Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-MAGAZINE

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvahethmagazine — TIKVAH-MAGAZINE
ርዕሶች ከሰርጥ:
Update
Digitalmarketing
Cloudbridge
Traininginstitute
Safaricomethiopia
All tags
የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethmagazine
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196.61K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን 251913134524

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 168

2022-12-07 13:13:54
HIV / AIDS አሁን ላይ ለእርሶ
Anonymous Poll
19%
መረጃ አለኝ፣ ግን እዘናጋለው
6%
ተጋላጭ በመሆኔ ያሳስበኛል
34%
ምንም የሚያሳስበኝ ነገር የለም
41%
ሳልዘናጋ እጠነቀቃለው
4.6K voters29.9K views10:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-07 12:14:09
ከሞሮኮ 218 ሺህ 894 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ጂቡቲ ወደብ ይደርሳል ተባለ።

በኢትዮጵያ ለሚመረተው የበጋ ስንዴ ምርት የሚውል 218 ሺህ 894 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተጓጉዞ ጂቡቲ ወደብ የሚደርስ መሆኑን የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ገልጿል።

በቀጣይም ተጨማሪ ሶስት ባለ ከፍተኛ ጭነት መርከቦች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ 218 ሺህ 894 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ ላይ የሚያራግፉ መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ሮባ መገርሳ ለኢዜአ ተናግረዋል።

@tikvahethmagazine
30.6K viewsedited  09:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-07 12:07:44
ወደ ት/ቤት በመሄድ ላይ የነበረችን ልጅ አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በ8 አመት ፅኑ እስራት ተቀጣ፡፡

ደቡብ ጎንደር ዞን ደራ ወረዳ በአንበሳሜ ከተማ ህዳር 19 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ላይ ተማሪ አበባይቱ አራጋው ወደ አንበሳሜ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመማር በመሄድ ላይ እያለች ተፈራ ማሬ ካሳ የተባለ ግለሰብ አስፈራርቶ በመያዝ አስገድዶ ሲደፍራት በአካባቢው የጸጥታ ሀይል ይያዛል።

በዚህም ወንጀለኛው ላይ ምርመራው በማድረግ አቃቢ ህግ ክስ መስርቶበት የወረዳው ፍ/ቤትም መዝገቡን መርምሮ ጥፋተኛ መሆኑን በማስረጃ በማረጋገጥ ህዳር 27 ቀን 2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ8 አመት ፅኑ እስራት የተቀጣ መሆኑን ተገልጿል፡፡

መረጃው፦ የደራ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ነው

@tikvahethmagazine
28.1K viewsedited  09:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-07 11:28:03
#Tanzania

የታንዛኒያው ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን ሀገራቸው ለነጻነት ቀን ዝግጅት ተብሎ በጀት ተመድቦ የነበረ 445,000 ዶላርን ለልዩ ፍላጎት ት/ቤት የህጻናት ማደሪያ ለመገንባት እንዲውል ቀጭን መመሪያ ሰጥተዋል።

በዚህም ሀገሪቷ 61 ዓመት የነጻነት በዓሏን ህዝባዊ ውይይቶችን በማድረግ ቀኑን የምታከብር ይሆኗል። ታንዛኒያ ከእንግሊዝ ቀኝ ግዛት የተላቀቀችበትን የነጻነት በዓሏን በየዓመቱ ህዳር 30 (December 9) ታከብራለች።

@tikvahethmagazine
5.1K viewsedited  08:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-07 11:15:20
ይህን ያውቁ ኖሯል . . .?

በተሸከርካሪ አደጋ ምክንያት ጉዳት የደረሰበት ማንኛውም ሰው እስከ ብር 2000 ድረስ የአስቸኳይ የህክምና አገልግሎት የማግኘት መብት እንዳለው ያውቃሉ?

ለተሸከርካሪ አደጋ ተጎጂዎች በግልና በመንግስት የህክምና ተቋማት እስከ 2 ሺህ ብር ድረስ የአስቸኳይ ህክምና አገልግሎት ለሁሉም የተሸከርካሪ አደጋ ተጎጂዎች እንዲሰጥ የ3ኛ ወገን የመድን ሽፋን ለማስፈፀም በወጣው በሚንስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 300/2006 በአዋጅ ቁጥር 799/2005 አንቀጽ 27 ላይ ተደንግጓል፡፡

በአዋጁ አንቀጽ 27 ንዑስ አንቀጽ 1 እና 2 መሰረት በተሸከርካሪ አደጋ ምክንያት ጉዳት የደረሰበት ማንኛውም ሰው እስከ ብር 2000 ድረስ የአስቸኳይ የህክምና አገልግሎት የማግኘት መብት አለው፤ ማንኛውም የህክምና ተቋም የተሸከርካሪ አደጋ ደርሶበት ወደ ህክምና ተቋም ለመጣ ማንኛውም ተጎጂ የአስቸኳይ ህክምና አገልግሎት በነፃ የመስጠት ግዴታ ይኖርበታል፡፡

በአዋጅ ቁጥር 799/2005 አንቀጽ 2 ንዑስ አንቀጽ 16 መሰረት በመንገድ ላይ በደረሰ በተሸከርካሪ አደጋ የተጎዳ ግለሰብ ከአደጋ ቦታው ወደ ህክምናው ተቋማት በሚጓጓዝበት ወቅት እና በህክምና ተቋሙ ድንገተኛ ክፍል ውስጥ የሚሰራ የህክምና አገልግሎት ነው፡፡

