኃል::

ሰባኪው ስብከቱን አቁሞ በዓይኖቹ ተቆጣው:: ከስብከቱ በኋላ ምእመናን ስብከቱን በመረበሹ #ወቀሱት:: አንዳንዶቹም እያዩት ራሳቸውን በትዝብት ነቀነቁ:: ከሚስቱ ጋር ወደ ቤታቸው ሲሔዱም ሚስቱ ስለ #ቸልተኝነቱ ምክር መሥጠትዋን ቀጠለች::
እፍረት መሸማቀቅና ውርደት ዘልቆ እንደተሰማው በፊቱ ላይ ይታይ ነበር:: ከዚያች ሰንበት በኋላ እግሩን ወደ ቤተ ክርስቲያን አንሥቶ አያውቅም::

ውስጡ የተረበሸው ይህ ሰው ያንኑ ምሽት ወደ #መጠጥ_ቤት አመራ:: አእምሮው እንደታወከ ነበር::

ቁጭ ባለበት ድንገት የሚጠጣበት #ጠርሙስ ወድቆ ተሰበረና መጠጡም በዙሪያ ተረጨ:: ፍንጣሪው የነካቸው ሰዎች ወደ እሱ መጠጋት ጀመሩ:: ሊጮኹበትና በጥፊ ሊሉት እንደሆነ ታውቆት ቀድሞ #ዓይኖቹን_ጨፈነ::

ሰዎቹ ግን በተሰበረው ጠርሙስ ስብርባሪ #ተጎድቶ_እንደሆነ_ተጨንቀው ጠየቁት::

#አስተናጋጁ መጥቶ የፈሰሰበትን እንዲያደርቅ ማበሻ ሰጠው:: #የጽዳት ሠራተኛዋ መሬቱን ወለወለች::

የቤቱ ባለቤት " #አይዞህ_ያጋጥማል? ዕቃ የማይሰብር ማን አለና?" አለችውና ሌላ መጠጥ አስመጣችለት::
ከዚያች ቀን ጀምሮ ከዚያ መጠጥ ቤት #ቀርቶ_አያውቅም::

#በቤተ_ክርስቲያን ውስጥ ስልክን ክፍት ማድረግና ሥርዓተ አምልኮ መረበሽ መቅደስ ውስጥ ጫማ አድርጎ የመግባት ያህል ስኅተት ነው:: እንኩዋን ቤተ ክርስቲያን #ኤምባሲ እንኩዋን ስልክህን ውጪ አስቀምጠህ ትገባለህ:: ሰውዬው ላጠፋው ጥፋት ግን #በፍቅር የሚያናግረው ሰው በማጣቱ ከነ ስልኩ ሊጠፋ ወሰነ::

ቤተ ክርስቲያን #የድኅነት ሥፍራ ናት:: መጠጥ ቤት ደግሞ የጥፋት ጎዳና ነው:: በዚህ ሰው ታሪክ ውስጥ ግን #በድኅነት ሥፍራ ካሉ ሰዎች ይልቅ #በጥፋት ሥፍራ ያሉ ሰዎች ለሰውዬው ስኅተት የተሻለ #ፍቅር አሳዩ:: አንዳንዴ የአንዳንድ ምእመናን #ጠባይ ነፍሳትን ወደ ሲኦል ይሰድዳል::

አንዳችን የአንዳችን ጠባቂ መሆን እንችላለን ዓለምን ለመፈወስ የሚቻለንን እናድርግ:: ነፍሳትን #ከማዳን ነፍሳትን #ማጥፋት በጣም ቀላል ነው::

መድኃኔዓለም ክርስቶስ የኃጢአተኞች #ወዳጅ ነበረ:: እሱ የማንንም ቅስም በክፉ ቃል አልሰበረም:: እኛ ግን ሰው ላይ ስንጨክን መጠን የለንም:: በዚህ ምክንያት እንደ ኒቼ ያሉ ሰዎች "ብቸኛው #ክርስቲያን መስቀል ላይ #የሞተው ነው" ብለው እስኪዘብቱብን ደርሰዋል::

