Get Mystery Box with random crypto!

ትዳር እና ጥበባዊ ቃላቶች

የቴሌግራም ቻናል አርማ tdarenatbebawikalatoch — ትዳር እና ጥበባዊ ቃላቶች
የቴሌግራም ቻናል አርማ tdarenatbebawikalatoch — ትዳር እና ጥበባዊ ቃላቶች
የሰርጥ አድራሻ: @tdarenatbebawikalatoch
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.08K
የሰርጥ መግለጫ

ትዳር የሰው ዘር እንዳይቋረጥ ትልቅ ሚና ይጫወታል የህዎት ግብህን አስምር

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 09:07:17 ተከታተሉ





237 views06:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 09:10:23





ሰብስክራይብ
ሼር
ላይክ
ኮሜንት
በማድረግ ይህን ቻናል ተደራሽነቱን በማስፋት ተባበሩን
217 views06:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 16:09:34
ተወዳጁ ወንድማችን ኡስታዝ ሀቢብ ኢስማዒል ኒካህን በማሰር ወደ ትዳር ተቀላቅለዋል مبارك لكم
بارك الله لكما وبارك عليكما وجمع بينكما في الخير
ያማረ እና የሰመረ ትዳር ያድርግላችሁ
363 views13:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 18:51:18






ሊላህ ብለን እየገባን ቻናሉን
ሰብስክራይብ እናድርግ
ላይክና ኮሜንት እንድሁም
ሼር
ሼር
ሼር
በማድረግ ኸይርን እናባዛ
463 views15:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 09:53:53 #የዊላዳው_ጎህ

በይፋው መቀነት በጋሃዱ ዓለም፣
የደከመ ጉልበት የራፈቀ አቅም፣
ከልቡ አይስቅም፣
ጦሀን ያልወደደ በቀጣዩ ዓለም ዘውድ አይታጠቅም።


ደግሞ በኛው ዘመን...
በዚህ ሰበህለላ በዓለመ-ምጸት፣
በድቅድቅ ጨለማ ደግሞ በኛ ቁጭት፣
የዘይኔ ዊላዳ ሰንደቅ ባይተክልበት፣
የህይወት ሙናዋን እድሜ የሚፈትት፣
የዝሆን ማርጣ ነው ዘቅዝቆ ሚገትት።

ያኔ ድሮ
በዚያኛው ጎህ ደግሞ በጥንቱ ሰመመን፣
ከዕልፍ አመት በፊት በዚያ ቋያ ዘመን፣
በሸውቅ አስወገዱት የምድርን ዳረመን።


የሰይዲን አንገት ቢያዘልቀው ዊላዳው፣
ማራኪው ጠረኑ ዓለምን አወደው፣
ሚስክንም غሊያ
ሽቶ የተባለን ጠራርጎ ወሰደው።


የኔው ወገን ደግሞ በሸውቅ የሰከረው፣
መውደዱ መዲና ሊነዳው ሞከረው፣
ወራትን ሰንቆ ዙል ሂጃን ሲጠብቅ፣
አያየው ነጎደ ስንቁን ሲያጠባብቅ፣
ያኔ ከድሮው ሸንቁጦት ኖሮ፣ የፍቅሩ ለበቅ፣
ለትቶ ጅስሙ ቢበን እንደብቅ፣
ሰከን አረገው የዊላዳው ጎህ ተራ እንዲጠብቅ።


ከዚያ ከዚያማ ቡኋላ
አይቶት ያንን አወራ በህልሙ ጋሞራ፣
ያ ውቡ ከንፈሩ ተላውሶ ሲያወራ፣
እንኳን ያዳመጠው ሙትን ሲያንሰራራ፣
በትንፋሹ ዓለም አብቦ ጎመራ፣
የመውሊዱ ሎሌ ታጥቆ ተሰማራ።


