Get Mystery Box with random crypto!

'የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡ ወየው ወየው ወየው አማኑኤል አምላካችን፡፡ ወየው ወየው | መልካም እረኛ

"የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡

ወየው ወየው ወየው አማኑኤል አምላካችን፡፡

ወየው ወየው ወየው መድኃኒታችን ኢየሱስ፡፡

ወየው ወየው ወየው መድኃኒታችን ኢየሱስ፡፡

ወየው ወየው ወየው ንጉሣችን ክርስቶስ፡፡

ወየው ወየው ወየው ጻድቃን ከዕንጨት አወረዱት፡፡

ሥጋውንም ለመገነዝ ከርቤ የሚባል የጣፈጠ ሽቱንና ንጹሕ በፍታን አመጡ፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው የማይሞት የማይለወጥ፡፡

ከድንግል ማርያም የተወለደ አቤቱ ይቅር በለን፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ የማይሞት የማይለወጥ በዮርዳኖስ የተጠመቀ በመስቀልም የተሰቀለ አቤቱ ይቅር በለን፡፡"

~ ቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