Get Mystery Box with random crypto!

መልካም እረኛ

የቴሌግራም ቻናል አርማ the_good_shepherd — መልካም እረኛ
የቴሌግራም ቻናል አርማ the_good_shepherd — መልካም እረኛ
የሰርጥ አድራሻ: @the_good_shepherd
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 798
የሰርጥ መግለጫ

"እንደ ኢየሱስ ያለን መልካም እረኛን ይፈልጉታል"
~ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
"በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል" ዮሐ 10:27
ጥያቄ ወይ አስተያየት ካለዎት በዚህ አድራሻ ይላኩልን:- @The_Good_Shepherdbot

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-03-27 10:06:51
“እርሱንና የትንሣኤውን ኃይል እንዳውቅ፥ በመከራውም እንድካፈል፥ ወደ ሙታንም ትንሣኤ ልደርስ ቢሆንልኝ፥ በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ።”

ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች
ምዕ 3፥10-11
335 views07:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-17 22:41:39 ቫላንታየን ዴይ የዝሙት ደውል!

/በበጎ ፈቃዱ/

“በበጎ ፈቃዱ እንደ ወደደ ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ለእርሱ ልጆች ልንሆን አስቀድሞ ወሰነን ።” ኤፌ. 1 ፡ 5 ።

ቫላንታይን ዴይ /የፍቅረኞች ቀን/ እየተባለ የሚጠራው የጣኦት አምልኮ ፣ ዘመናዊ ስያሜና ልምምድ አግኝቶ በወጣቶች ዘንድ እየተከበረ ይገኛል ። ወጣቶችም የሚያከብሩት ራሳቸውን በማዋረድ በመሆኑ በዓሉ መንፈሳዊ ክብር የሌለው ነው ። በዚህ ቀን ወጣቶች ቀይ ለብሰው ፣ ቀኑን ሲውሉ ምሽቱን ደግሞ ደማቸው ፈስሶ ፣ ድንግልናቸውን አጥተው ያድራሉ ። በቀይ ባንዲራ የዋለው ተረፈ ጣኦት ፣ ቀይ መስመር ውስጥ በማስገባት የወጣቶችን ሕይወት ይቀጫል ። በዚህ ቀን ዘላቂ ሕይወታቸው የሚበላሽባቸው ወጣቶች የትየለሌ ናቸው ። የጥንት የጣኦት አምልኮዎች ከዝሙት ጋር ጥብቅ ግንኙነት አላቸው ። ዝሙት ሥጋን ፣ ነፍስንና መንፈስን የሚያረክስ በመሆኑ የአጋንንት ትልቅ መሥዋዕት ነው ።

ወደ መንፈሳዊው ዓለም ስንመጣ የፍቅር ቀን የሚባል የለም ። ፍቅር ቀን የለውም ፣ ዘላለማዊ ነው ። ያ ፍቅርም እግዚአብሔር ነው ። መንፈሳዊው ፍቅር ቀይ በመልበስ የተገለጠ ሳይሆን ደሙን ባፈሰሰልን በክርስቶስ ሞት ላይ ያበበ ነው ። ይህ ፍቅርም ወደ ንጽሕና የሚጠራ ፣ ዝሙትን የሚረታ ነው ። ወጣቶችንም እንኳን የሚጎዳውን ኃጢአት ለመተው ይቅርና ሕይወታቸውን ለሰማዕትነት ለመስጠት የሚያስጨክን ፣ እነ ቅዱስ ጊዮርጊስን ለሰማዕትነት ያበቃ ነው ።

ባሕል የሚመስሉ ጎጂ ነገሮች ፣ በዓል የሚመስሉ ውድቀቶች ፣ ከሌላው ዓለም የተቀዱ የሚመስሉ ዘመናዊነት የተላበሱ የደፈረሱ ውኃዎች ሊታሰብባቸው ይገባል ። በዚህ በፍቅረኞች ቀን የመገናኛ ብዙኃን ሳይቀሩ አልጋ ቀረሽ ወሬ እያወሩ ፣ ስለተላላፊ በሽታዎች በሚነገርበት ዘመን ሞራልና ጤናው የወደቀ ትውልድ እያተረፉ ናቸው ። ይልቁንም ስሜት እንጂ እውቀት የሌላቸውን ወጣቶች በጭድ አጠገብ ያለ እሳት እየሆኑባቸው ያሉ ሚዲያዎች በሕግ ሊጠየቁ ፣ በሃይማኖት ሊወገዙ ይገባቸዋል ።

