Get Mystery Box with random crypto!

❤ የፍቅር ነገር ❤

የቴሌግራም ቻናል አርማ yefeker_neger — ❤ የፍቅር ነገር ❤
የቴሌግራም ቻናል አርማ yefeker_neger — ❤ የፍቅር ነገር ❤
የሰርጥ አድራሻ: @yefeker_neger
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.03K

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-12-30 21:25:16 (አሳዛኝ ታሪክ)

አንዲት ሴት ለፍቅረኛዋ ያለእሷ አንድ ቀን እንዲኖር challenge ትጠይቀዋለች፣ ምንም ሳያወሩ ሳይገናኙ ቀኑን ካሳለፈ ለዘላለም እንደምታፈቅረው ትነግረዋለች እሱም ይስማማል።

በቀጣዩ ቀን ፍቅረኛዋ ቀኑን ሙሉ መልእክት ሳይልክ ሳይደውል ዋለ ግን ያላወቀው ነገር ቢኖር ፍቅረኛው በካንሰር በሽታ ምክንያት ለመሞት 24 ሰአታት ብቻ ነበር የቀራት
በቀጣዩ ቀን ልጁ ወደፍቅረኛው ቤት ሄደ
"አደረኩት የኔ ፍቅር " አለ ግን ከመቀፅበት ከአይኖቹ የእንባ ዘለላዎች ወረዱ ምክንያቱም ፍቅረኛው በሬሳ ሳጥን ውስጥ ነበረች ለመጨረሻ ጊዜ የፃፈችለት ደብዳቤ ይህ ነበር....." አደረከው ፍቅሬ በል አሁን ሁልቀን አድርገው እሺ እወድሀለው"
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
Like ና #አደራ_ሼር_አድርጉ

@yefeker_neger
98 viewsAbduke, 18:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-30 21:05:23 #ልቤ
.
..ልቤ በቃላት ለማስቀመጥ በሚከብዱ ስሜቶች እንደተሞላ ልነግራት ብል አንደበቴ ተሳሰረ ገላጭ መስመር አጣ አፈቅርሻለሁ ወይ እወድሻለሁ ከማለት በዘለለ ሌላ ስያሜ መስጠት አቃተው! ..ዝም ብየ አቀፍኳት በሐይል እጆቼ ዉስጥ ደረቴ ላይ ያዝኳት ምናልባት ስሜቴ ትንሽ ዉል ቢላት..!

Daniel Mak


     ,,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,,
                  •═••• •••═•
  
     @yefeker_neger    ,,,,,, @Abdu_ke
━━━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━━━
     
100 viewsAbduke, 18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-29 22:17:47 አፍቃሪ ይትረፈው


በድህነቴ ወቅት ያቺን ሴት ሳፈቅር
ትዝ ይለኛል ያኔ ኪሴ ባዶ ነበር
መውደዴን ለመግለፅ ውብ ቃላት ደርድሬ
ላሳምናት ብጥር በአፍቃሪ ተግባሬ
አትምጣብኝ አለች አትድረስ ከበሬ
ነገሩ ልክ ናት እኔ አልፈርድባትም
ኪሴ ከጎደለ ፍቅረኛ አልሆናትም
የተትረፈረፈ ከሌለኝ እንጀራ
ሀብቴ ካልዘነበ ላፍታ ሳያባራ
ተቸግራ ልትኖር ልትልስ ፍቅፋቂ
ሴት ወደኔ አትመጣም ለሷ ነኝ ውዳቂ
ቅዳሜን ጠብቄ ክለብ ካልወሰድኳት
ሪዞርት ለሪዞርት ካላንሸራሸርኳት
በስጦታ ብዛት ካላጨናነኳት
እንዲሁ በባዶ አፈቀርኩሽ ብላት
በሉ እስቲ ፍረዱ ምን ፍቅረኛ ሆንኳት
እና ስነግራችሁ ያየሁትን እውነት
አፈቀርኩኝ ያለ ፍቅሩን እንዳያጣት
አስንቆ ሳይጥለው ያ ክፉ ድህነት
ፍቅር እቃ ሆኖ ገንዘብ ከሸመተው
ኪሱ ከቶ አይጉደል አፍቃሪ ይትረፈው
     
