Get Mystery Box with random crypto!

አማኑኤል ሆይ መድኃኒቴ ሆይ አትተወኝ አንተ ሞትን እንዳላይ /2/ የግብፅ ከተማ ደምቃ ስትታየ | መልካም እረኛ

አማኑኤል ሆይ መድኃኒቴ ሆይ
አትተወኝ አንተ ሞትን እንዳላይ /2/

የግብፅ ከተማ ደምቃ ስትታየኝ
ተሰሎንቄ አድጋ ላይኔ ስትሰበኝ
ኤልሻዳይ ኢየሱስ ልቤን መልስልኝ/2/

አዝ
መታመን በሰው ላይ ምንም አይጠቅምም
መከታነት በሰው ለእኔ አይሆንም
አትተወኝ አንተ አምላክ ዘለዓለም/2/

አዝ
የሚያጽናናኝ የለም እኔ እንዲህ ስከፋ
ህልምም ሆኖብኛል የሰው ሁሉ ተስፋ
ቃልህን የማታጥፍ አንተ ከእኔ አትጥፋ /2/

አማኑኤል ሀገራችንን በመልካም ያስብልን!