እኛ የምናከብረው የፍቅር ቀን የለንም ። ያከበረን ፍቅር ግን አለ ። ይህንንም ፍቅር የምናከብረው ዘወትር ለሌሎች መሥዋዕት በመሆንና በተለወጠ ሕይወት ነው ።

የእግዚአብሔር ፍቅር በጎ ፈቃድ ያለው ነው ። የዓለም ፍቅር ግን ክፉ ምርጫ ያለበት ነው ። ፍቅር እግዚአብሔር ነውና እግዚአብሔርን የሚያሳዝን ግብር ሁሉ የፍቅር ስም የተሰጠው ውድቀት ነው ።

የኤፌሶን መልእክት ትርጓሜ /8

ዲ.አ.መ
የካቲት 10 ቀን 2014 ዓ.ም.

እባካችሁ ለሌሎች አካፍሉት
533 views19:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-06 16:15:28
" የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን?" (1ኛቆሮ3:16)

ወንድሞቼ ለቤዛነት ቀን የታተምንበተትን ቅዱሱን የእግዚአብሔር መንፈስ አናሳዝናን::ክርስቶስን ከማወቃችን(ማቴ 16:16)  አስቀድሞ ማን እንደሚመራን እንዴት እንደምንመራ ወዴትም እንደምንሄድ አናውቅም ነበርና በስጋ ፈቃድና በዓይን አምሮት በበዛም የአለም ጥበብ ተወስደን ነበር ። አሁን ግን ርቀን የነበርን እኛ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆነን ልጆች ሆነናልና " ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ማለት የእግዚአብሔር ወራሾች ነን፥ አብረንም ደግሞ እንድንከበር አብረን መከራ ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን።" (ሮሜ 8:17)

እናም በመደንዘዝ በመመኘትም ርኩሰትን ሁሉ ያደረግንበት ዘመን ይብቃን። ለእውነት ለሚሆን ፅድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠርንበትን ሰው በእውነት እንልበሰው።
ወንድሞቼ ሆይ ያለ ተጋድሎና ቅድስናንና ንፅህናን ተስፋ ባለማድረግ ለምን ክርስቲያኖች ተብለን ብቻ እንኖራለን?  ቅዳሴያችን እንደሚያሳስበን ክቡር ስንሆን ልብ እንደሌለው እንደ እንስሳ አንሁን: ንጉስ ስንሆን በፈቃዳችን ራሳችንን በማዋረድ ባሪያ አንሁን ጌቶቻችን ያልሆኑም አይግዙን። (ከአንድ ከክርስቶስ ኢየሱስ በቀር) ; ሁሉ ያለን (ከክርስቶስ በቀር ሌላ ነገር ከሌለህ እንዴት ደስ ይላል) ባለፀጋዎች ስንሆን ራሳችንን ነዳይ አናድርግ" (መፅሐፈ ቅዳሴ|ቅዳሴ አትናቴዎስ ከቁጥር ፳-፳፰ )

 +| ዲያቆን አቤሴሎም ድንቅአለም 
https://t.me/orthodoxy_life
https://t.me/orthodoxy_life
489 views13:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-02 00:12:17
ይህች ከላይ በፎቶ የምትመለከቷት ወጣት ቸስሊ ክሪስት (Cheslie Kryst) ትባላለች። 30 ዓመቷም ነበረ ። ከNorth Carolina የህግ ተመራቂና አሜሪካዊት ሞዴል ነች ፣ እ.አ.አ በ2019 የአሜሪካ የቁንጅና ውድድር አሸናፊም ነበረች፣ የቴሌቪዥን የመዝናኛ ፕሮግራም መሪ የነበረችው ቸስሊ ስለ ውበቷ ብዙ ተብሎላታል። በዚህም ያተረፈችው እውቅና እና ክብር ብዙዎችን አስደምሟል። ባለፀጋም አድርጓቷል ። በሚዲያውም ዘርፍ ከታዋቂ ሰዎች ጋር የመስራት እድል የገጠማት ይቺህ እንስት ከአንድ ቀን በፊት ከምትኖርበት አፓርታማ እራሷን ፈጥፍጣ ገድላለች።

