Get Mystery Box with random crypto!

(( በቃ እወድሻለሁ)) —————— ለምን አትበይኝ ምክኒያት የለኝም፣ ፍቅር ስሜት እንጂ ሰበብ | ❤ የፍቅር ነገር ❤

(( በቃ እወድሻለሁ))
——————
ለምን አትበይኝ ምክኒያት የለኝም፣
ፍቅር ስሜት እንጂ ሰበብ አይመስለኝም፣
ብቻ እወድሻለሁ መዉደዴም ጥልቅ ነዉ፣
ፍቅርሽ ለእኔነቴ የልቤ ዙፋን ነዉ፣
ህያዉ የምሆነዉ አንቺን በማፍቀር ነዉ፣
ቂልነት አይደለም ሁሌ አንቺን ማለቴ፣
ሞኝነት አይሆንም ለፍቅርሽ መክሳቴ፣
ጅልነት አይደለም እራሴን መስጠቴ፣
በቃ አንቺን መዉደድ ነዉ ደስታ መደሰቴ፣
ዉለታን ፈልጌ ዉደጂኝ አላልኩም፣
ፍቅር ሰጠሁ እንጂ ምላሽ አልፈለኩም፣
እንዴት ለምን ካልሺኝ እኔም አላወኩም፣
በቃ እወድሻለሁ ማለቴን አልተዉኩም፣
አዎ እወድሻለሁ፣
አዎ አፈቅርሻለሁ፣
ፍቅርቅር አድርጌሽ በፌሽታ እኖራለሁ፣
ዉድድ አድርጌሽ አንቺን እፎይታ አገኛለሁ፣
ዉዴን እየወደድኩ ሀሴት አደርጋለሁ፣
በፍቅርሽ ዉቅያኖስ ስዋኝ እኖራለሁ፣
አንቺ ካለሽልኝ ህያዉ እሆናለሁ፡፡

ይድረስ ልቤን ለሰረቅሺዉ ሌባ...

✽‌»‌ ✿ »‌✽
የፍቅር ነገር

@yefeker_neger