Get Mystery Box with random crypto!

መልካም እረኛ

የቴሌግራም ቻናል አርማ the_good_shepherd — መልካም እረኛ

የሰርጥ አድራሻ: @the_good_shepherd
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 798
የሰርጥ መግለጫ

"እንደ ኢየሱስ ያለን መልካም እረኛን ይፈልጉታል"
~ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
"በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል" ዮሐ 10:27
ጥያቄ ወይ አስተያየት ካለዎት በዚህ አድራሻ ይላኩልን:- @The_Good_Shepherdbot

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1

የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-05-22 10:35:44
ቸር የሆነው አምላካችን ሁሌም እያንዳንዱአን ነፍስ የሚያድንበትን ምክንያት እና አጋጣሚን ይፈልጋልና ለቤተሰባችሁና ለወዳጆቻችሁ ነፍስ ድኅነት መጸለይን አታቋርጡ።

ቅዱስ አባ ዮሴፍ
283 views07:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 21:29:11
በውስጤ ያለችው የኃጢአት ፍቅር ለአንተ ካለኝ ፍቅር ስትበልጥ ይሰማኛል አንተንም እንዳላይ የልቦናዬን አይን የምትጋርድ እርሷ ናትና አቤቱ እንድወድህ ግድ በለኝ ፈቃዴን አልሻውምና። ከኃጢያት ከምትለየዋ ከአንተ ፍቅር አድርሰኝ።
331 views18:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-02 08:25:55
መነኩሴ ልቦናው ሕሙም ነው። ፍቅረ እግዚአብሔርን ያጣጥማልና ከፍቅረ እግዚአብሔር ለራቀው ሁሉ ምነው ባወቁህ እያለ ልቡ ይደማል። ይህቺም ቅድስት ሕመም ናት። እሷም ከእግዚአብሔር የምትሰጥ ናት ልቦናው እንዲህ የቆሰለ አለመፀለይ አይችልምና። ማርልኝ ከማለት አያቆምምና።
381 views05:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-29 23:07:27
"እሱን በመሻት ብታዝን አግኝተኸው ደስ ይልሃል።...እያለቀስህ መከራ እየተቀበልክ እሱን ለማየት መንፈሳዊ ቅንዓት ብትቀና መልኩን በዓይነ ነፍስ ታየዋለህ። ....አቤቱ ጌታዬ ሆይ ወዮልኝ። በፍቅርኽ መንደዴን የሚያበርድልኝ ማነው?... መወደድ ያለህ አቤቱ አንተን የሚወድኽ ንዑድ ነው እላለኁ። አንተን አይቶ የሚሰለችኽ የለምና።"
.......

"እሱን አይቶ ልቡ እሱን ከማየት የሰለቸ ማነው? የቃሉን ነገር ሰምቶ እሱን ከመስማት የሰለቸ ማነው?መዓዛዉን ያሸተተ እሱን ለመያዝ እየቸኰለ ደረቱን ያልደቃ ማነው?

አረጋዊ መንፈሳዊ
330 views20:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-25 08:20:58
...አንተ ከእኔ ጋር ነበርህ ። ነገር ግን ከእምቢተኝነቴ ብዛት እኔ ከአንተ ጋር አልነበርሁም :እስከዛሬ ድረስና ሁልግዜ በእኔ ውሰጥ ነበርህ :የአንተን መኖር ግን አስተዉየዉ አላውቅም ።በእኔ ውስጥ በልቤ ውስጥ መስገህ ሳለ ወዴት እንደምታሰማራ ወዴትም እንደምታስመስግ እደነቅ ነበር።ዳሩ ግን አንተ በውሰጤ መኖርህን አላውቅም ነበር።ምንኛ የምትነካ እና ልብን የምትመስጥ ነህ።

ቅ.አውግስጦስ
328 views05:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 22:15:17 † † የጌታ መከራ በሊቃውንት አንደበት አገላለጽ † †

