Get Mystery Box with random crypto!

ውድ የሀገሬ ልጆች ፤ ወቅቱ የክረምት ወቅት እንደመቃረቡ መጠን ከፍተኛ ቅዝቃዜና ብርድ እንዳለ ይታ | TRIAD HEALTH System / ትሪያድ ሐልዝ ሲስተም

ውድ የሀገሬ ልጆች ፤ ወቅቱ የክረምት ወቅት እንደመቃረቡ መጠን ከፍተኛ ቅዝቃዜና ብርድ እንዳለ ይታወቃል።
ይህን ብርድ ለመከላከል ሲባል እቤት ውስጥ ከሰል የማቀጣጠልና የቤቱን ሙቀት ለመጨመረ የሚደረግ ሂደት አለ።
ሆኖም በቂ አየር በማይገባበተት፣ መስኮትና በር በተዘጋበት ቤት ውስጥ የሚቀጣጠልና የሚጤሰ ከሰል ለCarbon monoxide Poisoning ስለሚያጋልጥ በዚህም የተነሳ ለከፍተኛና አጣዳፊ የአየር እጥረትና ለሞት እየተጋለጡ እንዲሁም በመኝታቸው ላይ ሞተው እየተገኙ ያሉ ዜጎች እየተበራከቱ በመሆኑ ጥንቃቄ እንድታደርጉ በአክብሮት አሳስባለሁ።
ጥንቃቄ
1. ከሰል በሚያቀጣጥሉበት ወቅት ቤት ውስጥ በቂ አየር እንደሚገባ ያረጋግጡ
2. ከመተኛትዎ በፊት የተቀጣጠለ ከሰል ካለ ማጥፋትዎን አይዘንጉ!
3. ከሰል በተቀጣጠለበት ቤት ውስጥ ከፍተኛ ራስ ምታት፣ ማቅለሽለሽ፣ የድካም ስሜትና መልፈስፈስ ያጋጠመው ሰው ካለ በቂ አየር እንዲያገኙ ያግዟቸው፣ ራሱን የሳተ ከሆነ በፍጥነት ወደ አቅራቢያው የጤና ተቋም ያድርሱ።
ሁሌም ሠላም ሁኑ!
ዶ/ር ብዙአየሁ ፤ ጠቅላላ ሀኪም