Get Mystery Box with random crypto!

+ #የአንድ_ሰው_ውሎና_አመሻሽ + ይህ እስካሁን ምንጩን ያላገኘሁት አንድ ወንድሜ የላከልኝ በፈ | ይሄ ነው ሐበሻ!

+ #የአንድ_ሰው_ውሎና_አመሻሽ +

ይህ እስካሁን ምንጩን ያላገኘሁት አንድ ወንድሜ የላከልኝ በፈረንጅ አፍ የተጻፈ የቆየ የአንድ ሰው ገጠመኝ ነው :-

አንድ ወንድም #ስልኩን ድምፅ አልባ ማድረግ ረስቶ ወደ #ቤተ_ክርስቲያን ገብቶ ስብከት ይማራል:: በዚህ መካከል ስልኩ ይጮኃል::

ሰባኪው ስብከቱን አቁሞ በዓይኖቹ ተቆጣው:: ከስብከቱ በኋላ ምእመናን ስብከቱን በመረበሹ #ወቀሱት:: አንዳንዶቹም እያዩት ራሳቸውን በትዝብት ነቀነቁ:: ከሚስቱ ጋር ወደ ቤታቸው ሲሔዱም ሚስቱ ስለ #ቸልተኝነቱ ምክር መሥጠትዋን ቀጠለች::
እፍረት መሸማቀቅና ውርደት ዘልቆ እንደተሰማው በፊቱ ላይ ይታይ ነበር:: ከዚያች ሰንበት በኋላ እግሩን ወደ ቤተ ክርስቲያን አንሥቶ አያውቅም::

ውስጡ የተረበሸው ይህ ሰው ያንኑ ምሽት ወደ #መጠጥ_ቤት አመራ:: አእምሮው እንደታወከ ነበር::

ቁጭ ባለበት ድንገት የሚጠጣበት #ጠርሙስ ወድቆ ተሰበረና መጠጡም በዙሪያ ተረጨ:: ፍንጣሪው የነካቸው ሰዎች ወደ እሱ መጠጋት ጀመሩ:: ሊጮኹበትና በጥፊ ሊሉት እንደሆነ ታውቆት ቀድሞ #ዓይኖቹን_ጨፈነ::

ሰዎቹ ግን በተሰበረው ጠርሙስ ስብርባሪ #ተጎድቶ_እንደሆነ_ተጨንቀው ጠየቁት::

#አስተናጋጁ መጥቶ የፈሰሰበትን እንዲያደርቅ ማበሻ ሰጠው:: #የጽዳት ሠራተኛዋ መሬቱን ወለወለች::

የቤቱ ባለቤት " #አይዞህ_ያጋጥማል? ዕቃ የማይሰብር ማን አለና?" አለችውና ሌላ መጠጥ አስመጣችለት::
ከዚያች ቀን ጀምሮ ከዚያ መጠጥ ቤት #ቀርቶ_አያውቅም::

#በቤተ_ክርስቲያን ውስጥ ስልክን ክፍት ማድረግና ሥርዓተ አምልኮ መረበሽ መቅደስ ውስጥ ጫማ አድርጎ የመግባት ያህል ስኅተት ነው:: እንኩዋን ቤተ ክርስቲያን #ኤምባሲ እንኩዋን ስልክህን ውጪ አስቀምጠህ ትገባለህ:: ሰውዬው ላጠፋው ጥፋት ግን #በፍቅር የሚያናግረው ሰው በማጣቱ ከነ ስልኩ ሊጠፋ ወሰነ::

ቤተ ክርስቲያን #የድኅነት ሥፍራ ናት:: መጠጥ ቤት ደግሞ የጥፋት ጎዳና ነው:: በዚህ ሰው ታሪክ ውስጥ ግን #በድኅነት ሥፍራ ካሉ ሰዎች ይልቅ #በጥፋት ሥፍራ ያሉ ሰዎች ለሰውዬው ስኅተት የተሻለ #ፍቅር አሳዩ:: አንዳንዴ የአንዳንድ ምእመናን #ጠባይ ነፍሳትን ወደ ሲኦል ይሰድዳል::

አንዳችን የአንዳችን ጠባቂ መሆን እንችላለን ዓለምን ለመፈወስ የሚቻለንን እናድርግ:: ነፍሳትን #ከማዳን ነፍሳትን #ማጥፋት በጣም ቀላል ነው::

መድኃኔዓለም ክርስቶስ የኃጢአተኞች #ወዳጅ ነበረ:: እሱ የማንንም ቅስም በክፉ ቃል አልሰበረም:: እኛ ግን ሰው ላይ ስንጨክን መጠን የለንም:: በዚህ ምክንያት እንደ ኒቼ ያሉ ሰዎች "ብቸኛው #ክርስቲያን መስቀል ላይ #የሞተው ነው" ብለው እስኪዘብቱብን ደርሰዋል::

#መጽሐፍ ግን ሰው ሲሳሳት ስናይ ምን ማድረግ እንዳለብን እንዲህ ሲል ይናገራል :-

"ወንድሞች ሆይ፥ ሰው በማናቸውም #በደል ስንኳ ቢገኝ፥ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ እንደዚህ ያለውን ሰው በየውሃት መንፈስ #አቅኑት" ገላ. 6:1

በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
@ይሄ ነው ሐበሻ!
https://t.me/yihenewhabesha