Get Mystery Box with random crypto!

TRIAD HEALTH System / ትሪያድ ሐልዝ ሲስተም

የቴሌግራም ቻናል አርማ triadhealth1 — TRIAD HEALTH System / ትሪያድ ሐልዝ ሲስተም T
የቴሌግራም ቻናል አርማ triadhealth1 — TRIAD HEALTH System / ትሪያድ ሐልዝ ሲስተም
የሰርጥ አድራሻ: @triadhealth1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 428
የሰርጥ መግለጫ

የዚህ ቻናል ዋናው አላማ፣ ለህብረተሰቡ አስፈላጊውን የህክምና አስተምሮት እና መልእክት ማስተላለፍ ነው።
Group https://t.me/triadhealth
Channel https://t.me/triadhealth1

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-30 23:56:43
ውድ የሀገሬ ልጆች ፤ ወቅቱ የክረምት ወቅት እንደመቃረቡ መጠን ከፍተኛ ቅዝቃዜና ብርድ እንዳለ ይታወቃል።
ይህን ብርድ ለመከላከል ሲባል እቤት ውስጥ ከሰል የማቀጣጠልና የቤቱን ሙቀት ለመጨመረ የሚደረግ ሂደት አለ።
ሆኖም በቂ አየር በማይገባበተት፣ መስኮትና በር በተዘጋበት ቤት ውስጥ የሚቀጣጠልና የሚጤሰ ከሰል ለCarbon monoxide Poisoning ስለሚያጋልጥ በዚህም የተነሳ ለከፍተኛና አጣዳፊ የአየር እጥረትና ለሞት እየተጋለጡ እንዲሁም በመኝታቸው ላይ ሞተው እየተገኙ ያሉ ዜጎች እየተበራከቱ በመሆኑ ጥንቃቄ እንድታደርጉ በአክብሮት አሳስባለሁ።
ጥንቃቄ
1. ከሰል በሚያቀጣጥሉበት ወቅት ቤት ውስጥ በቂ አየር እንደሚገባ ያረጋግጡ
2. ከመተኛትዎ በፊት የተቀጣጠለ ከሰል ካለ ማጥፋትዎን አይዘንጉ!
3. ከሰል በተቀጣጠለበት ቤት ውስጥ ከፍተኛ ራስ ምታት፣ ማቅለሽለሽ፣ የድካም ስሜትና መልፈስፈስ ያጋጠመው ሰው ካለ በቂ አየር እንዲያገኙ ያግዟቸው፣ ራሱን የሳተ ከሆነ በፍጥነት ወደ አቅራቢያው የጤና ተቋም ያድርሱ።
ሁሌም ሠላም ሁኑ!
ዶ/ር ብዙአየሁ ፤ ጠቅላላ ሀኪም
427 views20:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 10:18:20 የአፍንጫ አለርጂ (Allergic rhinitis)

የአፍንጫ አለርጂ/ አለርጂክ ሪሄናይትስ የመተንፈሻ አካል አለርጂ ሲሆን ይህ ችግር እንደ የአፍንጫ ፈሳሽ መዝረብረብ፣ የአይን መብላት/ማሳከክ፣ የአፍንጫ ማፈን/መጠቅጠቅ ማስነጠስንና የሳይነስ ቦታዎች ላይ መክበድ የመሰሳሉትን ጉንፋን መሰል ምልክቶች የሚያመጣ የህመም አይነት ነዉ፡፡
ይህ ህመም የሚከሰተው አለርጂን ሊያመጡ በሚችሉ በቤት ዉስጥና ከቤት ዉጪ ያሉ እንደ ብናኝ፣ አቧራ፣ ግነት ያላቸው ጥሩም ይሁን መጥፎ ጠረኖች እንዲሁም የቤት ውስጥ እንደ እንስሳት አይነምድር ላሉ ነገሮች በምንጋለጥበት ወቅት ሰዉነታችን የሚያሳያዉ ያልተገባ ምላሽ በሚኖርበት ወቅት ነዉ፡፡

የህመሙ ምልክቶች ምንድናቸው?

