Hepatitis b ህክምና ለተወለደ ህፃን ከ HbsAg Positive እናት የተወለደ ህፃን በተወለደ ከ12 እስከ 24 ሰዓት ውስጥ መውሰድ ያለበት መድሀኒቶች ይኖራሉ። እነኝህም Hepatitis b vaccine(የሄፓታይተስ b ክትባት) እና Hepatitis b immunoglobulins (የሄፓታይተስ b ኢሚውኖግሎቡሊን) ተብለው ይታወቃሉ ። አሰጣጥ Hepatitis b vaccine(የሄፓታይተስ b ክትባት) የመጀመሪያው ክትባት ህፃኑ ኪሎው ከ 2000ግም በላይ ከሆነ ⁃ 0.5ML IM within 24 hr ህፃኑ ኪሎው ከ 2000ግም በታች ከሆነ ⁃ 0.5ML IM በተወለደ በ1 ወሩ ወይም እናትየው ከሆስፒታል ወደ ቤት በምትሸኝ ጊዜ መውሰድ ይኖርበታል። እናትየው በhepatitis ቫይረስ መጠቃቷ ወይም አለመጠቃቷ የማይታወቅ እና ማረጋገጥ ካልተቻለ ግን ህፃኑ ኪሎው ከ 2000ግም በላይ ከሆነ ⁃ 0.5ML IM within 24 hr ህፃኑ ኪሎው ከ 2000ግም በታች ከሆነ ⁃ የእናትየው የhepatitis ሁኔታ እስኪረጋገጥ መጠበቅ ሁለተኛው ክትባት ህፃኑ አንደኛውን ከወሰደ በ1 ወሩ መውሰድ ይኖርበታል ሶስተኛውን ክትባት ህፃኑ ሁለተኛውን ከወሰደ ከ5ወር በውሀላ መውሰድ ይገባዋል። Hepatitis b immunoglobulins (የሄፓታይተስ b ኢሚውኖግሎቡሊን) ⁃ 0.5ML IM within 12 hrs after birth ህፃኑ ክትባቱን ካልተከተበ እና ማግኘት ካልቻለ Hepatitis b immunoglobulinኑን በ 3 እና 6 ወር ላይ ደግሞ መውሰድ ይገባዋል። 213 views09:18