ወዳጆች ሆይ የምንሮጥለትና የሰበሰብነው ዝናና ክብር ፣ ገንዘብና እውቀት የደስታ ምንጭ ፣ የመኖር ዋስትና አይደለም "ያለ እርሱ ፈቃድ የበላ ደስ ብሎትም ተድላን የቀመሰ ማን ነው?" እንዲል ቃሉ። ነገር እግዚአብሔርን ደስ በማሰኘት ውስጥ ሁሉም አለ "እርሱም ደስ ለሚያሰኘው ሰው ጥበብንና እውቀትን ደስታንም ይሰጠዋል" በሌላም ስፍራ "አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል" (ፊል 4፥7)። ሰለዚህ ፍቅር ከሆነው አምላክ ጋር እንጣበቅ!

ያለበለዛ ያለእግዚአብሔር ፈቃድ ለሚኖር ፦ "ለኃጢአተኛ ግን እግዚአብሔርን ደስ ለሚያሰኘው ሰው ይሰጥ ዘንድ እንዲሰበስብና እንዲያከማች ጥረትን ይሰጠዋል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነፋስንም እንደ መከተል ነው" (መክ 2: 25-26)

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ ማረን!
https://t.me/orthodoxy_life
https://t.me/orthodoxy_life
440 views21:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-27 12:40:57
(1 ቆሮ 7፥32-36 )
------------
"ነገር ግን ያለ አሳብ ልትኖሩ እወዳለሁ። ያላገባው ጌታን እንዴት ደስ እንዲያሰኘው የጌታን ነገር ያስባል፤

ያገባው ግን ሚስቱን እንዴት ደስ እንዲያሰኛት የዓለምን ነገር ያስባል፥ ልቡም ተከፍሎአል።

ያልተጋባች ሴትና ድንግል በሥጋም በነፍስም እንዲቀደሱ የጌታን ነገር ያስባሉ፤ የተጋባች ግን ባልዋን እንዴት ደስ እንድታሰኘው የዓለምን ነገር ታስባለች።

ይህንም ለራሳችሁ ጥቅም እላለሁ፤ በአገባብ እንድትኖሩ ሳትባክኑም በጌታ እንድትጸኑ ነው እንጂ ላጠምዳችሁ ብዬ አይደለም።"
!
https://t.me/orthodoxy_life
420 views09:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-13 22:50:15
እርስ በእርስ እየተጯጯህን ለምን መሰማማት አቃተን?
+
አባ ዮሐንስ(John of krnostadt) እንዲህ አሉ ፦ "አንድ አባት ለደቀ መዛሙርቶቻቸው እንዲ ብለው ይጠይቃሉ።'ለምንድነው ግን በቁጣ/በንዴት የሚነጋገሩ ሰዎች በጣም የሚጮሁት?'። ከደቀ መዛሙርቱ አንዱም 'ያው መረጋጋት ስለሚያቅታቸው ለዛ ነው የሚጮኹት' አለ። እኛአባትም መልሰዉ 'አጠገብ ለአጠገብ ሆነው ለምን ይጮሀሉ ቀስ ብለው ማውራት እየቻሉ?' ብለው ደግሞ ይጠይቁና ሁሉም የራሱን ሐሳብ ከሰጠ በኋላ እርሳቸው እንዲህ ብለው መለሱ። 'ሁለት ሰዎች በተናደዱና በተቆጡ ሰአት እርስ በእርሳቸው ልባቸው ይራራቃል ያን ጊዜ ደግሞ ያንን እርቀትን ለመሸፈን እጅግ ይጯጯሃሉ። በተናደዱ ቁጥርም ድምፃቸው ይበልጡኑ ከፍ ይላል ያንንም ባደረጉ ጊዜ ርቀቱ ይበልጥ ይጨምራል። በተቃራኒው ደግሞ ሁለት ሰዎችም በተወደዱ ጊዜ እርስ በእርሳቸው አይጯጯሁም ቀስ ብለው ይነጋገራሉ ይጫወታሉ እንጂ። ለምን ያላችሁኝ እንደሆነ በልባቸው መካከል ያለው ርቀት በጣም ቀርቧልና በእነርሱም መካከል ያለው ርቀት ትንሽ ሆኗልና የተዋደዱ መጠን መነጋገርም ያቆማሉ። በፍቅርም ሲዋሃዱ ሳይነጋገሩ እንዲሁ ተያይተው ብቻ ይግባባሉ።"
|
ልብን ከቁጣና ጩኸት በመጠበቅና በማጽዳት ቤተ-እግዚአብሔርነቷን አፅንታ እንድትጠብቅ እንድትይዝ ማድረግ ይገባናል። አምላከ ቅዱሳን ክርስቶስ ያግዘን!

