Get Mystery Box with random crypto!

#ልብህ_ውስጥ_ምን_አለ ? አንድ ገበሬ፣ በረት ውስጥ ባለ የሳር ክምር ውስጥ የእጅ ሰዓቱ ጠፋበት | ይሄ ነው ሐበሻ!

#ልብህ_ውስጥ_ምን_አለ ?

አንድ ገበሬ፣ በረት ውስጥ ባለ የሳር ክምር ውስጥ የእጅ ሰዓቱ ጠፋበት። ሰዓቱ ለእሱ ተራ አልነበረም፤ የሚወደው አያቱም ማስታወሻም ነበር።
ክምሩ ውስጥም ላይ ታች ፈለገ፤ በኋላም ተስፋ ቆረጠ፡፡ ውጪ ላይ ሲጫወቱ የነበሩ ህጻናትን እንዲረዱት ጠራቸው።
ከእነሱም መሃል ሰዓቱን ላገኘ ሽልማት እንደሚሰጥ ቃል ገባ።
ልጆቹም ይህንን ሲሰሙ እየተሯሯጡ ወደ በረቱ ውስጥ ገቡ። ክምሩንም እየበታተኑ ፈለጉ። ሆኖም ሰዓቱን ሊያገኙት አልቻሉም። ገበሬው ተስፋ ቆርጦ ልጆቹን ይዟቸው ወደ ውጪ ወጣ፤ ከልጆቹ መሃል ያለ አንድ ብላቴና ሌላ እድል እንዲሰጠው ጠየቀ።
ገበሬውም ብላቴናውን ወደታች እየተመለከተው፤ በቅሬታ ፈገግታ “አይ ምን ጥቅም አለው ብለህ ነው፤ የሚገኝም አይመስለኝም” አለና ጉንጩን ቆንጠጥ አድርጎ የእጅ ሰዓቱን እንዲፈልግ ፈቀደለት።
ብላቴናው ወደ በረቱ ገባ፤ ከበረቱ ተመልሶ ሲወጣም በእጁ ሰዓት ይዞ ነበር!
ገበሬው ተደሰተም ተገረመም። ብላቴናውንም፤ “እኛ ፈልገን ያጣነውን አንተ ብቻህን እንዴት አገኘኸው?” ብሎ ጠየቀው።
ህጻኑም መለሰ፣ “ምንም አላደረኩም፤ በጸጥታ መሬት ላይ ተቀምጬ መስማት ጀመርኩኝ። ሰዓቱም ቲክ ቲክ… ሲል ሰማሁት። በድምጹም ተመርቼ አገኘሁት”
****
አንተ እና እኔ ስንሯሯጥ እንውላለን፤ በጸጥታ እና በስክነት ውስጥ ከማሰብም ይልቅ፤ ምስቅልቅል ያለ እና ማሰርያ አልባ ቀንን እናሳልፋለን።
በጩኸት እና በግርግር ውስጥስ ማን ራሱን ያዳምጣል?
ሰላም ያለው፣ ጸጥ ያለ እና የተረጋጋ አእምሮ፤ ምስቅልቅል ውስጥ ከገባ እና ጥድፊያ ውስጥ ካለ አእምሮ በተሻለ ያስባል። ለደቂቃዎች #አእምሮህን ጸጥ አሰኘው፤ #የልብህንም ድምጽ … አድምጥ… ድው… ድው …

#ልብህ ውስጥ ምን አለ?

#ልብህ ምን ይፈልጋል?

@ይሄ ነው ሐበሻ!
https://t.me/yihenewhabesha