† † በክርስቶስ መከራ ውስጥ የመለኮትና የሥጋ(የትስብእት) ተዋሕዶ ምሥጢር † †

‹‹ታመመ፤ ሞትን ከተቀበለበት ከሥጋ ተዋሕዶ በመስቀል ላይ በፈቃዱ ለሥጋውያን ሞተ፣ ባሕርየ መለኮት ሥጋን ተዋሕዶ በማኅፀን ካደረ ጀምሮ ሥጋ ገንዘቡ እንደመሆኑ በሥጋ ይኸንን ሥርዓት ፈጸመ፡፡ ለማይመረመር ለመለኮቱ ባሕርይ እንደሚገባ ደግሞ እርሱ ኅብስት አበርክቶ ዂሉን ያጠግባል፡፡ አይራብም፤ አይጠማም፤ አይደክምም፤ አያንቀላፋም፤ አይታመምም፤ አይሞትም፤ ሕይወትን ለዂሉ ይሰጣል፡፡ ዳግመኛ በዚያ በሲኦል ተገዝተው ያሉ ነፍሳትን ያድን ዘንድ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወረደ፤ በመለኮቱም ሲኦልን በዘበዘ፤››
(የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ ቄርሎስ)

‹‹እጆቹን፤ እግሮቹን በተቸነከረባቸው ችንካሮች መወጋቱንም እናምናለን፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ ‹እርሱ ደዌያችንን ወሰደ፤ ሕማማችንንም ተሸከመ፤ እኛን ለማዳን ኃጢአታችንንም ለማስተስረይ መከራ ተቀበለ› እንዳለ፤ በባሕርዩ ሕማም የሌለበት ሲኾን በሥጋ የታመመ ነው፡፡ በእርሱ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ድነናል፡፡ በተገረፈና በተቸነከረም ጊዜ በመከራው ዂሉ መለኮትን ሕማም ተሰማው የሚል ሰው ቢኖር የተለየ የተወገዘ ይሁን፤››
(ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ጎርጎርዮስ)

‹‹እርሱ መቼም መች ከመለኮቱ ሳይለይ የሰውነትን ሥራ ዂሉ ገንዘቡ አደረገ፡፡ ይኸውም መራብ፣ መጠማት፣ መንገድ በመሔድ መድከም፣ በመስቀል ላይ መሰቀል፣ በብረት ችንካር መቸንከር ነው፡፡ በሰውነቱ መቸም መች ሰው ነው፤ በአምላክነቱም ሰውን የፈጠረ ነው፡፡ ነገር ግን ከማይከፈል ተዋሕዶ በኋላ መከፈል የለበትም፡፡ ሰው እንደ መኾኑ ስለ እኛ የታመመው፣ የሞተው እርሱ ነው፡፡ በመለኮቱ ግን መቸም መች አይታመምም፤ አይሞትም፡፡ ሕማምንና ሞትንም አይቀበልም፡፡ በሞቱ ሞትን ያጠፋው እርሱ ነው፡፡ ሲኦልንም የበዘበዘው እርሱ ነው፤›› (የአንጾኪያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ዲዮናስዮስ)፡፡

‹‹ነፍሱን ከሥጋው በለየ ጊዜ ያን ጊዜ በሲኦል ፈጥኖ ብርሃን ታየ፡፡ ጌታችን በአካለ ሥጋ ያይደለ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ሔደ፡፡ ሲኦል ተነዋወጠች፤ መሠረቶቿም እፈርስ እፈርስ አሉ፡፡ ምድርን ያለ ጊዜዋ እንዳታልፍ ክብርት ደሙን በምድር ላይ አፈሰሰ፡፡ ከኅልፈት ጠበቃት በእርሷ ያለውንም ዂሉ ጠበቀ፡፡ ስለ ፍጥረት ዂሉ ሥጋውን በመስቀል እንደ ተሰቀለ ተወው፡፡ ነፍሱ ግን ወደ ሲኦል ወረደች ከዚያ ተግዘው የነበሩ ነፍሳትን አዳነች፤ ሲኦልንም በዘበዘች፡፡ ፍጥረትንም ዂሉ ገንዘብ አደረገች፡፡ ሥጋውም በመቃብር ያሉ ሙታንን አስነሣ፤ ነፍሱም በሲኦል ተግዘው የነበሩ ነፍሳትን ፈታች፤›› (የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ሐዋርያው ቅዱስ አትናቴዎስ)፡፡

