Get Mystery Box with random crypto!

🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ wektawi_meraja — 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ wektawi_meraja — 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @wektawi_meraja
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.54K
የሰርጥ መግለጫ

This is national and international News and advertising channel
🇪🇹🇪🇹🇪🇹"ስለኢትዮጲያ ሳትሰማ ያሳለፍከው ቀን እንደባከነ ይቆጠራል" 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
⏭▶️➡️ ሀገራዊና አለም አቀፋዊ ዜናዎችን በፍጥነት ይደርሶታል።🔚

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-09-05 19:30:41 ነሐሴ 30 ቀን 2014 ዓ.ም

የህወሓት የሽብር ሰነድ ሲገለጥ...


አሸባሪው ህወሓት ሀገርን የሚያፈርስበትና የኢትዮጵያን ህዝብ በመበቀል ለመከራ የሚዳርግበት አዲስ ሰነድ አዘጋጅቶ ወደ ተግባር ገብቷል። አሁን እያካሄደ ያለው ውጊያም የዚሁ አካል ነው።

ፅሁፉ ሰፊ ከመሆኑ የተነሳ በማሳጠርና መታየት ያለባቸው ነጥቦች ብቻ ቀርቧል።

ከሰነዱ የተወሰዱ ዋና ወና ሃሳቦች

# ስለ ሰላም አማራጮች ያላቸው አቋም:

• የሰላም አማራጭ በሚል ስትራቴጂው፣ በአንድ በኩል ጊዜ ወስዶ ለአጠቃላይ ዘመቻ ለመዘጋጀት በሌላ በኩል ደግሞ ህወሓት ሰላም ፈላጊ አይደለም ብሎ ለዓለም ማህበረሰብ ጥላቻ ለማሰተጋባት እንዲያግዘው በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት የጀመረው አካሄድ በፍፁም የማያዋጣና የትግራይ ህዝብን ጥቅም የማያስከብር መሆኑን ያስቀምጣል።

• የውስጥ ትግላችን በማገዝ የሚንቀሳቀሱ እንደ ኦነግ የመሳሰሉ አጋሮቻችን እንዲሁም በተለያዬ የዓለም መአዘናት የሚገኙ የትግራይ ዲያስፖራና ዓለም አቀፍ አጋዦቻችንና አጋሮቻችን በዚህ ጊዜ የተሳካ ጥምረት በማድረግq ወደ አዲስ አበባ በምናደርገው እንቅስቃሴና ዘመቻ ከጎናችን መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መሆኑን የትግራይ መንግስት ፕሬዝዳንት ጋር በዝግ ባደረገው ውይይት አረጋግጧል።

የአማራ ሃይል የተመለከተ

• ይሄ ፅንፈኛ የአማራ ተስፋፊ ሃይል በትግራይ ላይ ካሳየው ጫፍ የወጣ ጥላቻ በላይ፣ በክልሉ ያገኘውን ሕዝባዊ ተቀባይነት ሽፋን በማድረግ እና ጠንካራ ቅንጅት በመፍጠር ከአማራ ክልል መንግሥት የሚስተካከል አቅም መፍጠር በመጀመሩ የዐቢይ አስተዳድር በወሰደው ርምጃ በተወሰነ መልኩ መዳከም ታይቶበታል።

አሁንም ግን የዚህ ሃይል አመራሮች በህዝብ ጉያ ተደብቀው ስለሚገኙ ምቹ ሁኔታ ካገኙ ዳግም ሃይል አግኝተው መነሳታቸው አይቀርም። ይህ ሁኔታ የትግራይ ሰራዊት እንደ ጥሩ አጋጣሚ ሊጠቀምበት የሚገባ ሲሆን፣ ይሄ ሃይል ራሱን “ፋኖ” ብሎ በመጥራቱ የተወሰደበት ርምጃ በርከት ያሉ የአማራ ታጋይ ሃይሎች ከዐቢይ ጎን ተሰልፈው ለመንቀሳቀስ ያላቸውን እንዲቀንስ አድርጎታል። ይህንን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ሰፊ የፕሮፓጋንዳ ስራ በመስራት የተፈጠረውን መሻከርና ክፍተት የበለጠ እንዲከር ማድረግ ይገባል።