ስንቱ ወዳጅ ነበር...
ስንቱ ወዳጅ ነበር በፍቅር ያጓራ፣
እጅግ ሲዘረጋ ሲረበብ ሲጣራ፣
እስትንፋሱ በሮ ከንፎ እንዳሞራ፣
በዊላዳው ሽታ ከሞት አንሰራራ።


ባይሆን ነው 'ሚደንቀው...
ለእዝነት ተልከው ለሰውም ለጅኑ፣
በመውሊዱ ለሊት ክህደቶች ቀጠኑ፣
እልፍ አዕላፍ ወልጋዶች በነቢ ተቃኑ።

ስለዚህም አሁን...
ህይወት ያለወትሮው በጌጥ አሸብርቋል፣
ዓለም ደሟ ባርቋል፣
ጽልመት ያለበሳት ዳመናው ተገልጧል
የዘይኔ ዊላዳ የብርሃን ጎህ ቀዷል።
ከኔ አንጻር እንኳን፣
ዓይሼ ተቀላጥፏል በመውሊዱ ድንኳን።
ለነገሩ...
የራምሳቸው ሆታ የበርዘንጁ እጣን፣
እንኳን ደርዘኛውን ያድነው የለ እንዴ
መረን የወጣውን።


ከፊሉ ሰው ደግሞ...
ጥንት የጎሰመው የፍቅሩ ቃሬዛ፣
ሙሐቻ አስመስሎት ህይወት እንደዋዛ፣
መውሊዱ ቢመጣ ነቁን እያወዛ፣
ቆቤ ቅል ይመስል እያደር ወረዛ።

እናማ ወዳጆቼ...
አርምሞ ሞልቶቦት ጥንት አቅም ላጣው፣
ለዚህ የክት ዓለም ለክህደት ባላንጣው፣
የዘይኔ መውሊድ ነው ቅናቻን ያመጣው።


ገጣሚ አንዋር ዩሱፍ







#የቃልት_መፍቺያ(ካስፈለገ)

የራፈቀ=አቅም አጣ፣ደከመ
የሚፈትት=የሚቆረሰ፣የሚገመስ
ሙና=ብላቴና፣ህጻን
የዝሆን ማርጣ= የዝሆን ጭራ
ቋያ=ሰደድ
ዳረመን=እከክ፣ፎከት
ለበቅ=ልምጭ፣አርጩሜ
ለትቶ=ደከሞ፣ዝሎ
ሲረበብ=ሲዘረጋ
መረን=ባለጌ፣ስድ
አርምሞ=ጸጥታ፣ዝምታ
ነቅ=የፈካ መሬት(የተሰነጣጠቀ)
ሙሐቻ= የማይጠራ የሊጥ ማቡኪያ
1.0K views06:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 13:34:51
ዘይኑ ነብዬ ነብዬ
ዘይኑ ነብዬ ነብዬ
ሰለሏህ አለይህ ወሰለም
………………
ዚያራሁን ባልታደል፣
ተዚሁ እንዴት ነሁ ልበል።

