Get Mystery Box with random crypto!

አሸባሪው ህወሀት በቆቦ ህፃናትና አዛውንቶች ላይ በከባድ መሳሪያ ጥቃት ፈፅሟል አሸባሪው የህወሀ | 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

አሸባሪው ህወሀት በቆቦ ህፃናትና አዛውንቶች ላይ በከባድ መሳሪያ ጥቃት ፈፅሟል

አሸባሪው የህወሀት ቡድን የሽብር ቡድኑ ነሐሴ 19 ቀን 2014 በቆቦ ወረዳ ህፃናትና አዛውንቶች ላይ በከባድ መሳሪያ ጥቃት መፈፀሙን የጥቃቱ ተጎጂዎችና ቤተሰቦቻቸው ገለጹ።
ንፁሃንን በመጉዳት የተካነው የሽብር ቡድኑ በቆቦ ወረዳ የአርሶ አደሮችን ቤት እና ከብቶችን በመጠበቅ ላይ የነበሩ ታዳጊዎችን በመድፍ በመደብደብ በህፃናትና አዛውንቶች ላይ ጉዳት አድርሷል።

"እኛ አርሶ አደሮች ነን፤ የሽብር ቡድኑ በማዕበል ወረራ ፈፅሞ ዘረፋ መፈጸሙ ሳያንስ በከባድ መሳሪያ ደብድቦናል" ይላሉ።
የሽብር ቡድኑ ያደረሰባቸው ጉዳት መቼም የማይሽር ጠባሳ መሆኑን የገለጹት ተጎጂዎቹ፤ በአሁኑ ወቅት ተገቢ ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ጠቅሰዋል።

ሆኖም በሽብር ቡድኑ ወረራ ውስጥ ያሉ ቤተሰቦቻቸውን በህይወት የመኖርና አለመኖር ሁኔታ አለማወቃቸው በእጅጉ እንዳሳሰባቸውም ነው የተናገሩት።
የሽብር ቡድኑ ለሰላም የተሰጠውን እድል ትቶ ጦርነት በከፈተባቸው የአማራ ክልልና አፋር ክልል ወረዳዎች በንፁሃን ዜጎች ላይ ጥቃት በማድረስ የሽብር ተግባር መፈጸሙን አሁንም መቀጠሉን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
https://t.me/Merja01