ቅድሚያ የሚታዩ ምልክቶች ፦
የአፍንጫ፣የአፍ አካባቢ፣የጉሮሮ፣የቆዳ ወይም የሌሎች የአካል ክፍሎች መቆጥቆጥ
ለማሽተት መቸገር
ለረጅም ጊዜ የማያቋርት ቀጭን ንፍጥ
ማስነጠስ
የአይን ማልቀስ

በሂደት የሚታዩ
ምልክቶች ፦
የአፍንጫ መደፈን
ሳል
የጆሮ መደፈን
የጉሮሮ ህመም
ጥቁርና ክብ ቅርፅ ያለዉ ምልክት በአይን ላይ መታየት
የአይን ማበጥ
የራስ ምታት ወ.ዘ.ተ.

የአፍንጫ አለርጂ መንስኤዎች
የእጽዋት ወይም የአበባ ሽታ
የሽቶ፣ ሳሙና፣ ሰንደል ወይም እጣን አይነት ሽታዎች

የአመቱ ወቅትና የአፍንጫ አለርጂ
የአፍንጫ አለርጂ የሚነሳበት/የሚባባስበት ወቅት በአመት ዉስጥ የሚለያይ ሲሆን በተለይ ዛፎች፣ ሳርና የተለያዩ አበቦች በሚያብቡት ወቅት ይብሳል በተጨማሪም ብርድ እና ቅዝቃዜ የሚበረታበት ወቅትም ላይ ችግሮቹ ሲባባሱ ይስተዋላል፡፡ በቤትዎ ዉስጥ ያሉና አለርጂን ሊያስነሱ የሚችሉ እንደ የምንጣፍም ይሁን ከሌላ ነገሮች የሚነሱ አቧራና ቡናኝ፣ በረሮ፣ ሻጋት፣ የቤት እንስሳት አይነምድር ሁሌ ካለ አመቱን በሙሉ የህመሙ ምልክቶች ላይጠፋ ይችለል/ሊኖሮት ይችላል፡፡
ለአፍንጫ አለርጂ

ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ነገሮች
አስም ወይም ሌላ የአለርጂ ህመም ካሎት
በቤተሰብ ዉስጥ መሰል ህመም ካለ (አስም ወይም ሌላ የአለርጂ ህመም ካለ)
የሚሰሩበት ወይም የሚኖሩበት አካባቢ ብዙዉን ጊዜ ለአለርጂኖች (አለርጂን ሊያስነሱ ለሚችሉ ነገሮች) የሚያጋልጦ ከሆነ
ለአፍንጫ አለርጂ ሊደረግ የሚችል ህክምና ምንድነው?
ለአፍንጫ አለርጂ ሊደረግ ከሚችሉ ህክምናዎች ዋናዉ ለአለርጂ ሊያጋልጦት ከሚችሉ ነገሮች እራስን መከላከል መቻል ነዉ፡፡ ነገር ግን ሁልጊዜ እራስን ተከላክሎ መቆየት ስለማይቻል በጤና ተቋሟት የሚታዘዙ የአለርጂ መዳኒቶች ይውሰዱ፡፡
ቤትዎን በእንፋሎት ያጥኑት
እንደ ሲጋራ ያሉ የሚረብሹ ነገሮችነን መራቅ
በቂ ውሃ መጠጣትና የአፍንጫ እስፕሬዎች መጠቀም
ሌሎች የተለዩ ምክንቶች ካሉ ማከም
አበቦች በሚያብቡበት ወቅት በርንና መስኮትን መዝጋት
የሚቻል ከሆነ የአየር ማፅጃ በመኪናዎ ዉስጥ መጠቀም
ጠዋት እና ምሽት ላይ የሚሞቅ ነገር መልበስ
በጣም ነፋሻማና ደረቅ አየር በሚበዛበት ሰዓት ከቤት ያለመዉጣት
በአትክልት/ጋርደን አካባቢ ስራ የሚሰሩ ከሆነ የአፍንጫ ማስክ መጠቀም(አፍንጫን
መሸፈን) ቡናኝን ለመከላከል
በረሮዎች ሊገቡበትና ሊራቡበት የሚችሉ ቀዳዳዎችን መድፈን
የወዳደቁ የምግብ ተርፍራፊዎችን ከዕቃና ከወለል ላይ ማፅዳት
ምግቦችን በሚከደን እቃ ዉስጥ ማስቀመጥ
የበረሮ ማጥፊያ መድሃኒቶችን መጠቀም
ከተቻለ የቤት እንስሳት በቤት ዉስጥ እንዳይኖሩ ማድረግ
61 views07:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 17:17:06
59 views14:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 17:16:58 ሙዝ ለጤና የሚኖረው 15 ጠቀሜታዎች