እንዴት ነው የረውዳ አዳራሽ፣
መከዳው የነቢ ፊራሽ።

የሒጃዝ ቀበሌው እጣን፣
ሸውቁ እንደ ጅራፍ የቀጣን።

እንዴት ነው ቁባው ሚናራው፣
ኸበሩ ተሩቅ ሚጠራው።

እንዴት ነው ነቢዬ ጓዳው፣
መስጂዱ ጣራ ግድግዳው።

እንዴት ነው መስኮቱ በሩ፣
እንዴት ነው ግቢው አጥሩ።

እንዴት ነው ሳሩ ቅጠሉ፣
ጠንቷል ሩሔ መንጠልጠሉ።

ለምለሙ ጉዝጓዝ ቀጤማው፣
እሱን ነው ነፍሴን የጠማው።

እንዴት ነው ሽቶ ሽታዬ፣
ርቀውኝ ባሰ ስቃዬ።

ኸበሩ ሲወሰውሰኝ፣
ነውሬ ግን ተዚዉ መለሰኝ።

ስምሁን ልከርር ዘላለም፣
ብሶቴን ላውጋ በቀለም።

ቆምኩኝ ሆኜልሁ ብቸኛ፣
ስምሁን አርጌ ጓደኛ።

ስቃይ ነው የሩቅ ሰው መውደድ፣
ታላዩት አይኖርም መብረድ።

አይሰላም ሀያት ያላንቱ፣
ጭልም ነው ቀኑም ምሽቱ።

እንዴት ነው ከንዜ የጠይባው፣
ናፍቆቱ ጉቶን ያስነባው።

እንዴት ነው ጎጆ ያስሐባው፣
ኸበሩ ሆድ የሚያባበው።

አንቱ የጂብሪል ባለሟል፣
ወዳጅሁ ሰው ሀገር ቷሟል።

ፈውሱ ሆኑና ሙስጠፋ፣
ታማሚ መከራው ከፋ።

ፈውሱ ሆነ ሙሐመድ፣
ተገዷል ዳዒም ለመንደድ።

ናፍቄቅ ቆምኩኝ ተደጄ፣
ስጠብቅ የሩህ ወዳጄ።

ታልሔድኩኝ እሱም ታልመጣ፣
እስተመች እንዲህ ልቀጣ።
°°°°°°°°°°°
ዘይኑ ነብዬ ነብዬ
ዘይኑ ነብዬ ነብዬ
ሰለሏህ አለይህ ወሰለም
1.2K views10:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 11:03:40 ዘምዘም ሰፈራቸዉ መግቢያ እስከሚደርሱ ድረስ ምንም አላወራችም ዃሊድ ግን ሰፈሩ አዲስ አልሆነበትም ግን ወደ ሆስፊታል ሚቸኩል በማስመሰል <እዚ ጋር ብናወርድሽሰ
<<ዘሙ አስቀድማ አላህ ይስጥህ ጀዛከላህ በማለት ወረደች ፈዲላንም በቃ ነገ አላህ ካለ እመጣለዉ ብላት ወደ ሰፈሯ መጟዝ ጀመረች.....┏•━•━•━ ❸ ━•━•━•┓
#ክፍል_ሶስት[❸]
┗•━•━•━ ❸ ━•━•━•┛

ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!

አሁኑኑ ይቀላቀሉ ⇩⇩
Telegram chanal

جمعية المشاريع الخيرية الإسلامية
https://t.me/joinchat/R_QhFIbufEC65ol6
865 views08:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 11:03:27 ". #ልጅነቴ ".

. ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.
ይከታተሉ ይማሩበታል
┏•━•━•━ ❷ ━•━•━•┓
#ክፍል_ሁለት[❷]
┗•━•━•━ ❷ ━•━•━•┛
""በዚ መሀል መተንፈስም እያቃታቸዉ ስለነበር ኻሊድ በድንጋጤ ጮሆ ወደ ኦስፒታል ይዘዋቸዉ መጟዝ ጀመሩ

