Get Mystery Box with random crypto!

ሙዝ ለጤና የሚኖረው 15 ጠቀሜታዎች 1. ጥርስን ያነጣል!! ጥርስዎን ሁልጊዜ ሲቦርሹ ለሁለት ደቂ | TRIAD HEALTH System / ትሪያድ ሐልዝ ሲስተም

ሙዝ ለጤና የሚኖረው 15 ጠቀሜታዎች

1. ጥርስን ያነጣል!!
ጥርስዎን ሁልጊዜ ሲቦርሹ ለሁለት ደቂቃ ያህል በሙዝ ልጣጭ/ልጫ ጥርስዎን ይሹት ከዚያም አስደናቂ ለውጥ ያገኙበታል።

2. በተለያዩ ነፍሳቶች ሲነከሱ ቁስልዎን ያስታግስልዎታል!!
ነፍሳቱ የነከስዎት ቦታ ላይ በሙዝ ልጫ በማሸት የሚኖረውን እብጠትና ህመም መቀነስ ይቻላል።

3. የተጎዳን የሰውነት ቆዳን ያስተካክላል!!
ሙዝ የተበላሸ ወይም የተጐዳ የፊት ቆዳን በሚያምር አዲስ የፊት ቆዳ የመተካት ምትሀታዊ ሀይል አለው።

4. ለእፅዋት ማዳበሪያነት ያገለግላል!!
ደረቅ የሙዝ ልጫ ተወዳዳሪ የሌለው የአትክልትና እፅዋት ማዳበሪያ ነው።

5. የፊት መሸብሸብ ወይም መጨማደድን ይከላከላል!!
ሙዝ ከፍተኛ የክሬምና የተፈጥሮ ማር ካላቸው ምግቦች የሚመደብ ሲሆን አንዳንድ ሴቶች የፊት መሸብሸብን ለመከላከል ሲሉ ከሙዝ የተሰሩ የፊት ክሬሞችን በሳምንት ለ3 ጊዜ ያህል ይጠቀማሉ።

6. የቆዳ መሰንጠቅን ይከላከላል!!
የሰውነት ቆዳዎ እያሳከክዎትና እየተሰነጣጠቀ ተቸግረዋል? ህመምዎ(ችግርዎ) ይገባኛል፤በጣም እድለኛ ነዎት!! እንደዚህ ያድርጉ የተሰነጠቀውን የሰውነትን ቆዳ በሙዝ ልጫ(ልጣጭ) ይሹት እንደዚያ ሲያደርጉ በሙዙ ልጫ ላይ ያለው ተፈጥሮአዊ ኢንዛይም በተሰነጠቀው ቆዳዎ ላይ በመግባት ስራውን ይሰራል ማለት ነው።

7. ጥሩ የአይስክሬም መስሪያ ነው!!
በጣም ጣፋጭ ነገር ይወዳሉ? ነገር ግን ለማዘጋጀት ጊዜ ወይም ገንዘብ የለዎትም? እንግዲውስ እንዲህ ያድርጉ በጣም የቀዘቀዘ ሙዝ ቆራርጠው ወደ አይስክሬም መስሪያ ያስገቡት ከዚያም አስደናቂ ጣዕም ያለው አይስክሬም ይመገባሉ።

8. ክንታሮትን ያድናል!!
ሙዝ በፓታሲየም የበለጸገ ነው። ይህ ንጥረ ነገር ክንታሮትን የማዳን አቅም አለው ስለዚህ ሙዝ ተፈጥሮአዊ የክንታሮት መድሀኒት ሆኖ ያገለግላል።

9. ሰውነታችን በስለት ሲቆረጥ ወይም ሲያብጥ የማዳን ሀይል አለው!!
ሙዝ ሰውነታችን በግጭት ወይም በሌላ ምክንያት ሲያብጥ ወይም ስለት ነገር ሲቆርጠን በውስጡ ፓታሲየም የተባለ ንጥረ ነገር ስላለው ሰውነታችን ለማገገም የሚያደርገውን ሂደት ያግዛል ወይም ያፋጥነዋል።

10. ሙዝ ወፎችንና ቢራቢሮዎችን የመሣብ ሀይል አለው!!
ወፎችንና ቢራቢሮዎች ልክ እንደሠው ልጅ ሁሉ የሙዝን ቃና በጣም ይወዱታል።ስለዚህ ሙዝ ይህን ያህል የመሣብ አቅም ስላለው ወፎችን የመመልከት ፍላጎት ካለዎት በአካባቢዎ ሙዝ ይጣሉላቸው ከዚያም በአስደናቂው ቃና ወደርስዎ ይስባሉ።

11. የቆዳ ውጤቶችንና የብር ጌጣጌጦችን (silver) ያፀዳል!!
የቆዳ ዉጤቶችንና ከብር የተሰሩ ጌጣጌጦችን ለማፅዳት ለመርዛማ ኬሚካሎችን ለመግዛት ገንዘብዎን አያጥፉ በምትኩ በሙዝ ልጫ(ልጣጭ) በደንብ ካሹት በኋላ በጨርቅ ይጥረጉት።

12. ሙዝ በፀረ-ተባይ መድሀኒትነት ያገለግላል!!
ማንም ሰው ቢሆን እፅዋት ተጎድተው ማየት አይፈልግም!! የሙዝ ልጫን ቆራርጠው በእፅዋቱ አካባቢ ከ6-7 ሳ.ሜ አርቀው ይቅበሩዋቸው ከጥቂት ጊዜ በኋላ በአካሎቹ ላይ ያሉት ተባዮች ይሞታሉ።

13.የውሻን በሽታ ይከላከላል!!
በፍቅር የሚወድዎትን ውሻዎ በቀላሉ ጤናውን ይጠብቅልዎታል።

14. ውሀን ያጣራል!!
የተለያዮ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የሙዝ ልጫ/ልጣጭ በወንዝ ውሀ ውስጥ የሚገኙትን መርዛማ ንጥረ ነገሮችን መጦ የመያዝ አቅም አለው።

15. በሽታ የመከላከል አቅምዎን ይጨምራል።