#መጽሐፍ ግን ሰው ሲሳሳት ስናይ ምን ማድረግ እንዳለብን እንዲህ ሲል ይናገራል :-

"ወንድሞች ሆይ፥ ሰው በማናቸውም #በደል ስንኳ ቢገኝ፥ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ እንደዚህ ያለውን ሰው በየውሃት መንፈስ #አቅኑት" ገላ. 6:1

በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
@ይሄ ነው ሐበሻ!
https://t.me/yihenewhabesha
63 viewsNebiይ, 17:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 09:12:16 #ልብህ_ውስጥ_ምን_አለ ?

አንድ ገበሬ፣ በረት ውስጥ ባለ የሳር ክምር ውስጥ የእጅ ሰዓቱ ጠፋበት። ሰዓቱ ለእሱ ተራ አልነበረም፤ የሚወደው አያቱም ማስታወሻም ነበር።
ክምሩ ውስጥም ላይ ታች ፈለገ፤ በኋላም ተስፋ ቆረጠ፡፡ ውጪ ላይ ሲጫወቱ የነበሩ ህጻናትን እንዲረዱት ጠራቸው።
ከእነሱም መሃል ሰዓቱን ላገኘ ሽልማት እንደሚሰጥ ቃል ገባ።
ልጆቹም ይህንን ሲሰሙ እየተሯሯጡ ወደ በረቱ ውስጥ ገቡ። ክምሩንም እየበታተኑ ፈለጉ። ሆኖም ሰዓቱን ሊያገኙት አልቻሉም። ገበሬው ተስፋ ቆርጦ ልጆቹን ይዟቸው ወደ ውጪ ወጣ፤ ከልጆቹ መሃል ያለ አንድ ብላቴና ሌላ እድል እንዲሰጠው ጠየቀ።
ገበሬውም ብላቴናውን ወደታች እየተመለከተው፤ በቅሬታ ፈገግታ “አይ ምን ጥቅም አለው ብለህ ነው፤ የሚገኝም አይመስለኝም” አለና ጉንጩን ቆንጠጥ አድርጎ የእጅ ሰዓቱን እንዲፈልግ ፈቀደለት።
ብላቴናው ወደ በረቱ ገባ፤ ከበረቱ ተመልሶ ሲወጣም በእጁ ሰዓት ይዞ ነበር!
ገበሬው ተደሰተም ተገረመም። ብላቴናውንም፤ “እኛ ፈልገን ያጣነውን አንተ ብቻህን እንዴት አገኘኸው?” ብሎ ጠየቀው።
ህጻኑም መለሰ፣ “ምንም አላደረኩም፤ በጸጥታ መሬት ላይ ተቀምጬ መስማት ጀመርኩኝ። ሰዓቱም ቲክ ቲክ… ሲል ሰማሁት። በድምጹም ተመርቼ አገኘሁት”
****
አንተ እና እኔ ስንሯሯጥ እንውላለን፤ በጸጥታ እና በስክነት ውስጥ ከማሰብም ይልቅ፤ ምስቅልቅል ያለ እና ማሰርያ አልባ ቀንን እናሳልፋለን።
በጩኸት እና በግርግር ውስጥስ ማን ራሱን ያዳምጣል?
ሰላም ያለው፣ ጸጥ ያለ እና የተረጋጋ አእምሮ፤ ምስቅልቅል ውስጥ ከገባ እና ጥድፊያ ውስጥ ካለ አእምሮ በተሻለ ያስባል። ለደቂቃዎች #አእምሮህን ጸጥ አሰኘው፤ #የልብህንም ድምጽ … አድምጥ… ድው… ድው …

#ልብህ ውስጥ ምን አለ?

#ልብህ ምን ይፈልጋል?

@ይሄ ነው ሐበሻ!
https://t.me/yihenewhabesha
48 viewsNebiይ, 06:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 16:33:58 #እናመስግን! #ይመስገን #ተመስገን!