አፋር ክልልን በተመለከተ

• የዓፋር መንግሥት የእርዳታ ተደራሽነት በመቆጣጠር በየጊዜው ምክንያት የሌለው ግጭቶች በመፍጠር በአዋሳኝ አከባቢዎች በዘላቂነት ሰላም እንዳይሰፍን በማድረግ በአከባቢው የሚኖሩ ተጋሩ በስጋት ውስጥ እንዲሆኑ አድርጓል። በአወል አርባ የሚመራ ግጭት ቀስቃሽ ቡድን ከዐቢይ አስተዳድር በሚሰጠው አድናቆትና ቁጥር የሌለው የትጥቅ እገዛ አይኑ የታወረ፣ ጆሮው የተደፈነ በመሆኑ፣ ትግላችን በሚያግዙ የዓፋር የነፃነት ታጋዮችና ቤተሰቦቻቸው አፈናና ግድያ እየፈፀመባቸው ይገኛል።

ኤርትራን በተመለከተ

• ይሄ ፍፁም አምባገነን የሆነ የኤርትራ መንግሥት፣ አሁንም እንደ ትላንት ዋነኛ የሰላምና የትግራይ ህዝብ ነፃነት ጠላት መሆኑ ዳግም እያሳየ ይገኛል። ይሄ ጨቋኝ መንግሥት ባጭር ጊዜ መፍትሄ ካላገኘ ሕዝባችንን ወደ ማያቋርጥ ጦርነትና መከራ ዳግም ለማስገባት የሚችል ስጋት በውስጡ የያዘ ነው። ከዚህ በተጨማሪ፣ በሶማሌና ኦሮሚያ ክልሎች የሚገኙ የዐቢይ ታማኝ አመራሮችና ደጋፊዎች በክልላቸው ውስጥ በምናደርገው እንቅስቃሴ የሚያግዙንን የውስጥ አካላት እያደኑ ማጥቃት ቀጥለዋል።

ከኦነግ ጋር ያለን ግንኙነት

• ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አመራር ጃል ሚልኬሳ ጋር በሚስጢር ባደረግነው ውይይት፣ ባጭር ጊዜ አመራራቸው ወደሚመች አከባቢ ወይም ወደ አጎራባች ሃገሮች ስልታዊ ማፈግፈግ የሚያደርጉበት ሁኔታ እንዲመቻች፣ እንዲሁም የመከላከል አቅምና ዝግጁነት የሌላቸው የሰራዊቱ አባላት ከተቻለ ዩኒፎርማቸውን ጥለው ወደ ሕዝባቸው እንዲቀላቀሉና እንዲደበቁ ካልተቻለም ለመንግሥት ሃይሎች እጃቸውን መስጠት የተሻለ አማራጭ እንደሆነ አንስቶ ነበር።

• በወለጋ ያለው ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አመራር መካከል ጃል ራሣና ጃል ቃንቄ በፋሺስት ዐቢይ ከተከፈተባቸው ከበባ ለመውጣት አስቸኳይ ዘዴ ዘይደው መመርያ በመስጠት ወደሚመች ምስጢራዊ ቦታዎች እንዲንቀሳቀሱ የተደረገው ሙከራ የተሳካ ነው። በዚህ አግባብ በአንዳንድ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አመራሮች መካከል የትግል ስልት ልዩነት ቢኖርም በአስቸጋሪ ሁኔታ ሁነንም የመረጃ ልውውጣችን እና መተጋገዛችን የሚቀጥል ይሆናል። የዚህ ግንኙነት ዋነኛ መሰረት፣ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ለአዲስ አበባ ካላቸው ቅርበትና ለሚታሰበው ዘመቻ ከፍተኛ ትግል በማድረግ ድል ሊያስመዘግቡ የሚችሉ በመሆናቸው ላይ ካለን መተማመን የሚመነጭ ነው።

• ይሁን እንጂ አሁንም የፋሺስት ዐቢይ አህመድና ሽመልስ አብዲሳን አገዛዝ ሽባ በማድረግ ወደ አዲስ አበባ የሚደረገው የመጨረሻ የትግል ምዕራፍ ላይ የቅርብ አጋዦች እነዚህ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በመሆናቸው ሊስተካከሉ የሚገባቸው እና ባለፈው ግምገማ የታዩ ክፍተቶች ታርመው ወደ መጨረሻው ምዕራፍ እንዲዘጋጁ ማድረግ አስፈላጊ ነው።

ይቀጥላል ...

