Get Mystery Box with random crypto!

ለገሐር አካባቢ በሚገኝ ህንጻ ምድር ቤት ውስጥ የአንድ ግለሰብ ህይወት አልፎ ተገኘ በአዲስ አበ | 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

ለገሐር አካባቢ በሚገኝ ህንጻ ምድር ቤት ውስጥ የአንድ ግለሰብ ህይወት አልፎ ተገኘ

በአዲስ አበባ በዛሬው እለት ከጠዋቱ 3 ሰዓት 30 ደቂቃ ላይ ለገሐር አካባቢ በአንድ ህንጻ ምድር ቤት ስር የተጠራቀመ ውሃ ውስጥ በስፋራው የሚሰራ አንድ ግለሰብ ህይወቱ አልፎ መገኘቱን የእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት ህይወቱ ያለፈዉ ግለሰብ የ32 ዓመት ወጣት ሲሆን እየተገነባ ባለዉ ህንጻ  ላይ ሰራተኞችን ቀጥሮ የሚያሰራ ከፍተኛ ባለሙያ ነበር። ትላንት ቀን ላይ በድንገት ከስራ ቦታዉ በመጥፋቱና ዛሬም ስራ ላይ ባለመገኘቱ ጥርጣሬ የገባቸዉ ሰራተኞች ዛሬ ለፖሊስ ሪፖርት አድርገዋል።

ፖሊስ በመጠራጠር አስከሬኑ እንዲፈለግ ለኮሚሽን መስሪያ ቤት ሪፖርት በማድረጉ አስከሬኑ በህንጻዉ የተለያዩ ስፍራዎች ሲፈለግ ቆይቶ በህንጻዉ ቤዝመንት በተጠራቀመ ዉሀ ዉስጥ ሊገኝ ስለመቻሉን ተገልፃል።

አስከሬኑን የእሳት አደጋ ባለሞያዎችና በቦታዉ ከነበሩ ሰራተኞችና የፖሊስ አባላት ጋር  በመተባበር አዉጥተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል።ፖሊስ ጉዳዩን ለማጣራት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አዉሎ ምርመራ እያደረገ እንደሚገኝ አቶ ንጋቱ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
https://t.me/Merja01