"ፈዲላና ዘምዘም" ስለሚቀሩት ቁረአን የተነጋገሩ ሳያዉቁት እቤት ገቡ ገና ከመድረሳቸዉ በዝግታ ዘምዘም አሰላም አለይኩም ብላ ሳትጨርስ አባትየዉና እናቷ ዋአሌይኩም ወሰላም ጥቡቛና ትሁቷ ልጄ ብለዉ ተቀበሏት ፈዲላ በዘምዘም ቤተሰቦች ከልቧ ትቀናለች ምናለ የነሱ ልጅ በሆንኩኝ እያለች ትመኛለች ገብተዉ ዘምዘም የራሷ ክፍል ገብተዉ ተቀመጡ ዘምዘምም መጣዉ ብላ ከክፍሏ ወጣች ና ኡሚ ብላ በዝግታ ጠራቻትና
<ወዬ የኔ ልጅ
<<ፎዙ የለችምንዴ
<አይ አንቺ እንደዉ ያለሷ አይሆንልሽም አይደል መቼስ የእህትሽ ነገር አይሆንልሽም ከእንግዳ ጋር ሆነሽ አይደል
<< እረ ኡሚዬ ከጓደኛዬ ጋርኮ ላስተዋዉቃት ነበር
<እሷኮ አንቺ ከመግባትሽ ቀደም ብላ ነበር ስልክ ሲደወልላት እያወራች የወጣችዉ
<<አይ በቃ ሜካፕ ኖሮባት ይሆናል ኡሚዬ በቃ ጓደኛዬን እንዳይደብራት ኩኪስ ነገር ልወስድም ነበር የመጣሁት ብዬ ለሻይ ዉሀ ጥጄ ወደ ክፍሌ ስመለስ ፈዱ ከቦታዋ የለችም ግራ በመጋባት ወደ ዉጪ ወጣች የዘሙ አባት ዉጪ ቁጭ ብለዉ ፂማቸዉን እየነካኩ በአንድ እጃቸዉ ደሞ ተስቢ ይዘዉ ከሆነ ጥላ ስር ተቀምጠዋል
<<አቢ አብራኝ የገባችዉ ልጅስ
<የኔ ልጅ አሁንኮ እየተቻኮለች ወጣች
<<እሺ አባዬ በቃ እደዉልላታለሁ ብዬ ወደ ክፍሌ ተመልሼ ገባሁ ልደዉል ስልኩን ሳነሳ ፈዲ ቀድማኝ ደዉች የኔ ዉድ ጓደኛ ከእህቴ ዉጪ የምወዳትና የምቀርባት ጓደኛዬ ብትኖር ፈዲላ ናት ስወዳትኮ ስልኩን አነሳሁት
<<ሄለዉ አሰላም አለይኩም ፈዱ
<ወአሌይኩም ወሰላም ዘሙዬ በጣም ይቅርታ ሳልነግርሽ በመሄዴ
ምነዉ በሰላም ነዉ የተፈጠረ ችግር አለንዴ ብላ ዘምዘም በቀዘቀዘ ድምፅ ጠየቀቻት?: ፈዲላም ቀጠል አድርጋ አባቴ ታሞ ወንድሜ ደዉሎልኝ ነዉ ብላ ልትሰዘጋዉ ስትል ዘምዘም ቆይ መጣዉ የት ነሽ ስትላት ከእናንተ ሰፈር መዉጫ ላይ ነኝ ታክሲ እየጠበኩ ነዉ።
በቃ ፈዱ ጠብቂኝ እመጣለዉ ብላት ለባብሳ ለቤተሰቦቿ ነግራት ወጣች
በመዉጣት ላይ እንዳለች ወደ በር አካባቢ ስትደርስ ፎዚያ ወደ ግቢ ስትገባ ተገናኙ ፎዚያ ፊቷ የደነገጠና ያዘነ ይመስል ነበር ዘምዘምም ምነዉ እህቴ ብላት አቀፈቻት ፎዙም ቀጠል አድርጋ አይ እንዲዉ ነዉ ብላት ወዴት ነዉ ምትሄጅዉ በማለት ጠየቀቻት ዘምዘምም አይ ጟደኛዬ ቤተሰቦቿ ቲኒሽ ታመዉ ነዉ እናም እሷ እየጠበቀችኝ ስለሆነ ነዉ ብላት ከአጠገቧ ተሰናብታ ወጣች