የኢትዮጵያ መከላክያ ሰራዊት
ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
https://t.me/Merja01
2.1K views16:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 16:02:55
ጠላት በአድርቃይ ከዓመት በላይ ሲጠቀምበት የነበረ ምሽግ ነው።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
https://t.me/Merja01
2.7K views13:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 15:17:31 ህወሓት ዳግም ጦርነት መክፈቱ በትግራይ ህዝብ ጫንቃ ላይ ቆሞ የስልጣን እድሜውን ለማራዘም መሆኑን ምርኮኞች አጋለጡ

አሸባሪው ህወሓት የቀረበለትን የሰላም አማራጭ ረግጦ ዳግም ጦርነት መክፈቱ በትግራይ ህዝብ ጫንቃ ላይ ቆሞ የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ነው ሲሉ በተለያዩ ግንባሮች እጃቸውን ለጀግናው የሃገር መከላከያ ሰራዊት የሰጡ ምርኮኞች አጋለጡ፡፡

ምርኮኞቹ እንደተናገሩት የትግራይን ህጻናት ሳይቀር ወደ ጦር ግንባር እየማገደ የሚገኘው አሸባሪው ህወሓት በሃሰተኛ ትርክት የትግራይን ወጣት ራሱ ወደለኮሰው ጦርነት እየማገደ ክልሉን ትውልድ አልባ የማድረግ እኩይ አላማውን ገፍቶበታል።
ይህ ተግባሩ የሽብር ቡድኑን የባንዳነት ትክክለኛ ባህሪ በተጨባጭ እያረጋገጠ መሆኑንም ነው ምርኮኞቹ የተናገሩት።
ምርኮኞቹ አሸባሪው የህወሓት ቡድን በትግራይ ህዝብና ህፃናት ላይ እየፈፀመ ያለውን ስቃይና እንግልት በመቃወም በፕሮፖጋንዳ ተታለው ከገቡበት ጦርነት በመውጣት ለጀግናው የሃገር መከላከያ ሰራዊት እጃቸውን መስጠታቸውን ገልፀዋል፡፡
የሰላም አማራጭ በሰፊው ቀርቦለት ጦርነትን መርጦ ህጻናትን ሳይቀር ወደ ጦርነት እየማገደ ያለው የሽብር ቡድኑ ህወሓት የራሱን የስልጣን ላይ ቆይታ ለማራዘም ትግራይ ላይ ምንም አይነት ጥፋት ከመፈጸም ወደኋላ እንደማይመለስ ምርኮኞቹ አረጋግጠዋል።
“የትግራይ ከፍታ የሚረጋገጠው በኢትዮጵያ መቃብር ላይ ነው” በሚል ቀቢፀ ተስፋ በመነሳሳት ኢትዮጵያን ለማፍረስና ህዝቦቿን ለመበተን ዳግም ጦርነት ቢከፍትም አላማ ቢስ ለሆነው የሽብር ቡድኑ አላማ መሰለፍ ከንቱ በመሆኑ እጃቸውን ለመስጠት እንዳስገደዳቸው ተናግረዋል።
በቡድኑ የውሸት ወሬና ፕሮፓጋንዳ ተታለው በመሰለፍ ለፈፀሙት ጥፋት በመፀፀት ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ፤ ለመከላከያ ሰራዊቱና ለሌሎች የፀጥታ ኃይል ይቅርታ ጠይቀው የህወሓት የሽብር ቡድንን ከንቱ ራስ ወዳድ አላማ ለማስፈፀም የተሰለፉ የትግራይ ወጣቶችም የሚጓዙበት መንገድ ፈጽሞ እንደማያዋጣ ተረድተው ፈጥነው እንዲነቁ ምርኮኞቹ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ምርኮኞቹ በመከላከያ ሰራዊትና በሌሎች የፀጥታ ሃይሎች ለተደረገላቸው መልካም አቀባበልና እንክብካቤ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ ከጦርነት ኪሳራ እንጂ ትርፍ እንዳማይገኝ የገለፁት ምርኮኞቹ፤ አሸባሪ ቡድን ለዳግም እልቂት የከፈተውን ወረራ በማውገዝ ወደ ሰላም እንዲመጣ የትግራይ ህዝብ፤ ወጣቶችና ልዩ ኃይል አባላት ጫና መፍጠር እንደሚገባቸው ጥሪ ማቅረባቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
https://t.me/Merja01
2.8K views12:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 15:16:55
2.7K views12:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 07:12:01 ልዩ መረጃ