ቻናሉን ተቀላቀሉ መልዕክቶቹን ለወዳጆችዎ ያካፍሉ https://t.me/orthodoxy_life
469 views19:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-08 12:17:46
ወደ አንተ እንደተዘረጉ ያረጁ እጆች የተቀደሱ ናቸው።
397 views09:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-06 18:54:59
#ልዩ_ሚስጥር!
|
አባት በዘመን የሚቀድም ፣ በክብር የሚበልጥ ነው ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ከአባቱ በዘመን የማይቀዳደም ፣ በክብር የማይበላለጥ ነው ። እናት የወለደችው ልጅ በዓለም ሁሉ ሞልቷል ፣ እናቱን የፈጠረ ልጅ ግን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው ። ፈጣሪዋን ፈጣሪዬ ያለች ብዙ ሴት አለች ። ፈጣሪዋን የወለደችና ልጄ ብላ የጠራች ግን ድንግል ማርያም ብቻ ናት ። የጌታችን ሰው መሆን ተተንትኖ የማያበቃ ልዩ ምሥጢር ነው ። የምሥጢር ባለሟልም እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት ። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆን ታላቅ ትሕትና ፣ ለሰው ልጆች ግን ታላቅ ልዕልና ነው ። ክብር ያገኘንበት የሥጋዌው ድልድይ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት። ያለ ልክ ዝቅ ዝቅ ብሎ ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገን ።

መልካም የገና በዓል ይሁንላችሁ!
420 views15:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-05 06:43:41
ነፍሴ የወደደችህ እረኛዬ ሆይ! የተቅበዘበዝሁ እንዳልሆን፥በጎችህን ወዴት እንደምታሰማራ ንገረኝ - መሓ ፩፤፯

“መንጋህን ሁሉ በትከሻህ የምትሸከም መልካሙ እረኛ ሆይ! በጎችህን በወዴት ታሰማራለህ?... የማሰማሪያህን ቦታ እባክህ አሳየኝ፣ የእረፍቱን ውኃ አስታውቀኝ፤ ወደለመለመው መስክ ምራኝ፤ እኔ የአንተ በግ ድምጽህን እሰማ ዘንድ በስሜ ጥራኝ፤ ጥሪህ የዘላለም ሕይወት በጎ ስጦታ ይሆነኝ ዘንድ። … የድህነት መሰማሪያን አገኝ ዘንድ፣ ወደሕይወት የሚገቡ ሁሉ ሊመገቡት ከሚገባው ከሰማያዊው ማዕድም እጠግብ ዘንድ [በጎችህን] የምትመግብበትን [የምታሰማራበትን] ቦታ አሳየኝ”
[ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ፣ የመሓልየ መሓልይ ትርጓሜ]

ተቀላቀሉ: https://t.me/orthodoxy_life
346 views03:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-04 19:09:22
"በሥላሴ ገመድ ፍጹም ታስረናል ከልባችን በማይነቀል በቅንዋተ ፍቅሩ ተቸንክረናል፣ እሱ ወዶናል አይጠላንም። እኛም በእምነት ይዘነዋል አንተወውም።"

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
313 views16:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