""""ኻሊድ በጣም ደንግጦ አባቱ ድንገተኛ ክፍል እንደገቡ እሱ ከበሩ በተስፋ እይታ ቆሟል ኻሊድ የቤቱ ብቸኛ ወንድ ሲሆን ብዙም በእምነቱ ጎበዝ አደለም በአባቱ ድርጅት ዉስጥ አባቱን በማገዝ ነዉ ብዙ ጊዜዉን ሚያሳልፈዉ ግን የሱ ጟደኞች በጣም መጥፎ ከመሆናቸዉ ጋር ተያይዞ እሱንም ወደ እማይሆን ነገር ነዉ ሚወስዱት ኻሊድ ዩንቨርስቲ ገብቶ ዊዝድሮ ሞልቶ ነዉ አባቱን ለማገዝ ሲል የወጣዉ እናም አባቱ ወርዶም ከነጋዴዎች ጋርም በመስራት እራሳቸዉን ከሰዉ በላይ ማድረግ አይወዱም።
<<ኻሊድ በሀሳብ እንደ ተዋጠ እናትና እህቶቹ መተዉ ማልቀስ ጀመሩ እሱም ከሀሳቡ ያነቃዉ የእናቱ የለቅሶ ድምፅ ነበር እናም የመጀመሪያ ልጅ እንደመሆኑ መጠን እንደምንም እህቶቹ ስለሚፈሩት ተቆጥቶ ዝም ካሰኛቸዉ ቡሀላ
እናቱን እንደምንም አቅፎ አባብሏት የአባታቸዉን ጤና ለመከታተል ከዲንገተኛ ክፍል አጠገብ ተቀምጠዉ
የዶክተሩን መዉጣት እየተጠባበቁ ነዉ
""ፈዲላና ዘምዘም ተገናኝተዉ በመኪና
እየሄዱ ሳለ በመሀል መንገድ ተዘጋግቶ ብዙ ቆሙ ፈዲላ የአባቷ ነገር እያስለቀሳት ነዉ ከቤተሰቦቿ በበለጠ ለአባቷ ቶሎ ነዉ ምትደነግጠዉ ነገር ግን ሀኪም ቤት እስከምትደርስ ድረስ በጣም እያለቀሰች ነዉ ዘሙ ደሞ.አቅፋ እያባበለቻት የተነገራት ሆስፒታል ደረሱ ዘሙ ፈዲላ እንዳትሮጥባት በማሰብ እጇን አጥብቃ ያዘቻትና ሂሳብ ከፍለዉ ወረዱና ወደ ዉስጥ ገቡ ቲኒሽ ገባ ብለዉ እንደተጟዙ
ፈዲላ ታላቅ እህቷን ስታያት እጇን ለዘሙ አንስታ አቅጣጫዉን ጠቆመቻት ዘሙም ፈዲላን አቅፋት ወደ ነሱ መሄድ ጀመሩ አጠገባቸዉ እንደደረሱም ፈዱ ወንድሟን ምን አገኘብኝ አባቴን ብላ በጥያቄ ማፋጠጥ ጀመረች በዚ ጊዜ ወንድሟ እንድትረጋጋ ቢነግራትም አልሰማ ብላዉ ማልቀስ ጀመረች ይሄ ሁሉ ሲሆን ዘሙ ኻሊድን አንዴም ቀና ብላአልተመለከተችዉም ነበር
እስከዛ ድረስ አይኗን ሰብራ ነበር
ኻሊድ ዲንገት ፈዲላን በጥፊ ሲመታት ዘሙ በድንጋጤ ስትመለከተዉ በሂወቷ
እንደዛ ሆና ሰዉን ተመልክታ አታዉቅም
""ዘምዘም በሂወቷ ሰዉን እንደዚ አይታና አፍጥጣ አታዉቅም በጣም ደነገጠች
የደነገጠችበት ምክንያትም አልገባትም ነገር ግን ድንጋጤዋን ቻል አድርጋ ወደ ፈዲላ በመጠጋት አቅፋት በዝግታ ታባብላት ጀመር ፈዲላ ወደ መረጋጋት ላይ ስትሆን ዘምዘምም አልሀምዱሊላህ በማለት አቀረቀረች ነገር ግን አቀርቅራም አልቻለችም ኻሊድን ሳታስበዉ ዲንገት እየተመለከተችዉ ነዉ
ቲኒሽ ታየዉና እስትግፋር ታረጋለች
ሀኪም ቤት ከገባችበት ደቂቃ ጀምሮ በተደጋጋሚ አይኗ ፊትና ዉስጥ ከቷታል የራሷ ሁኔታ ለራሱሷ ትንግርት ሆኖባታል።

