Get Mystery Box with random crypto!

የአፍንጫ አለርጂ (Allergic rhinitis) የአፍንጫ አለርጂ/ አለርጂክ ሪሄናይትስ የመ | TRIAD HEALTH System / ትሪያድ ሐልዝ ሲስተም

የአፍንጫ አለርጂ (Allergic rhinitis)

የአፍንጫ አለርጂ/ አለርጂክ ሪሄናይትስ የመተንፈሻ አካል አለርጂ ሲሆን ይህ ችግር እንደ የአፍንጫ ፈሳሽ መዝረብረብ፣ የአይን መብላት/ማሳከክ፣ የአፍንጫ ማፈን/መጠቅጠቅ ማስነጠስንና የሳይነስ ቦታዎች ላይ መክበድ የመሰሳሉትን ጉንፋን መሰል ምልክቶች የሚያመጣ የህመም አይነት ነዉ፡፡
ይህ ህመም የሚከሰተው አለርጂን ሊያመጡ በሚችሉ በቤት ዉስጥና ከቤት ዉጪ ያሉ እንደ ብናኝ፣ አቧራ፣ ግነት ያላቸው ጥሩም ይሁን መጥፎ ጠረኖች እንዲሁም የቤት ውስጥ እንደ እንስሳት አይነምድር ላሉ ነገሮች በምንጋለጥበት ወቅት ሰዉነታችን የሚያሳያዉ ያልተገባ ምላሽ በሚኖርበት ወቅት ነዉ፡፡

የህመሙ ምልክቶች ምንድናቸው?

ቅድሚያ የሚታዩ ምልክቶች ፦
የአፍንጫ፣የአፍ አካባቢ፣የጉሮሮ፣የቆዳ ወይም የሌሎች የአካል ክፍሎች መቆጥቆጥ
ለማሽተት መቸገር
ለረጅም ጊዜ የማያቋርት ቀጭን ንፍጥ
ማስነጠስ
የአይን ማልቀስ

በሂደት የሚታዩ
ምልክቶች ፦
የአፍንጫ መደፈን
ሳል
የጆሮ መደፈን
የጉሮሮ ህመም
ጥቁርና ክብ ቅርፅ ያለዉ ምልክት በአይን ላይ መታየት
የአይን ማበጥ
የራስ ምታት ወ.ዘ.ተ.

የአፍንጫ አለርጂ መንስኤዎች
የእጽዋት ወይም የአበባ ሽታ
የሽቶ፣ ሳሙና፣ ሰንደል ወይም እጣን አይነት ሽታዎች

የአመቱ ወቅትና የአፍንጫ አለርጂ
የአፍንጫ አለርጂ የሚነሳበት/የሚባባስበት ወቅት በአመት ዉስጥ የሚለያይ ሲሆን በተለይ ዛፎች፣ ሳርና የተለያዩ አበቦች በሚያብቡት ወቅት ይብሳል በተጨማሪም ብርድ እና ቅዝቃዜ የሚበረታበት ወቅትም ላይ ችግሮቹ ሲባባሱ ይስተዋላል፡፡ በቤትዎ ዉስጥ ያሉና አለርጂን ሊያስነሱ የሚችሉ እንደ የምንጣፍም ይሁን ከሌላ ነገሮች የሚነሱ አቧራና ቡናኝ፣ በረሮ፣ ሻጋት፣ የቤት እንስሳት አይነምድር ሁሌ ካለ አመቱን በሙሉ የህመሙ ምልክቶች ላይጠፋ ይችለል/ሊኖሮት ይችላል፡፡
ለአፍንጫ አለርጂ

ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ነገሮች
አስም ወይም ሌላ የአለርጂ ህመም ካሎት
በቤተሰብ ዉስጥ መሰል ህመም ካለ (አስም ወይም ሌላ የአለርጂ ህመም ካለ)
የሚሰሩበት ወይም የሚኖሩበት አካባቢ ብዙዉን ጊዜ ለአለርጂኖች (አለርጂን ሊያስነሱ ለሚችሉ ነገሮች) የሚያጋልጦ ከሆነ
ለአፍንጫ አለርጂ ሊደረግ የሚችል ህክምና ምንድነው?
ለአፍንጫ አለርጂ ሊደረግ ከሚችሉ ህክምናዎች ዋናዉ ለአለርጂ ሊያጋልጦት ከሚችሉ ነገሮች እራስን መከላከል መቻል ነዉ፡፡ ነገር ግን ሁልጊዜ እራስን ተከላክሎ መቆየት ስለማይቻል በጤና ተቋሟት የሚታዘዙ የአለርጂ መዳኒቶች ይውሰዱ፡፡
ቤትዎን በእንፋሎት ያጥኑት
እንደ ሲጋራ ያሉ የሚረብሹ ነገሮችነን መራቅ
በቂ ውሃ መጠጣትና የአፍንጫ እስፕሬዎች መጠቀም
ሌሎች የተለዩ ምክንቶች ካሉ ማከም
አበቦች በሚያብቡበት ወቅት በርንና መስኮትን መዝጋት
የሚቻል ከሆነ የአየር ማፅጃ በመኪናዎ ዉስጥ መጠቀም
ጠዋት እና ምሽት ላይ የሚሞቅ ነገር መልበስ
በጣም ነፋሻማና ደረቅ አየር በሚበዛበት ሰዓት ከቤት ያለመዉጣት
በአትክልት/ጋርደን አካባቢ ስራ የሚሰሩ ከሆነ የአፍንጫ ማስክ መጠቀም(አፍንጫን
መሸፈን) ቡናኝን ለመከላከል
በረሮዎች ሊገቡበትና ሊራቡበት የሚችሉ ቀዳዳዎችን መድፈን
የወዳደቁ የምግብ ተርፍራፊዎችን ከዕቃና ከወለል ላይ ማፅዳት
ምግቦችን በሚከደን እቃ ዉስጥ ማስቀመጥ
የበረሮ ማጥፊያ መድሃኒቶችን መጠቀም
ከተቻለ የቤት እንስሳት በቤት ዉስጥ እንዳይኖሩ ማድረግ