1. ጥርስን ያነጣል!!
ጥርስዎን ሁልጊዜ ሲቦርሹ ለሁለት ደቂቃ ያህል በሙዝ ልጣጭ/ልጫ ጥርስዎን ይሹት ከዚያም አስደናቂ ለውጥ ያገኙበታል።

2. በተለያዩ ነፍሳቶች ሲነከሱ ቁስልዎን ያስታግስልዎታል!!
ነፍሳቱ የነከስዎት ቦታ ላይ በሙዝ ልጫ በማሸት የሚኖረውን እብጠትና ህመም መቀነስ ይቻላል።

3. የተጎዳን የሰውነት ቆዳን ያስተካክላል!!
ሙዝ የተበላሸ ወይም የተጐዳ የፊት ቆዳን በሚያምር አዲስ የፊት ቆዳ የመተካት ምትሀታዊ ሀይል አለው።

4. ለእፅዋት ማዳበሪያነት ያገለግላል!!
ደረቅ የሙዝ ልጫ ተወዳዳሪ የሌለው የአትክልትና እፅዋት ማዳበሪያ ነው።

5. የፊት መሸብሸብ ወይም መጨማደድን ይከላከላል!!
ሙዝ ከፍተኛ የክሬምና የተፈጥሮ ማር ካላቸው ምግቦች የሚመደብ ሲሆን አንዳንድ ሴቶች የፊት መሸብሸብን ለመከላከል ሲሉ ከሙዝ የተሰሩ የፊት ክሬሞችን በሳምንት ለ3 ጊዜ ያህል ይጠቀማሉ።

6. የቆዳ መሰንጠቅን ይከላከላል!!
የሰውነት ቆዳዎ እያሳከክዎትና እየተሰነጣጠቀ ተቸግረዋል? ህመምዎ(ችግርዎ) ይገባኛል፤በጣም እድለኛ ነዎት!! እንደዚህ ያድርጉ የተሰነጠቀውን የሰውነትን ቆዳ በሙዝ ልጫ(ልጣጭ) ይሹት እንደዚያ ሲያደርጉ በሙዙ ልጫ ላይ ያለው ተፈጥሮአዊ ኢንዛይም በተሰነጠቀው ቆዳዎ ላይ በመግባት ስራውን ይሰራል ማለት ነው።

7. ጥሩ የአይስክሬም መስሪያ ነው!!
በጣም ጣፋጭ ነገር ይወዳሉ? ነገር ግን ለማዘጋጀት ጊዜ ወይም ገንዘብ የለዎትም? እንግዲውስ እንዲህ ያድርጉ በጣም የቀዘቀዘ ሙዝ ቆራርጠው ወደ አይስክሬም መስሪያ ያስገቡት ከዚያም አስደናቂ ጣዕም ያለው አይስክሬም ይመገባሉ።

8. ክንታሮትን ያድናል!!
ሙዝ በፓታሲየም የበለጸገ ነው። ይህ ንጥረ ነገር ክንታሮትን የማዳን አቅም አለው ስለዚህ ሙዝ ተፈጥሮአዊ የክንታሮት መድሀኒት ሆኖ ያገለግላል።