""""ፎዚያ" ስልዃን በእጇ ይዛ ትደዉላለች ግን የደወለችበት ሰዉ ስልዃን አይመልስም አሁንም በተደጋጋሚ ትደዉላለች ግን የደወለችበት ሰዉ አይመልስላትም በጣም ተጨናንቃለች
የምትሄድበት ሁሉ ያጣች እስኪመስላት ድረስ ተከፍታለች የመከፋቷ ምክንያት ደሞ( በጣም የምቶደዉ የፍቅር ጟደኛዋ ነዉ የፍቅር ጟደኛዋ ብዙ ጊዜ ለሷ ቦታ ሰቷት አያዉቅም) ዛሬ እሱን ለማግኘት ቀጠሮ ነበራት ነገር ግን እሱ አደለም በሰአቱ ልታገኘዉ ስልዃንም በቅጡ ማንሳት እምቢ ብሏል. ፎዙ በጣም እያለቀሰች ነዉ አጠገቧ ማንም የለም ክፍሏን በራሷ ላይ ቆልፋለች
ስልዃን አሁንም እየሞከረች ነዉ ግን አይነሳም እሷ ተስፋ መቁረጥ አልቻለችም
በዚ ጊዜ ዘምዘም ደወለችላት ቶሎ አንስታ. ማልቀስ ጀመረች ዘምዘምም ልታረጋጋት እየሞከረች አሁን እመጣለዉ ብላት ዘጋችዉ

<<ዃሊድ በጣም ከመጨነቁ የተነሳ ደንዝዟል የፈዲላ ሁኔታም ሲያስተዉል አብራት የነበረችዉን ልጅ አያት እሷ ግን እሱ ሲመለከታት አይኗን ትሰብራለች በጭንቀት መሀል ተገረመ
ፈዲላን ሲመለከታት ተረጋግታለች
ከዚ በፊት እህቱ በቶሎ ስትረጋጋ አይቶ ስለማያዉቅ እህቴ እያደገች ነዉ መሰለኝ ብሎ ለራሱ ከልቡ ፈገግ አለ.
ዘምዘም ለፈዲላ በጆሮዋ የሆነ ነገር ነግራት ለመዉጣት ስትጣደፍ ፈዲላ ቆይ ለብቻሽ አትሄጅም ብላት ልትሸኛት ስትወጣ ዃሊድ ፈዲላን ጠራትና ሰፈሯ ቅርብ ከሆነ እኔ አደርሳታለዉ ብሎ ፈዲላን ወደ ዉስጥ ሲያስመልሳት

<ዘምዘም አይ እኔ እሷ ከተመለሰች ለብቻዬ ሄዳለዉ ጀዛከላህ ብላዉ መዉጣት ስትጀምር
<አብሽሪ አትፍሪ ብሎ የጋቢናዉን በር በመክፈት ሲጋብዛት እሷ መንገድ ቀይራ መሄድ ጀመረች
"ኻሊድ" የዘምዘም ሁኔታ ቢያስገርመዉም እህቱን ጠርቷት ሁለቱንም ከዋላ ጭኖአቸዉ ወደ ነ ዘምዘም ሰፈር መጟዝ ጀመሩ
779 views08:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 19:51:54 ልብ አንጠልጣይ የሆነ ታሪክ ነው ይከታተሉት ይማሩበታል

