2022-04-08 17:43:34
የኩላሊት በሽታ 5 ደረጃዎች / Stages of Kidney Disease
https://t.me/triadhealth1
የኩላሊት በሽታ ወይም የኩላሊት ሥራ ማቆም ከፍተኛ የሆኑ የኩላሊት ችግሮች ናቸው፡፡ ሥር የሰደደ የኩላሊት በሽታ (Chronic Kidney
Disease) በሚይዘን ጊዜ ሁለቱም ኩላሊቶቻችን በአንድ ጊዜ ስራቸውን አያቆሙም ነገር ግን በሽታው ቀስ በቀስ እየበረታ በመሄድ
ለአመታት ይቆያል፡፡ ስለዚህ በጊዜ በመታከም ዕድሜዎን ማራዘም ይችላሉ፡፡
የኩላሊት በሽታ 5 ደረጃዎች
ግሎመርላር ፊልትሬሽን ሬትን (Glomerular Filtration Rate (GFR)) መሠረት በማድረግ የኩላሊት በሽታን በአምስት (5) ደረጃዎች
ይከፈላሉ፡፡ ግሎመርላር ፊልትሬሽን ሬት (ጂ.ኤፍ.አር) (GFR) ማለት ኩላሊታችን ደምን በማጣራት ትርፍ ፈሳሾችንና ውጋጅ ቆሻሻዎችን
ለማስወገድ የሚያደርገው ሂደት ነው፡፡
ደረጃ አንድ (1) (Stage One)
• በዚህ ደረጃ ጂ.ኤፍ.አር በደቂቃ ውስጥ ከ 90 ሚ.ሊ. በላይ ደምን ያጣራል፡፡
※ምልክቶች
• ከመደበኛው መጠን የበለጠ ዩሪያ በደም ውስጥ ይገኛል፡፡
• በሽንት ውስጥ ፕሮቲን ወይም ደም ይገኛል፡፡
• በሲቲ ስካን ወይም በአልትራሳውንድ የኩላሊት ጉዳት ይታያል፡፡
• በቤተሰብ ውስጥ የፖሊሲስቲክ ኩላሊት በሽታ መኖር፡፡
ደረጃ ሁለት (2) (Stage Two)
• በዚህ ደረጃ ጂ.ኤፍ.አር በደቂቃ ውስጥ ከ 60-89 ሚ.ሊ. ደምን ያጣራል፡፡
• ምልክቶቹ ከደረጃ አንድ ጋር ተመሳሳይ ናቸው፡፡
ደረጃ ሶስት (3) (Stage Three(
• በዚህ ደረጃ ጂ.ኤፍ.አር በደቂቃ ውስጥ ከ 30-59 ሚ.ሊ. ይሆናል ወይም ደምን ያጣራል፡፡
※ምልክቶች
• በደረጃ አንድና ሁለት ላይ ከሚታዩ ምልክቶች በተጨማሪ የሚከተሉት ይስተዋላሉ፦
• ከፍተኛ የሆነ ድካም፡፡
• ኢዴማ፣ ውሃ ማዘል(መቋጠር) እና የትንፋሽ ማጠር፡፡
• ሻይ የሚመስል ወይም ቡናማ ቀለም ያለው ሽንት በተጨማሪም አረፋ ይኖረዋል፡፡
• በሽንት ውስጥ ደም መኖር(መታየት)፡፡
• ከፍተኛ የኩላሊት ህመም፡፡
• የእግር እረፍት ማጣት ወይም የጡንቻ መሸማቀቅ በመኖሩ ምክንያት የእንቅልፍ ማጣት፡፡
ደረጃ አራት (4) (Stage Four)
• በዚህ ደረጃ ጂ.ኤፍ.አር በደቂቃ ውስጥ ከ 15-59 ሚ.ሊ. ይሆናል ወይም ደምን ያጣራል፡፡
• ከደረጃ አንድ እስከ ሶስት የታዩት ምልክቶች እንዳሉ ሆነው በተጨማሪ፦
• የሽንት አሸናን መቀየር
• ማስመለስ
• ማቅለሽለሽ
• በአፍ ውስጥ የጣዕሞች መቀየር
• የምግብ ፍላጎት መቀነስ
• መጥፎ የአፍ ጠረን
• የትኩረት ማጣትና የነርቭ ችግር
• የእግር ወይም የእጅ ጣቶች መደንዘዝ።
ደረጃ አምስት (5) (Stage Five)
• በዚህ ደረጃ ጂ.ኤፍ.አር በደቂቃ ውስጥ ከ 15 ሚ.ሊ. በታች ይሆናል፡፡
※ምልክቶች
በዚህ የመጨረሻ ደረጃ ኩላሊት ህመም ላይ የሚታዩ ምልክቶች የሚከተሉትን ያጠቃልላል፦
• ማቅለሽለሽ
• የምግብ ፍላጎት መቀነስ
• ድካም
• ማሳከክ
• የራስ ህመምና
• ከመጠን ያነሰ ሽንት ማምረት ናቸው፡፡
በተጨማሪም በቁርጭምጭሚትና አይን አካባቢ እብጠት መኖር፣ የቆዳ ቀለም መቀየርና የቆዳ ቀለም(ፒግመንት) መጨመር ይታያሉ፡፡
383 views14:43