9. ሰውነታችን በስለት ሲቆረጥ ወይም ሲያብጥ የማዳን ሀይል አለው!!
ሙዝ ሰውነታችን በግጭት ወይም በሌላ ምክንያት ሲያብጥ ወይም ስለት ነገር ሲቆርጠን በውስጡ ፓታሲየም የተባለ ንጥረ ነገር ስላለው ሰውነታችን ለማገገም የሚያደርገውን ሂደት ያግዛል ወይም ያፋጥነዋል።

10. ሙዝ ወፎችንና ቢራቢሮዎችን የመሣብ ሀይል አለው!!
ወፎችንና ቢራቢሮዎች ልክ እንደሠው ልጅ ሁሉ የሙዝን ቃና በጣም ይወዱታል።ስለዚህ ሙዝ ይህን ያህል የመሣብ አቅም ስላለው ወፎችን የመመልከት ፍላጎት ካለዎት በአካባቢዎ ሙዝ ይጣሉላቸው ከዚያም በአስደናቂው ቃና ወደርስዎ ይስባሉ።

11. የቆዳ ውጤቶችንና የብር ጌጣጌጦችን (silver) ያፀዳል!!
የቆዳ ዉጤቶችንና ከብር የተሰሩ ጌጣጌጦችን ለማፅዳት ለመርዛማ ኬሚካሎችን ለመግዛት ገንዘብዎን አያጥፉ በምትኩ በሙዝ ልጫ(ልጣጭ) በደንብ ካሹት በኋላ በጨርቅ ይጥረጉት።

12. ሙዝ በፀረ-ተባይ መድሀኒትነት ያገለግላል!!
ማንም ሰው ቢሆን እፅዋት ተጎድተው ማየት አይፈልግም!! የሙዝ ልጫን ቆራርጠው በእፅዋቱ አካባቢ ከ6-7 ሳ.ሜ አርቀው ይቅበሩዋቸው ከጥቂት ጊዜ በኋላ በአካሎቹ ላይ ያሉት ተባዮች ይሞታሉ።

13.የውሻን በሽታ ይከላከላል!!
በፍቅር የሚወድዎትን ውሻዎ በቀላሉ ጤናውን ይጠብቅልዎታል።

14. ውሀን ያጣራል!!
የተለያዮ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የሙዝ ልጫ/ልጣጭ በወንዝ ውሀ ውስጥ የሚገኙትን መርዛማ ንጥረ ነገሮችን መጦ የመያዝ አቅም አለው።

15. በሽታ የመከላከል አቅምዎን ይጨምራል።
64 views14:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-20 15:42:52
237 views12:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-20 15:42:44 #የዴፖፕሮቨራ# ጥቅም እና ጉዳት

#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን
ትሪያድ ሐልዝ
#በመርፌ መልክ የሚሰጥ የወሊድ መከላከያ ነው፡፡ ይህ የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴ በአስተማማኝነቱ እና አዋጭነቱ ይታወቃል፡፡
በየ 3 ወሩ በህክምና ባለሙያ በመርፌ ተወግቶ የሚሰጥ ነዉ፡፡
# ጥቅም
ከፍተኛ ውጤታማነት ያለው ወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴ ነው
ኢስትሮጂን ሆረሞን የማይጨምር ዘዴ ነው
የደም ዑደት ችግር አያስከትልም
ከማህጸንና ከእንቁላል ማህደር ካንሰር የመከላከል ሁኔታ አለው
ጡት የምታጠባ ሴት በወተቱ መጠንና ይዞታ የሚያመጣው ለውጥ አይኖርም
በየቀኑ መከታተል የሚፈልግ አይደለም
ለማስገባትም ሆነ ለማስወጣት ቀዶ ጥገና የሚፈልግ አይደለም
# ጉዳት
በአማካይ ከ 6 እስከ 12 ወር ለሚያክል ጊዜ መርፌዉን አቋርጠው ለመውለድ በሚወሰንበት ጊዜ የመዘግየት ሁኔታ ያሰከትላል
የወር አበባ ቋሚ ጊዜ አለመያዝ
የጡት ካንሰር
ክብደት መቀነስ
ድብርት
t.me/triadhealth1
192 views12:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-16 12:18:20 Hepatitis b ህክምና ለተወለደ ህፃን