ከህወሓት ወያኔ ጉጁሌ ጀሌ ታጣቂ ነጻ የተደረጉ ቦታዎች

ምዕራብ ግንባር፦
1)ፀልሞይ
2)ማይሀንሲ
3)አዳሀመዳይ
4)ማይጣሳ
5)ደደቢት ናቸው።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
https://t.me/Merja01
1.5K views04:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 19:44:23 ሰበር ዜና

ጀግናው ጥምር ሀይላችን በአዲርቃይ ግንባር ከፍተኛ ድል እያገኘ ነው


ጠላት ለበርካታ ወራት በወረራ ይዟቸው የነበሩ የአድርቃይ አካባቢዎች ነፃ እየወጡ ነው ። የጥምር ጦር ሀይሉን ብቃት እና የሰሜን ጎንደር ህዝብ ጀግንነት ከፍ ያደረገ ጠላት አማራን የማዋረድና ኢትዮጵያን የማፈራረስ ህልሙን የመከነበት ድል ነው።

ጠላት ለረጅም ጊዜ ይዟቸው የቆያቸውን ተናፋቂዎቹ የቱሪስት መዳራሻ የነበሩት የሃገራችን ምልክት የሆኑት የሃዋዛ ተራሮችንና የአዝማች ያዕቆብ እምብርቷን መኒ ወንበርጌን ሙሉ በሙሉ ጥምር ጦራችን ተቆጣጥሯል።

ጥምር ሀይሉ ጠላትን ለወራት ቀን ከሌት የሰራውን ኮንክሪት ምሽግ ደረማምሶ ነፃ አውጥቶ ወደ አዲአርቃይ አናትና ማይሊሃም አቅጣጭ እየገሰገሰ ይገኛል!!

ድሉ ይቀጥላል። ህዝባዊ ድጋፉ ይቀጥል።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
https://t.me/Merja01
2.8K views16:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 19:18:32 #ሰቆጣ

በሰቆጣ ከተማና አካባቢው ከ50 በላይ የአሸባሪው ሕወሓት ሰርጎ ገቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን የዋግኽምራ ብሔረሰብ ዋና አስተዳዳሪ ስቡህ ገበያው ገልጸዋል።

ሰርጎ ገቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በሰቆጣ ከተማ የሽብር ተግባር ሲፈጽሙ በሕዝቡና በጸጥታ ኃይሉ ስለተደረሰባቸው መሆኑን አሚኮ ዘግቧል፡፡

ዋና አስተዳዳሪው የዋግኽምራ ሕዝብ በአሸባሪው ሕወሓት የተፈጸመበትን ወረራ ለመከላከል እያደረገ ያለውን ሁሉን አቀፍ ትግልና ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
https://t.me/Merja01
2.9K views16:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 12:25:04 አሸባሪው ህወሀት በቆቦ ህፃናትና አዛውንቶች ላይ በከባድ መሳሪያ ጥቃት ፈፅሟል

አሸባሪው የህወሀት ቡድን የሽብር ቡድኑ ነሐሴ 19 ቀን 2014 በቆቦ ወረዳ ህፃናትና አዛውንቶች ላይ በከባድ መሳሪያ ጥቃት መፈፀሙን የጥቃቱ ተጎጂዎችና ቤተሰቦቻቸው ገለጹ።
ንፁሃንን በመጉዳት የተካነው የሽብር ቡድኑ በቆቦ ወረዳ የአርሶ አደሮችን ቤት እና ከብቶችን በመጠበቅ ላይ የነበሩ ታዳጊዎችን በመድፍ በመደብደብ በህፃናትና አዛውንቶች ላይ ጉዳት አድርሷል።

"እኛ አርሶ አደሮች ነን፤ የሽብር ቡድኑ በማዕበል ወረራ ፈፅሞ ዘረፋ መፈጸሙ ሳያንስ በከባድ መሳሪያ ደብድቦናል" ይላሉ።
የሽብር ቡድኑ ያደረሰባቸው ጉዳት መቼም የማይሽር ጠባሳ መሆኑን የገለጹት ተጎጂዎቹ፤ በአሁኑ ወቅት ተገቢ ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ጠቅሰዋል።