‹‹ከብርሃን የተገኘ ብርሃን፣ ከባሕርይ አምላክ የተገኘ የባሕርይ አምላክ፣ የተወለደ እንጂ ያልተፈጠረ፣ በባሕርዩ ከአባቱ ጋር አንድ የሚኾን፡፡ ዂሉ የተፈጠረበት፤ ያለ እርሱ ግን ምንም ምን የተፈጠረ የሌለ፤ በሰማይ በምድር ያለውም ቢኾን፡፡ እኛን ስለ ማዳን ከሰማየ ሰማያት ወርዶ በግብረ መንፈስ ቅዱስ ከቅድስት ድንግል ማርያም ፍጹም ሰው ኾነ፡፡ የሠላሳ ዘመን ጐልማሳ ኾኖ በጲላጦስ የሹመት ዘመን ስለ እኛ ተሰቀለ፤ ስለ እኛም ታመመ፤ ሞተ፤ ተቀበረ፤›› (ሠለስቱ ምእት)፡፡

‹‹ምትሐት ያይደለ በእውነት ተራበ፤ ተጠማ፡፡ ዳግመኛም ከኃጥአን፣ ከመጸብሐን ጋር በላ፤ ጠጣ፡፡ ያቀረቡለትንም በላ፡፡ ራሱን አሳልፎ ለመስቀል ሰጠ፡፡ እጁን፣ እግሩን ተቸነከረ፤ ጐኑን በጦር ተወጋ፡፡ ከእርሱም ቅዱስ ምሥጢር የተገለጠበት ደምና ውኃ ፈሰሰ (ወጣ)›› (ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ)፡፡

‹‹የሚሠዋ በግ እርሱ ነው፤ የሚሠዋ ካህን እርሱ ነው፡፡ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም መሥዋዕት የሚቀበል እርሱ ነው፡፡ በፈቃዱ መከራን በሥጋው የተቀበለ መከራንም ዂሉ የታገሠ እርሱ ነው፡፡ እንደ በግ ሊሠዋ መጣ፤ በግ በሚሸልተው ሰው ፊት እንደማይናገር አልተናገረም፡፡ በአንደበቱ ሐሰት አልተገኘበትም፤›› (ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ)፡፡

‹‹በሥጋ መወለድ፣ በመስቀል መከራ መቀበል፣ መሞት፣ መነሣት፣ ገንዘቡ የኾነ እርሱ እግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ ስለዚህ በመስቀል ላይ ሳለ ከጥንት ጀምሮ በመቃብር ያሉ ሙታንን ዂሉ አስነሣ፤›› (ሰማዕቱ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ፊልክስ)፡፡

‹‹ሙሴም ሞትን ያጠፋ ዘንድ አልቻለም፤ እርሱንም ይዞ ገዛው እንጂ፡፡ ከእርሱም በኋላ የተነሡ ነቢያትንም ዂሉ ሞት ገዛቸው እንጂ፡፡ ክርስቶስ ግን በቸርነቱ ለዂሉ ሕይወትን ሰጠ፤›› (የሮማ ኤጲስ ቆጶስ ቅዱስ አቡሊዲስ)፡፡

‹‹በመስቀል በሥጋ ተሰቅሎ ሳለ ለመለኮት ከሥጋ መለየት የለበትም፡፡ አንዲት ሰዓትም ቢሆን የዐይን ጥቅሻ ያህል ስንኳ ቢሆንም መለኮት ከትስብእት አልተለየም፣ በመቃብር ውስጥ በሰላም መለኮት ከትስብእት አልተለየም (የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አዮክንድዮስ)፡፡

‹‹ከአብ ጋር አንድ እንደ መኾንህ ሞት የሌለብህ አንተ ነህ፡፡ ከእኛ ጋር አንድ እንደ መኾንህ በፈቃድህ የሞትህ አንተ ነህ፡፡ በመቃብር ያደርህ አንተ ነህ፡፡ በኪሩቤል ላይ ያለህ አንተ ነህ፡፡ ከሙታን ጋር በመቃብር የነበርህ አንተ ነህ፡፡ በአንተ ሕማምና ሞትም ድኅነት ተሰጠ፡፡ ከሙታን ጋር የተቈጠርህ አንተ ነህ፡፡ ለሙታንም ትንሣኤን የምትሰጥ አንተ ነህ፡፡ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በመቃብር ያደርህ አንተ ነህ፡፡ በዘመኑ ዂሉ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የምትኖር አንተ ነህ፡፡ በመለኮት ሕማም ሳይኖርብህ በሥጋ የታመምህ አካላዊ የእግዚአብሔር ቃል አንተ ነህ፤›› (የኪስኪስ ኤጲስ ቆጶስ ቅዱስ ኤራቅሊስ)፡፡

