Get Mystery Box with random crypto!

የጆሮ ኢንፌክሽን (otitis media) የጆሮ እንፌክሽን በብዛት በባክቴሪያ ወይም በቫይረስ ም | TRIAD HEALTH System / ትሪያድ ሐልዝ ሲስተም

የጆሮ ኢንፌክሽን (otitis media)


የጆሮ እንፌክሽን በብዛት በባክቴሪያ ወይም በቫይረስ ምክንያት የሚከሰት የህመም አይነት ነዉ፡፡የጆሮ ኢንፌክሽን ብዙ ጊዜ የላይኛውን የአየር ቧንቧ ከሚያጠቁ በሽታዎች ጋር ተያይዞ የሚመጣ በሽታ ነው፡፡

የላይኛውን የአየር ቧንቧ (እንደ ጉንፋንና አለርጂ የመሳሰሉት…) የሚያጠቁ በሽታዎች በሚኖሩ ጊዜ የጆሮን የመካከለኛውን ክፍል እና ጉሮሮን የሚያገናኘው ቱቦ (eustachian tube) ያብጥና አየር ወደ መካከለኛው የጆሮ ክፍል እንዳይገባ ያደርጋል፡፡

ይኼም በመካከለኛው የጆሮ ክፍል ውስጥ ፈሳሽ እንዲጠራቀም እና ለባክቴሪያ አመቺ የመራቢያ ሁኔታን እንዲፈጥር ያደርጋል፡፡

ባክቴሪያ ከተራባ በኋላ በአካባቢው ያሉ ህዋሶችን በመግደል መግል እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡ ይህ መግል በበዛ ቁጥር የጆሮ ታምቡርን በመጫን ህመም እንዲሁም የመስማት ችግርን ያስከትላል፡፡

የጆሮ ኢንፌክሽን (otitis media) አይነቶች

1 አጣዳፊ የጆሮ ኢንፌክሽን (acute otitis media) ማለት በ 15 ቀን ውስጥ የሚፈጠር የመሀል የጆሮ ክፍል ኢንፌክሽ ሲሆን የጆሮ የመሀለኛውን ክፍል ያጠቃል።

2 የጠና የጆሮ ኢንፌክሽን (chronic otitis media) ማለት ከ 15 ቀን በላይ የቆየ የጆሮ ኢንፌክሽን ሲሆን ብዙውን ጊዜ መግል የመያዝ ነገር ይኖራል።

3 ኢፊውዥን የጆሮ ኢንፌክሽን (otitis media with effusion) ይህ ከአጣዳፊ የጆሮ ኢንፌክሽን በሆኋ ወይም የህመሙ ምልክቶች ከጠፉ በሆኋ ፈሳሽ እዛው የመሀል የጆሮ ክፍል ሲቀር ነው።

ማልቀስ ከወትሮ በተለየ
መነጫነጭ
እንቅልፍ ማጣት
የጆሮ ህመም
ራስ ምታት
የአንገት ህመም
ከጆሮ ፈሳሽ መውጣት
ትኩሳት
ማስመለስ
ተቅማጥ
የመስማት ችሎታ መቀነስ
የሰውነት ሚዛንን መጠበቅ አለመቻል

ምልክቶች አዋቂ ሰዎች ላይ

የጆሮ ህመም
ከጆሮ ፈሳሽ መውጣት
ለመስማት መቸገር

ምክንያቶች

አለርጂ (allergy)
ጉንፋን
የሳይነስ ኢንፌክሽን (sinus infection)
የሳንባ ምች (pneumonia)
ማጂራት ገትር (meningitis)

አጋላጭ ሁኔታዎች

ከ6 ወር እስከ 3 አመት እድሜ ክልል ውስጥ የሆኑ ህጻናት
ጡጦ መጠቀም
ለተበከለ አየር መጋለጥ
በተደጋጋሚ ለሲጋራ ጭስ መጋለጥ
ቀዝቃዛ የአየር ንብረት

ህክምና

ሙቅ ነገር ቦታዉ ላይ መያዝ፡- ይህ ህመሙን ለመቀነስ ይረዳል፡፡
የህመም ማስታገሻ መድሃኒት፡- የህክምና ባለሙያዎች የህመም ማስታገሻ መድሃኒት ሊያዝሎት ይችላል፡፡
ፀረ ባክቴሪያ (Antibiotics)

ለተጨማሪ ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎች
በቴሌግራም ቻናላችን t.me/triadhealth1
በመወያያ ግሩፕ t.me/triadhealt
እንዲሁም
በፌስቡክ ገፅ fb.com/triadhealth1 ይከታተሉን።
‌‌

Translation: am-en
Otitis media


Ear infections are a type of illness caused by bacteria or viruses. Ear infections are often associated with diseases of the upper airways.

In diseases of the upper airways (such as colds and allergies…), the eustachian tube that connects the middle ear to the throat swells and prevents air from entering the middle ear.

This builds up fluid in the middle ear and creates a favorable breeding ground for bacteria.

When bacteria multiply, they kill the surrounding cells and cause pus. Excessive pressure on the eardrum can cause pain and hearing loss.

Types of otitis media

1 Acute otitis media is an infection of the middle ear that occurs within 15 days and affects the middle ear.

2 Chronic otitis media is an infection that lasts for more than 15 days and usually has pneumonia.

3 otitis media with effusion This is when there is an acute ear infection or if the symptoms disappear, there is still fluid in the middle ear.

Crying is unusual
Irritability
ማጣት Insomnia
ህመም Ear pain
Headache
Neck pain
መውጣት Outflow of fluid from the ear
Fever
Recovery
Diarrhea
መቀነስ Hearing loss
ቻል Inability to maintain body balance

Symptoms in adults

ህመም Ear pain
መውጣት Outflow of fluid from the ear
Difficulty hearing

Reasons

Aller Allergy
The flu
Sin Sinus infection
P Pneumonia
Men Meningitis

Risk factors

ህጻናት Children between 6 months and 3 years of age
መጠቀም Using a bottle
Exposure to polluted air
Frequent exposure to cigarette smoke
Cold weather

Treatment

፡ Hold a warm object in place - this will help reduce the pain.
፡ Painkillers: Doctors can prescription