ያለ አንዳች ምክንያት በቃ ዝም ብሎ የሚወድህ፣ ምክንያት እየፈለገ ሊምርህ የሚፈልግ አምላክ ስላለህ ከእድለኝነትም በላይ ነውና እግዚአብሔርን ይመስገን።


#እግዚአብሔር_ይመስገን።
#እግዚአብሔር_ይመስገን።
#እግዚአብሔር_ይመስገን።


@ይሄ ነው ሐበሻ!
https://t.me/yihenewhabesha
48 viewsNebiይ, 13:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 12:33:09 #አለመወዳደር ወይስ #መወዳደር_አለመፈለግ

ማን ፈጣን እንደሆነ ለማውቅ አቦ ሸማኔውን ከአራት ፈጣን ውሻዎች ጋር እንዲወዳደር አደረጉት። ነገር ግን ውድድሩ ተጀምሮ ውሻዎቹ መሮጥ ሲጀምሩ አቦ ሸማኔው በመሮጥ ፈንታ ቁጭ ብሎ ይመለከታቸው ጀመር። ሁሉም የውድድሩ ተመልካቾች የአቦ ሸማኔው አለመሮጥ እና ከቦታው አለመንቀሳቀስ አስገርሟቸው 'ምን ተፈጠረ ?' ሲሉ ጠየቁ !!

...አንዳንዴ ምርጥ መሆንህን ለማስመስከር ከሁሉም ጋር #መወዳደር መሞከር #ሞኝነት ነው። ስድብም ነው። ጠንካራ መሆንህን ለማሳየት ከደረጃህ መውረድ አያስፈልግህም። አቅምህን፣ ኃይልህን፣ ችሎታህን ለሚገባ ነገር ብቻ አውሉው።

bini_girmachew

@ይሄ ነው ሐበሻ!
https://t.me/yihenewhabesha
65 viewsNebiይ, 09:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 12:53:36 … #ችግር የለውም…

አንዳንዴ መጥላት ያለብንን ወደን…መውደድ ያለብንን ደሞ እንጠላለን…እኔ ደሞ ቶሎ ነው እማምነው…ወሸት እሚባል ያለ እስካይመስል አምናለው…መመኔን አልጠላውም…ግን እማምንበት መንገድ ያናደኛል…

ብዙ ጊዜ…አዋ በጣም ብዙ ጊዚያትን ይህን ቃል እልሽ ነበር…ችግር የለውም…ግን ችግር ሳይኖረው ቀርቶ እንዳይመስልሽ…ችግርማ አለው…ግን አንቺ ከችግሩ ትበልጫለሽ…ለዛም ነው…

…# ችግር የለውም…

ሰው እሚናደደው በሚወደው እና ግድ በሚሰጠው ሰው ነው…ምን አገባኝ በምንወደው ሰው ላይ አንልም… እኔ ለአንቺ ብቻ የነገርኩሽን እና እንቺ ብቻ እምታውቂያቸውን ሚስጥሮች ነበሩኝ…ሚስጥሮቼን ግን ከሌላ ሰማሁዋቸው…ግን ችግር የለውም…

…# ችግር የለውም…

እናም ችግር የለውም ስልሽ ችግር እያለው ነው…ግድ የለምም እምልሽ ግድ እያለው ነው…

… #ችግር የለውም…

እየተበደሉ ይቅር በሉኝ ማለት ግን ምን ያህል ብፁዕነት ነው…እየተከፉ መሳቅስ…መውራት ፈልጐ ዝም ማለትስ…እኔጃ…ብቻ ውስጤን ዛሬ ድረስ ብዙ ነገር ይለኛል…ቢለኝም ግን ችግር የለውም…

…ብቻ ውስጤ እንዲህ ይለኛል…

#ችግር የለውም
እኛ የችግር ተለውም ትውልዶቸወ
@ይሄ ነው ሐበሻ!
https://t.me/yihenewhabesha
61 viewsNebiይ, 09:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