ሆኖም በሽብር ቡድኑ ወረራ ውስጥ ያሉ ቤተሰቦቻቸውን በህይወት የመኖርና አለመኖር ሁኔታ አለማወቃቸው በእጅጉ እንዳሳሰባቸውም ነው የተናገሩት።
የሽብር ቡድኑ ለሰላም የተሰጠውን እድል ትቶ ጦርነት በከፈተባቸው የአማራ ክልልና አፋር ክልል ወረዳዎች በንፁሃን ዜጎች ላይ ጥቃት በማድረስ የሽብር ተግባር መፈጸሙን አሁንም መቀጠሉን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
https://t.me/Merja01
3.4K views09:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 08:26:03 ለገሐር አካባቢ በሚገኝ ህንጻ ምድር ቤት ውስጥ የአንድ ግለሰብ ህይወት አልፎ ተገኘ

በአዲስ አበባ በዛሬው እለት ከጠዋቱ 3 ሰዓት 30 ደቂቃ ላይ ለገሐር አካባቢ በአንድ ህንጻ ምድር ቤት ስር የተጠራቀመ ውሃ ውስጥ በስፋራው የሚሰራ አንድ ግለሰብ ህይወቱ አልፎ መገኘቱን የእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት ህይወቱ ያለፈዉ ግለሰብ የ32 ዓመት ወጣት ሲሆን እየተገነባ ባለዉ ህንጻ  ላይ ሰራተኞችን ቀጥሮ የሚያሰራ ከፍተኛ ባለሙያ ነበር። ትላንት ቀን ላይ በድንገት ከስራ ቦታዉ በመጥፋቱና ዛሬም ስራ ላይ ባለመገኘቱ ጥርጣሬ የገባቸዉ ሰራተኞች ዛሬ ለፖሊስ ሪፖርት አድርገዋል።

ፖሊስ በመጠራጠር አስከሬኑ እንዲፈለግ ለኮሚሽን መስሪያ ቤት ሪፖርት በማድረጉ አስከሬኑ በህንጻዉ የተለያዩ ስፍራዎች ሲፈለግ ቆይቶ በህንጻዉ ቤዝመንት በተጠራቀመ ዉሀ ዉስጥ ሊገኝ ስለመቻሉን ተገልፃል።

አስከሬኑን የእሳት አደጋ ባለሞያዎችና በቦታዉ ከነበሩ ሰራተኞችና የፖሊስ አባላት ጋር  በመተባበር አዉጥተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል።ፖሊስ ጉዳዩን ለማጣራት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አዉሎ ምርመራ እያደረገ እንደሚገኝ አቶ ንጋቱ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
https://t.me/Merja01
3.5K views05:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 22:38:08
#UPDATE

ሸዋሮቢት !

በሸዋሮቢት በተላለፈው የሰዓት ገደብ ክልከላዎች ላይ ማሻሸያ መደረጉን የከተማ አስተዳደሩ ዛሬ ምሽት አሳውቋል።

በዚህም መሰረት ፦

- ለባጃጅና ለሞተር ሳይክል የተቀመጠው የስአት ገደብ እስከ ምሽቱ ሁለት ሰአት የነበረው ወደ አንድ ሰአት ፤

- ለሰው እና ለመጠጥ ቤቶችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የተቀመጠው የሰአት ገደብ ተሻሽሎ እስከ ምሽቱ አንድ ሰአት ተደርጓል።

በሌላ በኩል ፤ የከተማው አስተዳደር የከተማውን ከንቲባ የገደሉ ታጣቂዎችን በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋል ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጾ በዚህ ሂደት አንዳንድ ግለሰቦች ጉዳዪን ወደ ሌላ ነገር ለመቀየር ጥረት እያደረጉ ነው ብሏል።

ከተማው " ወደ ሌላ ነገር " ያለውን ጉዳይ በግልፅ ያላብራራ ቢሆንም የከተማው ነዋሪዎች ጉዳዩን በሰከነ መንፈስ እንዲያዩት እና ህግን ለማስከበር በሚደረግ እንቅስቃሴ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቋል።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
https://t.me/Merja01
3.5K views19:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