Barmura


    ,,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,,
                  •═••• •••═•
  
     @yefeker_neger    ,,,,,, @Abdu_ke
━━━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━━━
     
58 viewsAbduke, 19:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-29 22:14:11 አሁን ስንት ገባሽ

አፍቅሬሽ ከልቤ ያኔ ስጠይቅሽ
አሻፈረኝ ያልሽው ብር የለህም ብለሽ
እድሜ ላንቺ ውዴ አሁን ብር ይዣለው
አሁን ስንት ገባሽ ይሀው ልገዛሽ ነው

Like ና #አደራ_ሼር_አድርጉ

@yefeker_neger
58 viewsAbduke, 19:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-27 21:38:40 ​​እሱን ተይው .....

ስትወጅው ካልወደደሽ
ስትቀርቢው ካልቀረበሽ
ስትጠጊው ካልተጠጋ
ስለፍቅር ካላወጋ
   
      አይሆንሽም እሱን ተይው
      አትድከሚ ላታገኚው
      ማፍቀርሽን እያወቀ
      በፍቅራችሁ ካልፀደቀ

በቃልሽ ላይ ካላመነ
ጥርጣሬ ከሰፈነ
በመውደድሽ እየኮራ
የውሸት ፍቅር ከሚሰራ
ልብሽ ይቁረጥ እሱን ተይው
ላንች ላይሆን አትወትውችው


━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን


     ,,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,,
                  •═••• •••═•
  
     @yefeker_neger   ,,,,,, @Abdu_ke
━━━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━━━
     
165 viewsAbduke, 18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-27 21:36:01 አትገረም……

አትዘን ወንድሜ!
ነግሬክ ነበረ እኔ አስቀድሜ

አደናቅፎክ ብትወድቅ፤
ባጭሮክ ብትደማ፤
በማንም አትዘን ማንንም አትማ
መንገድ ሁሉ እንቅፋት
በሆነበት አለም
መነሳት ነው እንጂ መውደቅ
ብርቅ አይደለም ።

,,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,,
•═••• •••═•

@yefeker_neger ,,,,,, @Abdu_ke
160 viewsAbduke, 18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-27 13:53:11 ካልመጣህ

ባትመጣም ቅጠረኝ
ሺ ጊዜ ልገተር
ፀሀይ ቆማ ትቅር
ብርሀንም ይፈር
ጨለማ ያሸንፍ

የሰዉ ልጅ ከርታታ
እንደቆመ ይቅር
አንተ 'ስክትመጣ
የፈካዉ ይገርጣ

ግሳንግሳም አለም
የምትመካበት ቴክኖሎጂም ይክተም

ብቻ አንተ እስክትመጣ
ደርቆ መቅረት ይሁን የዚች ዓለም እጣ።

ብልህ ደስ ባለኝ
ጅል ሆኖ ባስቀረኝ

                        የኔ ተናፋቂ................

አንተ ብትመጣም
አንተ ባትመጣም
ደግሞ ብትቀርም
እኔ እንደዉ ለሴኮንድ አንተን አልጠብቅም።

ስለ ፍቅር ብለዉ የቆሙ አዉቃለሁ
ባትመጪም ቅጠሪኝ ሲሉም ሰምቻለሁ
ደግሞም ሲጠብቁ በአይኔ አይቻለሁ

ከዚ ሁሉ መሀል እኔ የተረዳሁት
አፍቃሪዉን ሳይሆን አጠባበቁን ነዉ እነሱ የወደዱት።

አረ እንደዉም ዉዴ..............

