Get Mystery Box with random crypto!

ይሄ ነው ሐበሻ!

የቴሌግራም ቻናል አርማ yihenewhabesha — ይሄ ነው ሐበሻ!
የቴሌግራም ቻናል አርማ yihenewhabesha — ይሄ ነው ሐበሻ!
የሰርጥ አድራሻ: @yihenewhabesha
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 193
የሰርጥ መግለጫ

@ይሄ ነው ሐበሻ!

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-15 07:17:39 + #ዝም_ብለን_የምንጠላው_ሰው +

ከሩቅ የምናውቀው አንዳንድ ሰው የለም? ብዙም አናውቀውም:: ቀርበን አውርተነው አናውቅም:: ስናየው ግን እንዲሁ ደስ የማይለንና ያለ ምክንያት የምንጠላው ሰው የለም?

"እሱን ሰውዬ ጥሎብኝ አልወደውም"

"አይ እሱን ልጅ ቀልቤ ትከሻዬ አልወደደውም"

"እኔ እንጃ ለምን እንደሆነ ባላውቅም አልወዳትም:: ምክንያቴን አትጠይቀኝ ግን በቃ እንዲሁ አልወዳትም"

ምንም ምክንያት ሳይኖረን እንዲሁ #የምንጠላው ሰው አለ::

እግዚአብሔር ግን
"አንድያ ልጁን እስኪሠጥ ድረስ ዓለሙን #እንዲሁ_ወዶአል" (ዮሐ 3:16)

ጠላቶቹ ሳለን በልጁ ሞት አዳነን እንደሚል እርሱ እኛን ለመጥላት ብዙ ምክንያት ነበረው:: እርሱ ግን እንዲሁ #ወደደን:: ከእኛ ምንም ባያገኝም ስለ እኛ ያለው ፍቅር የእንዲሁ ፍቅር (unconditional love) ነበረ:: እርሱ #እንዲሁ_ወዶናል እኛ ግን እንዲሁ ሰው እንጠላለን::
ያለ ምክንያት #መውደድ ቢያቅተን እንኳን ያለ ምክንያት #መጥላታችን (unconditional hate) ቢቀር ምናለ?
የሚያሳዝነው ያለ ምክንያት የጠላናቸውን ሰዎች የበለጠ ለመጥላት በልባችን እስር ቤት ውስጥ በጥላቻ ሰንሰለት እናስራቸውና የበለጠ ለመጥላት ስለእነርሱ ክፉ ክፉ ማስረጃ ለመስማት እንተጋለን:: ጥሩ ነገራቸውን ለመስማት አንፈልግም:: ክፉ ስንሰማ ግን "እኮ እኔ እኮ ዝም ብሎ ትከሻዬ ይነግረኝ ነበር" ብለን በደስታ እንፈነድቃለን:: እንዲሁ የጠላነውን ሰው በምክንያት ለመጥላት በመቻላችን ደስ ይለናል::

እኛ ሰውን ለመጥላት ምክንያት የምንፈልገውን ያህል እንዲሁ የወደደን እግዚአብሔር ግን እኛን ለመማር ሰበብ ይፈልጋል:: #ትንሽ በጎነት ቅንጣት ቅንነት ሲያገኝ እጅግ ይደሰታል:: ባለቅኔው "እግዚአብሔር መንግሥቱን በርካሽ ዋጋ ሸጠው:: በቀዝቃዛ ውኃ በዘለላ ዕንባ እና ማረኝ በሚል የወንበዴ ጩኸት!" እንዳሉት እሱ እኛን ይቅር ለማለት የሚታይ በጎነት ቢያጣ ልባችን ውስጥ ገብቶ ትንሽ መጸጸት ካለ ይፈልጋል:: #እንዲሁ ወዶናልና እንዲሁ ሊተወን አይፈልግም::

"እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለሆነ
ከወደደን ከትልቅ #ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳን በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወትን ሠጠን"
ኤፌ 2:4

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
@ይሄ ነው ሐበሻ!
https://t.me/yihenewhabesha
70 viewsNebiይ, 04:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 07:54:05 #ወጥነት (consistency)

ብርድ ነው ብለን እንቅልፍን አንመርጥም። ሠው አይኖርም ብለን ከመንገዳችን ወደኅላ አንልም።

ሁሌም ለአላማችን እንተጋለን። ለውጥ ሂደት ነው። ቀናት፣ ወራት፣ አመታትን ይፈልጋል። በዚህ ረጅም መንገድ ለመጓዝ #የወጥነትን ባህሪ (consistency) ማዳበር ይገባናል። በህይወታቸው የፈለጉትን ያገኙ ሠዎች ትልቁ ባህሪያቸው #ወጥነት ነው። የትኛውም ሁኔታ ከሀሳባቸው እንዲያስቆማቸው አይፈቅዱም።