ከ HbsAg Positive እናት የተወለደ ህፃን በተወለደ ከ12 እስከ 24 ሰዓት ውስጥ መውሰድ ያለበት መድሀኒቶች ይኖራሉ። እነኝህም Hepatitis b vaccine(የሄፓታይተስ b ክትባት) እና Hepatitis b immunoglobulins (የሄፓታይተስ b ኢሚውኖግሎቡሊን) ተብለው ይታወቃሉ ።

አሰጣጥ

Hepatitis b vaccine(የሄፓታይተስ b ክትባት)

የመጀመሪያው ክትባት

ህፃኑ ኪሎው ከ 2000ግም በላይ ከሆነ
⁃ 0.5ML IM within 24 hr
ህፃኑ ኪሎው ከ 2000ግም በታች ከሆነ
⁃ 0.5ML IM በተወለደ በ1 ወሩ ወይም እናትየው ከሆስፒታል ወደ ቤት በምትሸኝ ጊዜ መውሰድ ይኖርበታል።

እናትየው በhepatitis ቫይረስ መጠቃቷ ወይም አለመጠቃቷ የማይታወቅ እና ማረጋገጥ ካልተቻለ ግን

ህፃኑ ኪሎው ከ 2000ግም በላይ ከሆነ
⁃ 0.5ML IM within 24 hr
ህፃኑ ኪሎው ከ 2000ግም በታች ከሆነ
⁃ የእናትየው የhepatitis ሁኔታ እስኪረጋገጥ መጠበቅ

ሁለተኛው ክትባት ህፃኑ አንደኛውን ከወሰደ በ1 ወሩ መውሰድ ይኖርበታል

ሶስተኛውን ክትባት ህፃኑ ሁለተኛውን ከወሰደ ከ5ወር በውሀላ መውሰድ ይገባዋል።

Hepatitis b immunoglobulins (የሄፓታይተስ b ኢሚውኖግሎቡሊን)

⁃ 0.5ML IM within 12 hrs after birth
ህፃኑ ክትባቱን ካልተከተበ እና ማግኘት ካልቻለ Hepatitis b immunoglobulinኑን በ 3 እና 6 ወር ላይ ደግሞ መውሰድ ይገባዋል።
213 views09:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-10 20:06:10 የጆሮ ኢንፌክሽን (otitis media)


የጆሮ እንፌክሽን በብዛት በባክቴሪያ ወይም በቫይረስ ምክንያት የሚከሰት የህመም አይነት ነዉ፡፡የጆሮ ኢንፌክሽን ብዙ ጊዜ የላይኛውን የአየር ቧንቧ ከሚያጠቁ በሽታዎች ጋር ተያይዞ የሚመጣ በሽታ ነው፡፡

የላይኛውን የአየር ቧንቧ (እንደ ጉንፋንና አለርጂ የመሳሰሉት…) የሚያጠቁ በሽታዎች በሚኖሩ ጊዜ የጆሮን የመካከለኛውን ክፍል እና ጉሮሮን የሚያገናኘው ቱቦ (eustachian tube) ያብጥና አየር ወደ መካከለኛው የጆሮ ክፍል እንዳይገባ ያደርጋል፡፡

ይኼም በመካከለኛው የጆሮ ክፍል ውስጥ ፈሳሽ እንዲጠራቀም እና ለባክቴሪያ አመቺ የመራቢያ ሁኔታን እንዲፈጥር ያደርጋል፡፡

ባክቴሪያ ከተራባ በኋላ በአካባቢው ያሉ ህዋሶችን በመግደል መግል እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡ ይህ መግል በበዛ ቁጥር የጆሮ ታምቡርን በመጫን ህመም እንዲሁም የመስማት ችግርን ያስከትላል፡፡

