Get Mystery Box with random crypto!

የፍቅር ነገር : #ማ_ይንገርሽ_እንደማፈቅርሽ ♡ ♡ ♡ ብዙ አስብና ማፍቀሬን ልነግር | ❤ የፍቅር ነገር ❤

የፍቅር ነገር :
#ማ_ይንገርሽ_እንደማፈቅርሽ





ብዙ አስብና ማፍቀሬን ልነግርሽ
መኖሬ ላንቺ ነው ወድሻለሁ ልልሽ

ግና ገና ሳይሽ

ያ ሁሉ ስቃየን አይደለም ልናገር
ላንቺ የሆንኩትን እንኳን ልመሰክር

ጉልበቴም ይዝላል 
አካሌም ይደክማል
ልሳኔም ይዘጋል
ልቤም ያው ይፈራል

ታዲያ የኔ ፍቅር

የልቤን ፍላጎት አፌ ካላወራው
ፍቅርሽን መራቤን ልቤ ካላወጣው
ገና ሳይሽ አንቺን ጉልበቴ ከዛለ
አካል እስትንፋሴ ባንቺ ከተከለለ

ማን ይንገርሽ እና እንዴትስ ታቂያለሽ
እስከ ሞቴ ድረስ እኔ እንደምወድሽ
 



     ,,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,,
                  •═••• •••═•
  
     @yefeker_neger   ,,,,,, @Abdu_ke
━━━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━━━