በየትኛውም የህይወት ክፍላችን ላይ (በስራ፣ በግንኙነት፣ በመንፈሳዊነት ወዘተ) #ወጥነትን ይኑረን። ያሰብነውን ውጤት እስክናገኝ ድረስ በመንገዱ ላይ እንቆይ። #ወጥ እንሁን።
ሙና ጀማል

@ይሄ ነው ሐበሻ!
https://t.me/yihenewhabesha
69 viewsNebiይ, 04:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 22:25:08 … #ተቀበል …

"እያንዳንዱ ሰው የራሱ የሆነ #ስብዕናና ቀለም አለው፣ ያንን ቀለም ማየት ካልቻልክ ችግሩ ያለው ሰውዬው ጋር ሣይሆን አንተ ጋር ነው። አህያ እፊትህ ቢንፈራገጥ ወይም አመድ ላይ ቢንከባለል መናደድ የለብህም። አህያው ያደረገው #የተፈጥሮውን ነው።

ብዙውን ጊዜ ጠብ ውስጥ የምንገባው ሰዎችን #ወደራሳችን ስብዕና ለመጎተት ስለምንሞክር ነው። ሰውን በራሱ ስብዕና አናከብረውም። ስም የምንሰጣጣውና የምንጠላላውም ለዚህ ነው።

በዚህ ዓለም #ከምትፈልገውም #ከማትፈልገውም ሁኔታ ጋር አብረህ ትኖራለህ። ሁሉም ነገር አንተ እንደምትፈልገው አይሆንም። ደስተኛ መሆን የሚመጣው የምትፈልገውን #ከማድነቅና የማትፈልገውን #ከመቀበል ነው።"

#ማድነቅና_መቀበል

ከፍልስምና መፅሐፍ በቴዎድሮስ ተ/አረጋይ
@ይሄ ነው ሐበሻ!
https://t.me/yihenewhabesha
82 viewsNebiይ, 19:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 20:32:25 #እግዚአብሔር_ሆይ_ተመስገን!


ሁለት ሰዎች በአንድ ጉዳይ አብረው ይጸልያሉ። አንደኛው ጸሎቱ ተመለሰለት፣ አንደኛው ሳይመለስለት ቀረ። በዚህ ጊዜ ጸሎቱ ያልተመለሰለት፡- “ጌታ ሆይ ሁለታችንም እኩል ጸለይን ለእርሱ ሰጥተኸው ለእኔ የከለከልከኝ ለምንድን ነው?” አለው። #እግዚአብሔርም፡- “ለእርሱ ባልሰጠው ይጠፋል፣ ላንተ ከሰጠሁህ ትጠፋለህ” አለው።

#እግዚአብሔር ከራሳችን በላይ እኛን ያውቀናል። ለአንዳችን በመስጠት፣ አንዳችንን በመከልከል ዕድሜያችንን ያረዝመዋል። መስጠቱም መንሣቱም ሁለቱም ለፍቅር ነውና ስለሆነልን ስለሚሆንልንና ስላልሆነልን ነገር ሁሉ #እግዚአብሔር ሆይ #ተመስገን፡፡

ስለ ላለፈው ስለሆኑትና ስላልሆኑት ነገሮች ሁሉ #እግዚአብሔር ሆይ #ተመስገን!

ዛሬ ስለሆኑትና ስላልሆኑት ነገሮች ሁሉ #እግዚአብሔር ሆይ #ተመስገን!

ወደፊት ስለሚሆኑትና ስማይሆኑት ነገሮች ሁሉ #እግዚአብሔር ሆይ #ተመስገን

@ይሄ ነው ሐበሻ!
https://t.me/yihenewhabesha
69 viewsNebiይ, 17:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 14:09:10 #ቶም እና #ጄሪ