የጆሮ ኢንፌክሽን (otitis media) አይነቶች

1 አጣዳፊ የጆሮ ኢንፌክሽን (acute otitis media) ማለት በ 15 ቀን ውስጥ የሚፈጠር የመሀል የጆሮ ክፍል ኢንፌክሽ ሲሆን የጆሮ የመሀለኛውን ክፍል ያጠቃል።

2 የጠና የጆሮ ኢንፌክሽን (chronic otitis media) ማለት ከ 15 ቀን በላይ የቆየ የጆሮ ኢንፌክሽን ሲሆን ብዙውን ጊዜ መግል የመያዝ ነገር ይኖራል።

3 ኢፊውዥን የጆሮ ኢንፌክሽን (otitis media with effusion) ይህ ከአጣዳፊ የጆሮ ኢንፌክሽን በሆኋ ወይም የህመሙ ምልክቶች ከጠፉ በሆኋ ፈሳሽ እዛው የመሀል የጆሮ ክፍል ሲቀር ነው።

ማልቀስ ከወትሮ በተለየ
መነጫነጭ
እንቅልፍ ማጣት
የጆሮ ህመም
ራስ ምታት
የአንገት ህመም
ከጆሮ ፈሳሽ መውጣት
ትኩሳት
ማስመለስ
ተቅማጥ
የመስማት ችሎታ መቀነስ
የሰውነት ሚዛንን መጠበቅ አለመቻል

ምልክቶች አዋቂ ሰዎች ላይ

የጆሮ ህመም
ከጆሮ ፈሳሽ መውጣት
ለመስማት መቸገር

ምክንያቶች

አለርጂ (allergy)
ጉንፋን
የሳይነስ ኢንፌክሽን (sinus infection)
የሳንባ ምች (pneumonia)
ማጂራት ገትር (meningitis)

አጋላጭ ሁኔታዎች

ከ6 ወር እስከ 3 አመት እድሜ ክልል ውስጥ የሆኑ ህጻናት
ጡጦ መጠቀም
ለተበከለ አየር መጋለጥ
በተደጋጋሚ ለሲጋራ ጭስ መጋለጥ
ቀዝቃዛ የአየር ንብረት

ህክምና

ሙቅ ነገር ቦታዉ ላይ መያዝ፡- ይህ ህመሙን ለመቀነስ ይረዳል፡፡
የህመም ማስታገሻ መድሃኒት፡- የህክምና ባለሙያዎች የህመም ማስታገሻ መድሃኒት ሊያዝሎት ይችላል፡፡
ፀረ ባክቴሪያ (Antibiotics)

ለተጨማሪ ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎች
በቴሌግራም ቻናላችን t.me/triadhealth1
በመወያያ ግሩፕ t.me/triadhealt
እንዲሁም
በፌስቡክ ገፅ fb.com/triadhealth1 ይከታተሉን።
‌‌

Translation: am-en
Otitis media


Ear infections are a type of illness caused by bacteria or viruses. Ear infections are often associated with diseases of the upper airways.

In diseases of the upper airways (such as colds and allergies…), the eustachian tube that connects the middle ear to the throat swells and prevents air from entering the middle ear.

This builds up fluid in the middle ear and creates a favorable breeding ground for bacteria.

When bacteria multiply, they kill the surrounding cells and cause pus. Excessive pressure on the eardrum can cause pain and hearing loss.

Types of otitis media

1 Acute otitis media is an infection of the middle ear that occurs within 15 days and affects the middle ear.

2 Chronic otitis media is an infection that lasts for more than 15 days and usually has pneumonia.

3 otitis media with effusion This is when there is an acute ear infection or if the symptoms disappear, there is still fluid in the middle ear.