‹‹ኃጢአታችንን ለማሥተስረይ በሥጋ እንዲህ ታመመ፤ እንደ ሞተ ከነፍሱም በተለየ ጊዜ ሥጋውን እንደ ገነዙ እናምናለን፤›› (የኢየሩሳሌም ኤጲስ ቆጶስ ቅዱስ ዮሐንስ እንዲህ አለ)፡፡

‹‹ነቢይ ዳዊት ‹ነፍሴን በሲኦል አትተዋትም፤ የባሕርይ ልጅህንም ሙስና መቃብርን ያይ ዘንድ አሳልፈህ አትሰጠውም› አለ፡፡ ይህም ጌታ በተዋሐደው አካል ያለውን የነፍስና የሥጋ ተዋሕዶ ያስረዳል፡፡ የቀና ልቡና ዕውቀት በእርሱ ጸንቶ ይኖር ዘንድ፡፡ ዳዊት እንደ ተናገረው እውነት ኾነ፤ ነፍስ መለኮትን ተዋሕዳ ወደ ሲኦል ወርዳለችና፡፡ ሥጋም ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በመቃብር ሳለ መለኮት ከሥጋ አልተለየም፤ አምላክ ሰው የመኾኑን እውነት ያስረዳ ዘንድ፡፡ መለኮት ነፍስን ተዋሕዶ በአካለ ነፍስ የሲኦል ምሥጢርን ገልጦ ፈጽሟልና በሲኦልም በቁራኝነት አልተያዘምና፤››
(የቆጵሮስ ደሴት ኤጲስ ቆጶስ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ ሃይማኖተ አበው

የአባቶቻችን በረከት ይደርብን!
282 views19:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 16:42:55
"የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡

ወየው ወየው ወየው አማኑኤል አምላካችን፡፡

ወየው ወየው ወየው መድኃኒታችን ኢየሱስ፡፡

ወየው ወየው ወየው መድኃኒታችን ኢየሱስ፡፡

ወየው ወየው ወየው ንጉሣችን ክርስቶስ፡፡

ወየው ወየው ወየው ጻድቃን ከዕንጨት አወረዱት፡፡

ሥጋውንም ለመገነዝ ከርቤ የሚባል የጣፈጠ ሽቱንና ንጹሕ በፍታን አመጡ፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው የማይሞት የማይለወጥ፡፡

ከድንግል ማርያም የተወለደ አቤቱ ይቅር በለን፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ የማይሞት የማይለወጥ በዮርዳኖስ የተጠመቀ በመስቀልም የተሰቀለ አቤቱ ይቅር በለን፡፡"

~ ቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ
245 views13:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-11 21:38:50 አማኑኤል ሆይ መድኃኒቴ ሆይ
አትተወኝ አንተ ሞትን እንዳላይ /2/

የግብፅ ከተማ ደምቃ ስትታየኝ
ተሰሎንቄ አድጋ ላይኔ ስትሰበኝ
ኤልሻዳይ ኢየሱስ ልቤን መልስልኝ/2/

አዝ
መታመን በሰው ላይ ምንም አይጠቅምም
መከታነት በሰው ለእኔ አይሆንም
አትተወኝ አንተ አምላክ ዘለዓለም/2/

አዝ
የሚያጽናናኝ የለም እኔ እንዲህ ስከፋ
ህልምም ሆኖብኛል የሰው ሁሉ ተስፋ
ቃልህን የማታጥፍ አንተ ከእኔ አትጥፋ /2/

አማኑኤል ሀገራችንን በመልካም ያስብልን!
328 views18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-30 11:05:27 † † የጌታ መከራ በሊቃውንት አንደበት አገላለጽ † †

385 views08:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