Get Mystery Box with random crypto!

#ብንስማማስ ???!!! እንዲህ የሚል ከጥንት ጀምሮ የሚታወቅ የአይሁዳውያን ተረት አለ፡- አንዲ | ይሄ ነው ሐበሻ!

#ብንስማማስ ???!!!

እንዲህ የሚል ከጥንት ጀምሮ የሚታወቅ የአይሁዳውያን ተረት አለ፡-

አንዲት በጣም የተራበች ድመት ከአንድ ሱቅ ስጋ ሰረቀች፡፡ ያንን ሌብነቷን የተመለከተ አንድ ውሻ ነበረና እኩል ካላካፈልሽኝ አጋልጥሻለሁ አላት፡፡ ድመቷ መካፈል ስላልፈለገች መጣላት ጀመሩ፡፡ ሁለቱ በነበራቸው ጸብ ማንም ማሸነፍ ስላልቻለና ጸቡ ማቆሚያ ስላጣ የስጋው ሽታ ስቧት የመጣች በአካባቢው የነበረችን አንዲት ቀበሮ ጠሩና እንድትዳናኛቸው ጠየቋት፡፡

ቀበሮዋ፣ “ከምትጣሉ ስጋውን እኩል ተካፈሉ” የሚልን ቀላል ምክር ለገሰቻቸው፡፡ በምክሩ ሁለቱም በመስማማታቸው ድመት ስጋውን ለሁለት ቆርጣ ለውሻ አካፈለች፡፡ ሆኖም ውሻው፣ የተሰጠው ድርሻ አናሳ እንደሆነ በማሰብ ጸቡን አላበርድ አለ፡፡ በዚያን ጊዜ ቀበሮ የስጋውን መጠን በማስተካከል ሰበብ ከድመት ድርሻ ላይ ደህና አድርጎ በመቦጨቅ ዋጥ በማድረግ ውሻን አስደሰተና ለማስተካከል ሞከረ፡፡

አሁን ደግሞ ድመት የእሷ በመቀነሱ ምክንያት፣ “የውሻ ድርሻ በዝቷል” በማለት ጸቡን አላበርድ አለች፡፡ አሁንም ቀበሮ ድመትን ለማስደሰት በሚል ሰበብ ከውሻው ድርሻ ላይ ጠቀም ያለ መጠን ቦጨቅ በማድረግ ዋጥ አደረገ፡፡ አሁን ደግሞ ውሻ እንደገና የእሱ ማነሱን ሲያይ የድመት በዝቷል፣ ከዚያም ቀበሮ ድርጊቱን ሲደጋግም ድመት ደግሞ የውሻ በዝቷል ሲባባሉ፣ ቀበሮ ከዚህም ከዚያም ሲቀናንስ ስጋውን ጨረሰውና ድመትና ውሻ ምንም ሳይደርሳቸው ባዶ ቀሩ ይባላል፡፡

ተጣልተን ሁሉን ከምናጣ #ተስማምተን ግማሽ ማግኘቱና አብሮ መኖሩ አይሻለንም?
@ይሄ ነው ሐበሻ!
https://t.me/yihenewhabesha