Crying is unusual
Irritability
ማጣት Insomnia
ህመም Ear pain
Headache
Neck pain
መውጣት Outflow of fluid from the ear
Fever
Recovery
Diarrhea
መቀነስ Hearing loss
ቻል Inability to maintain body balance

Symptoms in adults

ህመም Ear pain
መውጣት Outflow of fluid from the ear
Difficulty hearing

Reasons

Aller Allergy
The flu
Sin Sinus infection
P Pneumonia
Men Meningitis

Risk factors

ህጻናት Children between 6 months and 3 years of age
መጠቀም Using a bottle
Exposure to polluted air
Frequent exposure to cigarette smoke
Cold weather

Treatment

፡ Hold a warm object in place - this will help reduce the pain.
፡ Painkillers: Doctors can prescription
483 viewsedited  17:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-09 10:57:06
47) A patient present with enophthalmos after a trauma to face by blunt object. There is no fever and no extraocular muscle palsy. Diagnosis is:
Final Results
17%
a. Fracture maxilla
33%
b. Fracture zygoma
17%
c. Blow out fracture
33%
d. Fracture ethmoid
6 voters142 views07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-08 19:25:25 ኪንታሮት መንስኤና መፍትሄዎች (ህክምና)

የቂጥ ኪንታሮት ሠገራን በምናስወገድ ጊዜ ከማማጥ ወይንም በእርግዝና ጊዜ በሚከሰት የደም ስሮች ላይ የሚገኝ ግፊት ምክንያት የሚመጣ ሲሆን በሁለት መልኩ ይከፈላል፡፡
1) ውስጣዊ ኪንታሮት (internal hemorrhoid) በፊንጢጣ ውስጥ የሚገኝ
2) ውጫዊ ኪንታሮት (external hemorrhoid) በላይኛው ቆዳ ላይ የሚገኝ
ኪንታሮት በአብዛኛው የሚከሰት ሲሆን በተለይ ዕድሜያቸው 50 ዓመት የሞላቸው ሰዎች ላይ በስፋት (ግማሽ በሚሆን ደረጃ) የኪንታሮት ምልክቶች እንደሚያዩ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ነገር ግን አብዛኞቹ በቤት ውስጥ ሕክምና እና የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ በማድረግ ይድናሉ፡፡

ኪንታሮትን የሚያስከትሉ ምክንያቶች

• ሠገራን ሲያስወግዱ ለረጅም ጊዜ ማማጥ
• ለረጅም ሰዓታት በመፀዳጃ ቤት መቀመጥ
• የሆድ ድርቀት (ለረጅም ጊዜ የቆየ)
• ከመጠን ያለፈ ውፍረት
• ዕርግዝና
• የፋይበር መጠኑ የቀነሰ ምግብ መመገብ ናቸው
• በዕድሜ መጨመር ቬይኖችን የሚደግፉ የሰውንት ክፍሎች እንዲደክሙ ስለሚያደርግ ለሄሞሮይድ ያጋልጣል፡፡

የኪንታሮት ምልክቶች

• ሕመም የሌለው ከፊንጢጣ የሚፈስ ደም
• በሰገራ መውጫ አካባቢ ማሳከክ
• ሕመም ወይንም አለመመቸት
• በፊንጢጣ አካባቢ እብጠት ናቸዉ፡፡

ሃኪምዎን ማማከር የሚገባዎ መቼ ነው?