ምንጭ፦ የመንገድ ደኅንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት

@tikvahethmagazine
6.7K viewsedited  08:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-07 10:57:04
#ጎህቤቶችባንክ

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሞርጌጅ ባንክ የሆነው ጎሕ ቤቶች ባንክ ከጥቅምት እስከ ሰኔ 2014 በነበሩት 8 ወራት ውስጥ ከግብር በፊት 7.9 ሚሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን አስታውቋል።

ጎሕ ቤቶች ባንክ አጠቃላይ ሀብቱ 1.2 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ ካፒታሉ ደግሞ 787 ሚሊዮን ብር እንደሆነ ባንኩ አስታውቋል፡፡

ባንኩ 5 ሺሕ 23 ደንበኞችን እንዳፈራ ያስታወቀ ሲሆን፣ እነዚህ ደንበኞች 256 ሚሊዮን ብር ተቀማጭ ማድረጋቸውን ገልጿል፡፡

ባንኩ ከ298 ሚሊዮን ብር በላይ ለ37 ተበዳሪዎች እንዳበደረም ያስታወቀ ሲሆን፣ በከፈታቸው አራት ቅርንጫፎች አገልግሎቱን እያዳረሰ እንደሚገኝም ተነግሯል፡፡

@tikvahethmagazine
7.9K viewsedited  07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-07 10:55:05
በውስጥዎ ያለውን ውብ ነገ እውን ያድርጉ!

ከባለ 2 እስከ ባለ 4 መኝታ ዘመናዊ  አፓርታማዎችን
እስከ 30 ዓመት በሚቆይ የረጅም ጊዜ አከፋፋል
በ9.5% እጅግ አነስተኛ ወለድ

ለተሻለ ነገ ዛሬ ይወስኑ

#በመሀል_ከተማ_ካሳንቺስ 100% ያለቁ
የአፓርታማ ሽያጭ  ከአያት አ.ማ
#በቅርብ_ቀን ትንሽ ቤቶች ብቻ ስላሉን ቀድመው ይመዝገቡ

ለበለጠ መረጃ:
0912898237

ስለ ሪል ስቴት ፈጣን ና ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት  ይህንን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
https://t.me/Bruk_Ayat_Realstate
https://t.me/Bruk_Ayat_Realstate
7.9K viewsedited  07:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-07 10:55:05
#በመሀል_ከተማ_ካሳንቺስ 100% ያለቁ
የአፓርታማ ሽያጭ ከአያት አ.ማ
#በቅርብ_ቀን ትንሽ ቤቶች ብቻ ስላሉን ቀድመው ይመዝገቡ በውስጥ መስመር መልዕክት ለመላክ 

@Bruk23

ብሩክ ሠጠኝ
የአያት አ.ማ የዳያስፖራ ገበያ እና ሽያጭ ባለሙያ ብለው ይደውሉ


0912898237

ስለ ሪል ስቴት ፈጣን ና ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት  ይህንን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
https://t.me/Bruk_Ayat_Realstate
https://t.me/Bruk_Ayat_Realstate
7.4K views07:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-07 10:54:47
ለመኖርያ ቤት ለቢሮ ለንግድ ቦታዎ ውብ እና ማራኪ የሆኑ ዲዛይኖችን በተመጣጣኝ ዋጋ ጥራት ካለው የፊኒሺንግ ስራ ጋር ሰርተን እናስረክቦታለን። ይደውሉልን።

የምንሰጣቸው አገልግሎት
የኢንቴርየር ዲዛይን እና የፊኒሺንግ ስራ
አርቴክቸራል ዲዛይን
የኢፓክሲ ስራ ( Epoxy Work )
የእንጨት ፓርቲሽኖችን መስራት
አጠቃላይ የእንጨት ስራ
ብራንዲንግ

Contact us  @etheldesign1
0939902740
0919361804

Join Telegram: t.me/etheldesign
7.5K views07:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-06 18:06:10
የ2 ልጆቿን አባት በመጥረቢያ በመምታት የግድያ ወንጀል የፈጸመችው ግለሰብ በ21 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣች።

በተደጋጋሚ ይሰድበኛል በሚል በባለቤቷ ላይ ቂም በመያዝ እንቅልፍ የተኛበትን አጋጣሚ በመጠቀም በመጥረቢያ ጭንቅላቱን ደጋማ በመምታት ህይወቱ እንዲያልፍ ግለሰብ በ21 ዓመት ፅኑ አስራት እንድትቀጣ ፈርዶባታል።

ከበቡሽ አለሙ የተባለችው ግለሰብ የሁለት ልጆቿ አባት በሆነው ባለቤቷ ላይ የግድያ ወንጀሉን የፈፀመችው መጋቢት 14 ቀን 2014 ዓ/ም በንፋስ ስልከ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ልዩ ቦታው 58 መዝናኛ ጀርባ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡

ፖሊስ ግለሰቧን በቁጥጥር ስር አውሎ መዝገብ ካደራጀ እና በአቃቤ ህግ ክስ እንዲመሰረት ካደረገ በኋላ ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ሁለተኛ የከባድ ውንብድና እና ግድያ ወንጀል ችሎት በ21 ዓመት ፅኑ እስራት እንድትቀጣ የወሰነባት መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

@tikvahethmagazine
19.6K viewsedited  15:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