#ቶምና_ጄሪ የሚያስማሟቸው ሁለት ነገሮች ብቻ ናቸው። የመጀመሪያው ጥቅም ሲሆን ሁለተኛው የጋራ የጠላት መኖር ነው።
በሃገራችን ያሉ #ቶሞችናየጄሪዎች አንድ የሚሆኑት ጥቅም እስከተገኘ ብቻ ነው፤ ጥቅም ከተገኘ በርእዮተ አላማቸው ላይ እንኳን የረባ ውይይት ሳያደርጉ፤ የቱጋ የአቋም ለውጥ እንዳደረጉ በሚገባ ሳይረዱም ሳያስረዱም በቅጽበት ይቀናጃሉ፤ ይተባበራሉ፤ ይዋሐዳሉ፤ ግንባር ይመሰርታሉ። አከፋፈል ላይ ሲለያዩ ደግሞ የተባበሩ ቀርቶ የተጎራበቱ መሆናቸውን እስክንጠራጠር ድረስ ይናከሳሉ።
#ለቶም_እንደ_ጄሪ፣ ለጄሪም እንደ ቶም #የሚቀርባቸው የለም። በሌላ በኩል ደግሞ ለቶም እንደ ጄሪ፣ ለጄሪም እንደ ቶም #የሚጎዳቸው የለም። እኛም ይህንን ፊልም በመስራት ላይ ነን።
አሁንም ተቃውሞ እና ጠላትነትን አልለየንም፣ አሁንም ገና ደጋፊነትንና ምእመንነትን አልለየንም። ተቃዋሚያችን ምንም ዓይነት በጎ ነገር ቢያስብ ከመቃወም አንመለስም፤ ጠላትነት እንጂ ተቃውሞ አናውቅማ። የምንደግፈው አካልም ምንም ዓይነት ጥፋት ቢያጠፋ ከማመስገን ወደ ኋላ አንልም፤ ምእመንነት እንጂ ድጋፍ አናውቅም። አይ #ቶም_እና_ጄሪ።
ሁለት ኢትዮጵያውያን ጎራዎችን ለማስታረቅ የተሰየሙ የሀገሬ ሽማግሌ ያሉኝን ልንገራችሁ…
አንደኛው ወገን ከሌላው ወገን ጋር ለማስታረቅ በቅድመ ሁኔታነት አሥራ አምስት ነጥቦችን ያስቀምጣል። ሽማግሌዎቹም ይህንኑ ይዘው ወደዚያኛው ጎራ ይሔዱና ጉዳዩን ያቀርባሉ። እነዚህኞቹም ቡድኖች ከተወያዩ በኋላ "አሥራ አምስቱንም ነጥቦች በሙሉ እንቀበላለን" ብለው መልስ ይሰጣሉ። ሽማግሌዎቹም ድካማቸው ፍሬ በማፍራቱ ተደስተው ወደነዚያኞቹ ይሄዱና "እነዚያኞቹ በሐሳባችሁ ሙሉ በሙሉ ተስማምተዋል" ይሏቸዋል። ሰዎቹም አላመኑም "አሥራ አምስቱንም ነገር ተቀበሉት?" ይላሉ። "አዎ ሁሉንም ተቀብለዋል"። "እንዴት አንድ ሁለቱን እንኳን አልተቃወሙም፤ አንዳች ነገር ቢያስቡ ነውና እንዲያውም አንታረቅም" ብለው መለሱልን አሉ።
#የቶምና_ጄሪን ፊልም የጀመራችሁ ተዋንያን፣ እባካችሁ ሌላ ፊልም እንይበት። የመነካከስና የመበላላት፣ የማያቋርጥ ቅንቃኔና ጠላትነት የበዛበት ተከታታይ ፊልም ሰልችቶናል።
.
.
.
.
.
ደግ ደጉን እናስብ፣ በጎ በጎውን እንስራ፣ መልካምነት መልሶ ይከፍለናልና!
.
.
ፈጣሪ #ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!

@ይሄ ነው ሐበሻ!
https://t.me/yihenewhabesha
86 viewsNebiይ, 11:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 09:42:34 … #አንበሳ…

