Get Mystery Box with random crypto!

' የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን?' ( | መልካም እረኛ

" የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን?" (1ኛቆሮ3:16)

ወንድሞቼ ለቤዛነት ቀን የታተምንበተትን ቅዱሱን የእግዚአብሔር መንፈስ አናሳዝናን::ክርስቶስን ከማወቃችን(ማቴ 16:16)  አስቀድሞ ማን እንደሚመራን እንዴት እንደምንመራ ወዴትም እንደምንሄድ አናውቅም ነበርና በስጋ ፈቃድና በዓይን አምሮት በበዛም የአለም ጥበብ ተወስደን ነበር ። አሁን ግን ርቀን የነበርን እኛ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆነን ልጆች ሆነናልና " ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ማለት የእግዚአብሔር ወራሾች ነን፥ አብረንም ደግሞ እንድንከበር አብረን መከራ ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን።" (ሮሜ 8:17)

እናም በመደንዘዝ በመመኘትም ርኩሰትን ሁሉ ያደረግንበት ዘመን ይብቃን። ለእውነት ለሚሆን ፅድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠርንበትን ሰው በእውነት እንልበሰው።
ወንድሞቼ ሆይ ያለ ተጋድሎና ቅድስናንና ንፅህናን ተስፋ ባለማድረግ ለምን ክርስቲያኖች ተብለን ብቻ እንኖራለን?  ቅዳሴያችን እንደሚያሳስበን ክቡር ስንሆን ልብ እንደሌለው እንደ እንስሳ አንሁን: ንጉስ ስንሆን በፈቃዳችን ራሳችንን በማዋረድ ባሪያ አንሁን ጌቶቻችን ያልሆኑም አይግዙን። (ከአንድ ከክርስቶስ ኢየሱስ በቀር) ; ሁሉ ያለን (ከክርስቶስ በቀር ሌላ ነገር ከሌለህ እንዴት ደስ ይላል) ባለፀጋዎች ስንሆን ራሳችንን ነዳይ አናድርግ" (መፅሐፈ ቅዳሴ|ቅዳሴ አትናቴዎስ ከቁጥር ፳-፳፰ )

 +| ዲያቆን አቤሴሎም ድንቅአለም 
https://t.me/orthodoxy_life
https://t.me/orthodoxy_life