• በፊንጢጣ የሚወጣ ደም የኪንታሮት የተለመደ ምልክት ነው፡፡ ነገር ግን ከሌሎች የሕመም ዓይነቶች እንደ ኮሎሬክታል ካንሰር እና ሌሎች የህመም አይነቶች ጋር ተመሳሳይ ምልክት ሊኖረው ስለሚችል ሄሞሮይድ ነው በሚል ግምት ችላ ሊባል አይገባም፡፡ ስለዚህም ወደ ሐኪም በመሄድ መመርመር ያስፈልጋል፡፡
• ከፍተኛ ሕመም የሚሰማዎ ከሆነ እና በቤት ውስጥ የሕክምናዎች ለውጥ የማያገኙ ከሆነ ወደ ሕክምና ቦታ መሄድ ይገባዎታል፡፡
• ከፍተኛ መጠን ያለው ደም መፍሰስ ካጋጠምዎ እና እንዲሁም ራስ የማዞር የመሳሰሉት ስሜት ከተሰማዎ ወደ ሐኪም እንዲሄዱ ይመከራል፡፡

ኪንታሮት የሚያስከትለው ተያያዥ ጉዳቶች ምንድን ናቸዉ?

• አኒሚያ (የደም ማነስ) ከፍተኛ የሆነ ደም በሚፈስ ጊዜ በሰውነታችን ውስጥ ኦክስጂን ተሸካሚ ቀይ የደም ሴሎች መጠን ስለሚቀንስ የድካምና ራስ የመሳት ሁኔታዎችን ያስከትላል፡፡
• ለውስጣዊ ሄሞሮይድ የሚደርሰው የደም ፍሰት መጠን ሲቀንስ ከፍተኛ የሆነ ሕመምን ያስከትላል፡፡ ይህም ለሴሎች መሞት እና ለጋንግሪን ይዳርጋል፡፡

በቤት ውስጥ የሚደረጉ ሕክምናዎችና የአኗኗር ዘይቤ ለውጦች

• ለብ ባለ ውሃ ከ10 – 15 ደቂቃ በቀን በቀን ሁለትና ሶስት ጊዜ መዘፍዘፍ
• ሁሌም ከተፀዳዱ በኋላ በሚገባ በንፁህ ለብ ባለ ውሃ መታጠብ
• ደረቅ የሆነ የመፀዳጃ ወረቀትን አለመጠቀም
• እብጠት እንዲቀንስ በረዶን መጠቀም
• ሕመም ማስታገሻ መድኃኒቶችን መጠቀም
ከላይ የተጠቀሙትን በመጠቀም በአጭር ጊዜ ውስጥ ሄሞሮይድን ማጥፋት የሚቻል ሲሆን ሕመም የሚያብስ ከሆነ እና ምንም ዓይነት ለውጥ በሳምንት ውስጥ ካላገኙ ወደ ሕክምና ቦታ እንዲሄዱ ይመከራል፡፡

ሄሞሮይድን ለመከላከል ምን ማድረግ ይገባል?

• በፋይበር የበለፀጉ ምግቦችን ማዘውተር - አትክልት፣ፍራፍሬዎችን መመገብ ሠገራን በማለስለስ ማስማጥ እንዳይኖር ያድርጋል፡፡
• ፈሳሽ በብዛት ይውሰዱ - በቀን ከስድስት እስከ ስምንት ብርጭቆ ውሃን ወይም ጭማቂን መውሰድ
• ማስማጥን ማስወገድ - ሠገራን ለማስወጣት በምናምጥ ጊዜ በደም ስሮቻችን ላይ ከፍተኛ የሆነ ግፊትን ስለምንፈጥር ለሄሞሮይድ/ለኪንታሮት/ ተጋላጭንት ይጨምራል፡፡
• ሠገራ በሚመጣ ጊዜ ጊዜውን ሳያልፉ ወደ መፀዳጃ ቤት በመሄድ ያስወግዱ፡፡ አለዚያ ሠገራዎ ስለሚደርቅ ለማስወገድ አስቸጋሪ ይሆናል፡፡
• የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያዘውትሩ - የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ ጤናማ እንድንሆን ያደርጋል፣
• ለረጅም ሰዓታት መቀመጥን ያስወግዱ፡፡ በተለይም በመፀዳጃ ቤት ለረጅም ሰዓት መቀመጥ ለሄሞሮይድ መከሰት ምክንያት ሊሆን ይችላል፡
149 viewsedited  16:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