ከዕለታ በአንደኛው ቀን አያ አንበሳ የዱር አራዊት ሁሉ ንጉስ አንደመሆኑ መጠን ከሌሎች እንስሳት በሙሉ ለይቶ ሶስቱን ብቻ በመጥራት ስለ ራሱ የሚሰማቸውን ሳይፈሩና ሰይሳቀቁ አስተያየት እንዲሰጡት ይጋብዛቸዋል ፡፡ ተጋባዦቹም ፡- #በግ ፣ ተኩላ እና ጦጣ ነበሩ
አስተያየት የሚሰጡትንም በአንበሳው በጠረኑ ላይ ብቻ እንደሆነ ተነግሮአቸዋል ፡፡ በዚህ ምክንያት በሚሰጡት አስተያየት አንዳችም አይነት በደል እንደማያደርስባው በአራዊት ሁሉ ፊት ቃል ገብቶላቸዋል በአስተዳዳሩ ላይ ግን አስተያየት መስጠት እንደማይቻል ፣ይህን ማስጠንቀቂያ ተላልፎ መገኘትም ዋጋ እንደሚያስከፍልም ጭምር እንዲሁ በአያ አንበሳ ተነግሮአቸዋል ፡፡
ቅድሚያ አስተያየት ለመስጠት መድረኩን ያገኘችው በግ ነበረች ፡፤ #በግ ወደ አንበሳ ብብት ቀረበች ጠረኑን አሸተተች ...... ወደ ኋላዋም መለስ ብላ ቆመች እና መናገር ጀመረች . . .. በእውነት አያ አንበሳ ሆኜ ከተፈጠርኩ ጀምሮ ይሄ እግሬ ያልወሰደኝ ቦታ የለም ፡፡ ነገር ግን እንዲህ እንደዛሬው እንደ እርሶ ብብት መጥፎ አስቀያሚ ሽታና ጠረን ገጥሞኝ አያውቅም ፡፡ ምን አለ ዳሩ ሁሉ በውኋ የተሞላ ነው ፡፡ከወንዙ ወርደው ቢታጠቡ ? እንደው ለመሆኑ የእኛስ በሩቅ ነው ቤተሰቦዎችዎ በተለይ ደግሞ ባለቤትዎ እንዴት አብራዎት ኖረች ? በማለት እውነቱን ተናግራ ተቀመጠች ለመሆኑ የእኛስ በሩቅ ነው ቤተሰቦዎችዎ በተለይ ደግሞ ባለቤተዎ እንዴት አብራዎት ኖረች ? በማለት እውነቱን ተናግራ ተቀመጨት ፡፡ ከአድማጮች እና ተመልካቾች ለዚህ የንጉስ አስተያየት ጭብጨባው ሞቅ ያለ ነበር ፡፡ ጎብዝ ፣ደፋር ፣ጀግና ፣ሌላ ሌላ ከአጨብጫቢዎችም ወገን የተሰነዘሩ የሙገሳ ቃላት ነበሩ፡፡ አያ አንበሳ ግን #በግን ጠራት ወደ ዙፋኑ ፡፡ ሊሸልማት ግን አልነበረም በአራዊት ሁሉ ፊት ቅርጥፍጥፍ አድርጎ በላት ፡፡ በአራዊት ሁሉ ፊት ቅርጥፍጥፍ አድርጎ በላት ፡፡ አጨብጫቢዎች አሁንም ከቅድሙ በበለጠ ሞቅ ያለ ጭብጨባ ለአንበሳ ለገሱ፡፡ እስክተለውም እንዴት ብትዳፈር ነው ፣ የማናት ደፋር ፣ ያውም ንጉሳችንን አሉ ተባባሉም ፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ቀሪዎቹ አስተያየት ሰጪዎች በስፍራው ላይ ሆነው ድርጊቱን ይመለከቱ ነበር ፡፡
የተኩላ ተራ ደረሰ ፡፡ ቀርቦም የአያ አንበሳን ብብት አሸተተ ፡፡ እንዲህም ብሎ አስተያየቱን መስጠት ጀመረ፡፡ በእውነት አለ ተኩላ በእውነት እኔ ዛሬ እድለኛ ነኝ ፡፡ ምክንያቱም ከሁሉም በላይ በአያ አንበሳ ተመረጬ ወደ ዙፋኑ ቀርቤ ብብቱን እንዳሸት መመረጤ በራሱ እጅግ ልዩ መታደል ነው ፡፡በማለት ንግግሩን አስከትሉ ፡፡ በመጨረሻም ወደ ተነሳሁበት ጉዳይ ስመለስ እኔ በምድር ላይ ዞሬአለሁ ብዙ ነገሮችንም አሽትቼያለሁ እንደዛሬ እያ አንበሳ ብብት ያለ ግሩም መዓዛ ያለው ጠረን አጋጥሞኝ አያውቅም በማለት ተቀመጠ፡፡ ተኩላ በአፉ እንዲህ ይበል ከአንበሳ ብብት ወደ አፍንጫው የገባው መጥፎ ጠረን እያስነጠሰው ነበር ይህ ግን ያስተዋለ ማንም አልነበረም ፡፡ ተመልካች አድማጩ ግን ከመቀመጫው ተነስቶ ጭብጨባውን በፉጨት አጅቦ ረዘም ላሉ ደቂቃዎች አጨብጭቦ ፡፡አያ አንበሳም ፡ ተኩላን አለው ጎበዝ እንዲያው ሽልማትም ይገባሀል በማለት ከገደላትና ከበላት በግ ላይ የተረፈ አጥንቶችን ሰጠው ተኩላ የበግን አጥንት በሁሉም አራዊት ፊት ሳይሳቀቅ በላ ፡፡ አሁን ተራው የጦጣ ሆነ ፡፡ የአያ አንበሳን ብብትም አሸተተች ፡፡ ጦጢት በግን በአንበሳ ያስበላት ተኩላን ደግሞ ያሸለመውን ጉዳይ በደንብ አይታለችና ፡፡ እንዲህም ብላ መናገር ጀመረች ፡፡ያ አንበሳ እኔ እኮ በእርስዎ ተጠርቼ አልቀርም ብዬ ነው እንጂ አፍንጫዬ ከትናት ጀመሮ ማሽተት እንቢ ብሎኛል በማለት ተናገረች ፡፡ እንዲህ ብላ በመዋሸት ትናገር እንጂ እሱዋም ከመጥፎ ጠረኑ የተነሳ ደጋግማ ታስነጥስ ነበር ፡፡ አንበሳም ጎበዝ ብሎ አደነቃት ፡፡ ተመልካች አድማጩም እንደተለመደው ጭብጨባውን አቀለጠወው ፡፡
የተረቱ ማጠቃላያ ፡፤ እውነት ተናግረው የሚበሉት በጎች ፣ ሐሰት ተናግረው የሚሸለሙ ተኩላዎች ፣ መሃል ሰፋሪና እኔ ምንገባኝ ባይ ጦጣዎች ፣ ለሁሉም የሚያጨበጭቡ አድማጭ ተመልካቾች አሉ ፡፡ ይህ ደግሞ እውነት ነው ፡፡ እነዚህን ሰዎች በየትም ቦታ እናገኛቸዋለን ፡፡ እና እርስዎስ እራስዎን ከየት መደብ ፡፡ በቤተሰብ፣ በፓለቲካ፣ በኑሮ፣ በሀገርም ሆነ በሃይማኖትዎ ጉዳይ ከየትኛው ወገንነዎት ?፡፡ #ከበግ ፣ ከተኩላ ወይስ ከጦጣ ፡፡
እኔ ግነ >ከበግ ወገን የሆነ ወዳጅ ነው ያለኝ። ይመስገነው! ይቆየን!
@ይሄ ነው ሐበሻ!
https://t.me/yihenewhabesha
77 viewsNebiይ, 06:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 09:06:34 … እኛ ከብሶት፣ ከቁጭት፣ ከጠበሳዎችን፣ ከችግሮቻችን ውጪ ምንድን ነን?

