Get Mystery Box with random crypto!

… #ችግር የለውም… አንዳንዴ መጥላት ያለብንን ወደን…መውደድ ያለብንን ደሞ እንጠላለን…እኔ | ይሄ ነው ሐበሻ!

… #ችግር የለውም…

አንዳንዴ መጥላት ያለብንን ወደን…መውደድ ያለብንን ደሞ እንጠላለን…እኔ ደሞ ቶሎ ነው እማምነው…ወሸት እሚባል ያለ እስካይመስል አምናለው…መመኔን አልጠላውም…ግን እማምንበት መንገድ ያናደኛል…

ብዙ ጊዜ…አዋ በጣም ብዙ ጊዚያትን ይህን ቃል እልሽ ነበር…ችግር የለውም…ግን ችግር ሳይኖረው ቀርቶ እንዳይመስልሽ…ችግርማ አለው…ግን አንቺ ከችግሩ ትበልጫለሽ…ለዛም ነው…

…# ችግር የለውም…

ሰው እሚናደደው በሚወደው እና ግድ በሚሰጠው ሰው ነው…ምን አገባኝ በምንወደው ሰው ላይ አንልም… እኔ ለአንቺ ብቻ የነገርኩሽን እና እንቺ ብቻ እምታውቂያቸውን ሚስጥሮች ነበሩኝ…ሚስጥሮቼን ግን ከሌላ ሰማሁዋቸው…ግን ችግር የለውም…

…# ችግር የለውም…

እናም ችግር የለውም ስልሽ ችግር እያለው ነው…ግድ የለምም እምልሽ ግድ እያለው ነው…

… #ችግር የለውም…

እየተበደሉ ይቅር በሉኝ ማለት ግን ምን ያህል ብፁዕነት ነው…እየተከፉ መሳቅስ…መውራት ፈልጐ ዝም ማለትስ…እኔጃ…ብቻ ውስጤን ዛሬ ድረስ ብዙ ነገር ይለኛል…ቢለኝም ግን ችግር የለውም…

…ብቻ ውስጤ እንዲህ ይለኛል…

#ችግር የለውም
እኛ የችግር ተለውም ትውልዶቸወ
@ይሄ ነው ሐበሻ!
https://t.me/yihenewhabesha