በመጠበቅ ብዛት ስሙ የገነነዉ
እሷኑ ቢያሳዩት
       እየጠበቃት ነዉ።

ታዲያ ለምን ብዬ
ብትመጣም ባትመጣም ለምረሳህ ነገር
ሴኮንድ አልጠብቅህ ጥቅር ብለህ ብትቀር።

በትዝታ ወልዴ


     ,,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,,
                  •═••• •••═•
  
     @yefeker_neger    ,,,,,, @Abdu_ke
━━━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━━━
     
44 viewsየፍቅር ነገር, 10:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-26 10:49:11 አ ፈ ቅ ር ሻ ለ ሁ

አ = አንድ ነገር ቀረኝ ከጥፋት መታቀብ
ፈ = ፈልጌው አደለም አላበዛም ሰበብ
ቅ = ቅንነትሽ ደስታ ስሜትን ይስባል
ር = ርሀብን ያስታግሳል ጥምንም ያስቆማል
ሻ = ሻማ ሁነሽኛል በጨለመው ጎኔ
ለ = ለማንም አልፈቅድም እንዲለዩሽ ከ #እኔ
ሁ   = ሁሌም ወድሻለሁ ትናፍቂኛለሽ እስከማይሽ በ #አይኔ

@yefeker_neger
37 viewsAbduke, edited  07:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-26 10:36:56 የፍቅር ነገር :
#ማ_ይንገርሽ_እንደማፈቅርሽ





ብዙ አስብና ማፍቀሬን ልነግርሽ
መኖሬ ላንቺ ነው ወድሻለሁ ልልሽ

ግና ገና ሳይሽ

ያ ሁሉ ስቃየን አይደለም ልናገር
ላንቺ የሆንኩትን እንኳን ልመሰክር

ጉልበቴም ይዝላል 
አካሌም ይደክማል
ልሳኔም ይዘጋል
ልቤም ያው ይፈራል

ታዲያ የኔ ፍቅር

የልቤን ፍላጎት አፌ ካላወራው
ፍቅርሽን መራቤን ልቤ ካላወጣው
ገና ሳይሽ አንቺን ጉልበቴ ከዛለ
አካል እስትንፋሴ ባንቺ ከተከለለ

ማን ይንገርሽ እና እንዴትስ ታቂያለሽ
እስከ ሞቴ ድረስ እኔ እንደምወድሽ
 



     ,,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,,
                  •═••• •••═•
  
     @yefeker_neger   ,,,,,, @Abdu_ke
━━━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━━━
     
43 viewsየፍቅር ነገር, 07:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-25 07:51:00 (( በቃ እወድሻለሁ))
——————
ለምን አትበይኝ ምክኒያት የለኝም፣
ፍቅር ስሜት እንጂ ሰበብ አይመስለኝም፣
ብቻ እወድሻለሁ መዉደዴም ጥልቅ ነዉ፣
ፍቅርሽ ለእኔነቴ የልቤ ዙፋን ነዉ፣
ህያዉ የምሆነዉ አንቺን በማፍቀር ነዉ፣
ቂልነት አይደለም ሁሌ አንቺን ማለቴ፣
ሞኝነት አይሆንም ለፍቅርሽ መክሳቴ፣
ጅልነት አይደለም እራሴን መስጠቴ፣
በቃ አንቺን መዉደድ ነዉ ደስታ መደሰቴ፣
ዉለታን ፈልጌ ዉደጂኝ አላልኩም፣
ፍቅር ሰጠሁ እንጂ ምላሽ አልፈለኩም፣
እንዴት ለምን ካልሺኝ እኔም አላወኩም፣
በቃ እወድሻለሁ ማለቴን አልተዉኩም፣
አዎ እወድሻለሁ፣
አዎ አፈቅርሻለሁ፣
ፍቅርቅር አድርጌሽ በፌሽታ እኖራለሁ፣
ዉድድ አድርጌሽ አንቺን እፎይታ አገኛለሁ፣
ዉዴን እየወደድኩ ሀሴት አደርጋለሁ፣
በፍቅርሽ ዉቅያኖስ ስዋኝ እኖራለሁ፣
አንቺ ካለሽልኝ ህያዉ እሆናለሁ፡፡

ይድረስ ልቤን ለሰረቅሺዉ ሌባ...

✽‌»‌ ✿ »‌✽
የፍቅር ነገር

@yefeker_neger
39 viewsየፍቅር ነገር, 04:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