በሕመምና በሥቃይ ውስጥ እናልፋለን። እኔም ያመመኝ ጊዜ ለአንድ ወዳጄ ደውዬለት ነበር። ያን ምሽት ለረጅም ሰዓታት አወራን። ስለጠባሳዎቼ አንስቼ ሥቃይ ምን ያህል እንደ ሰለቸኝ ነገርኩት። በድምጼ ውስጥ የመከራዬን ክብደት አሳየሁት። በትዕግስት አድምጦኝ ከጨረሰ በኃላ ዛሬም ድረስ የማረሳውን አንድ ጥያቄ ጠየቀኝ።
" ካለጠባሳዎችህ አንተ ምንድን ነህ" ብሎ ካለጠበሳዎቼ ካለችግሮቼ እኔ ምንም አልነበርኩም። ጠበሳዎቼ ችግሮቼ ቢጠፉ የምናገረው ታሪክ የሌለኝ ነኝ።
ሕይወት አልጋ በአልጋ አይደለችም። የተወለድነው በጣዕርና በሥቃይ ውስጥ ነው። እናቶቻችን ሲወልዱን «ምጡን እርሺው ልጁን አንሺው» የተባሉ ናቸው። ተፅፈው ያነበብናቸው፣ የወደድናቸው መፅሕፍት ገፀ ባህርያት ሳይቀሩ በፅኑ መከራ ውስጥ ተፈትነው ያለፋ ናቸው። ምናልባት እያንዳንዳችን በየእርምጃዎቻችንና ውሳኔዎቻችን ልክ እየተፃፋ ያሉ ጅምር መፅሐፍቶች ነን። እያዘጋጀን ላለነው ግለ ታሪክ ፀሐፊውም ዋና ገፀ ባህርይውም እኛ ነን።
እስቲ መምን መልኩ ታሪካችንን መዝጋት እንፈልጋለን።
እሱባሌው አበራ ንጉሤ

እኛ ከችግሮቻችን ውጪ ምን አለን? ለሰው የምንነግረው ምን ብሷት ያልሆነ ነገር ምን አለን?
በስራችን ከምናማርረው ወቀሳ ውጪ ምን አለን?
በመንፈሳዊ ሕይወት በምንማረው ትምህርት «አሉ» ከምንለው ውጪ ምን ተግባር አለን?
ፓለቲከኞች ከሚያነሳሱን የቁጭት ትርክት በስተቀር ምን የምንሰማው ለሌላ የምንናገረው ምን ታሪክ አለን?
እኛ በችግራችን፣ በጠበሳችን፣ በብሶታችን፣ በወቀሳችን ብቻ የምንታወቅ ከሆነን እኛ ምንም ነን?

@ይሄ ነው ሐበሻ!
https://t.me/yihenewhabesha
95 viewsNebiይ, 06:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 13:26:17
ይህ ምስል ትክክለኛና ያልተነካካ ነው፤ ድንጋዩ፣ ዛፎቹ፣ አፈሩ፣ እና ሰማዩ የእውነት ነው።
አሁን ማድረግ ያለብህ ብቸኛ ነገር #እይታህን መቀየር ነው፤ ምስሉን ገልብጠህ ተመልከት።

#እይታንና_አመለካካትን_በመቀየር_ሕይወትን_ቀይር!

#ሁኔታዎች ሁሉ መጥፎ አይደሉም ነገር ግን #በእይታህ ምክንያት ነገሮች ትርጉም አልባ ይሆናሉ። #እይታህንና_አመለካከትህን በማስተካከል ሕይወትህን አስተካክል:: ዋ! አትሸወድ!!
@ይሄ ነው ሐበሻ!
106 viewsNebiይ, 10:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 15:08:38
@ይሄ ነው ሐበሻ!
109 viewsNebiይ, 12:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 07:37:44 =====----- #ለቃል_ታመን! -----=====

የሚገርማችሁ እስካሁን ባሳለፍኩት ሂይወት ትልቁ የህይወት ትምህርት ያገኘሁት ሁልጊዜም ለራሴ ቃል #መታመን እንዳለብኝ የገባኝ ቀን ነው። ለዚህም ይመስለኛል አደርገዋለሁኝ ወይም #ለራሴ_ቃል የገባሁትን እንደማደርገው እርግጠኛ ስለሆንኩኝ ያሰብኩትን ስለምኖር በጣም በራስ የመተማመን እና የተረጋጋ ሰላማዊ ኑሮ እና ህይወት እመራለሁ።

በዚህ ውስጥ በደንብ ያረጋገጥኩት ቢሮር ለምትፈልገው ነገር የሚያቆምህ #አመለካከትህ መሆኑን ነው! ሰዎችና ሁኔታዎች ጠንካራ ከሆንክ ከጎንህ ይቆማሉ፤ በአላማህ የማትፀና ወይ ልፍስፍስ ከሆነክ ግን ሁሉም ይጠቀምብሀል፤ ለራሳቸው ፍላጎት መረማመጃ ያደርጉሀል።
ነገሮች #በፈለከው መንገድ ላይሄዱ ይችላሉ፣ ሰዎች ጀርባቸውን ሊያዞሩብህ ይችላሉ፣ በዚህ አለም ለመኖር የሚያጓጉህን ነገሮች ሁሉ ልታጣ ትችላለህ፤ #ልብህን፣ ህልምህን የመኖር #ትርጉሙም ሊጠፋህ ይችላል ነገር ግን ሁላችንም በዚህ ስሜት ውስጥ አልፈን እናውቃለን ወደፊትም እናልፍ ይሆናል።

ግን #እመነኝ ነገሮች ተቀይረው ታላቅነትህን ለራስህ ለማሳየት ግን በዚህ ከባድ ጊዜ መቼም ተሰፋ ሳትቆርጥ ጥረትህን ወደ ስኬት ለመቀየር #ለራስህ_ቃል መግባት አለብህ! ያኔ ቃልህን ስትኖረው ታሪክ ይቀየራል!

#እናም_ለቃልህ_ታመን_ወዳጄ!
@ይሄ ነው ሐበሻ!
https://t.me/yihenewhabesha
120 viewsNebiይ, 04:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