جمعية المشاريع الخيرية الإسلامية
https://t.me/joinchat/R_QhFIbufEC65ol6
{እዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ማለትም ሙሉ ታሪኩ ሳይሆን እዉነተኛ የተወሰነዉ ክፍሉ የእዉነተኛ ነዉ በዚ ታሪክ ላይ ፎዚያ ብዬ ለመጥቀስ የሞከርኩት ያዉ የባለታሪኳን ስምና ቦታ ቀይሬ ነዉ የፃፍኩት እኔ ፀሀፊ ፎዚያ ፈይሳ ወይም ፀሀፊ በፎዚያ አይደለሁም የታሪኩ ባለቤት እናም የኔ ስራ ፅፎ ማስተላለፍ ብቻ ነዉ እናም ለድህንነት ሲባል የታሪኩ ቦታና ስም ተቀይሯል}

┏•━•━•━ ❶ ━•━•━•┓
#ክፍል_አንድ[❶]
┗•━•━•━ ❶ ━•━•━•┛

"ልጅነት ግን ደስ ሲል ወላሂ ደስ ይላል እህቴ ጋር እስከምደርስ ድረሽ ቸኩያለሁ አዎ በጣም ነዉ የናፈቀችኝ ግን ቤት ደርሼ ሳያት የለችም እህ ቆይ አሁን እኔ ካለሷ ምግብ እንደማልበላ ታዉቅ የለንዴ አቦ በቃ ቁጭ ብዬ ልጠብቃአትአ ኡፍ ደሞ በጣም ነዉ የምትናፍቀኝ ግን እኔ ግርም የሚለኝ አንድ ነገር አለ አሁን አግብቼ ስወጣ እንዴት ልንሆን ነዉ።
""ስሜ ፎዚያ ይባላል የአስራ አንደኛ ክፍል ተማሪ ነኝ የምኖረዉ አዲስ አበባ ነዉ ከኔ በእድሜ የምታንስ እህትም አለችኝ ዘምዘም ትባላለች እሷ በአሁን ሰአት ትምርት አቋርጣ ሙተነቂብ ሆናለች እናም በቃ በጣም ነዉ የምወዳት ወላሂ ስለሷ ሳስብ እኔንጃ አንዳንዴ ሁሉም ነገር ደስ ይላል ግን ምን ያረጋል አሁን አጠገቤ የለችም እኔ እረሀቡ ሊፈጀኝ ነዉ
<<ኡሚዬ ዘሙ አሁን አትመጣም
<እቆያለሁ ብላኛለች ወይም ካልሆነ ለምን አትደዉይላትም
<<ኡሚዬ ደዉዬ ካስጨነኳት ደሞ ሀጃዋን ጥላ ትመጣለች እናም በድጋሚ ጥላኝ መሄዷ ነዉ
<የእናንተ ፍቅር ደሞ ማሻአላህ ነበር አሁን ግን በዛ እዲያ ቆይ ምንድ ነዉ አንቺ እሷ ከሌለች አልበላም እሷ ደሞ ፎዙ ከሌለች አልበላም ቆይ ቢያምሽስ
<<ልታመማ ዘሙን ምግብ ጥያት ከምበላ ብታመም እመርጣለዉ

"ይገርማል የሚገርሙ ቤተሰብ ናቸዉ ዉይ በአላህ ቆይ ሙስሊሞች ሆነዉ እንኳን የአላህን ሰላምታ ለመመለስ እንዴት ይከብዳቸዋል ያአሏህ ዛሬ ምን ሲያቀብጠኝ ነዉ እህቴን ሳልጠብቅ የወጣሁት ደሞ
<ዘሙ ስልክሽን እንኪ My life የሚል ስልክ ተደዉሎብሻል
<<እሺ ፈዱዬ ስጪኝና አንዴ እኔ አዉርቼ ልመለስ
<እሺ ግን ወንድ ነዉዴ ብላኝ በሹክሹክታ ፈዱ ጠየቀችኝ አንቺ ቀዉስ እረ እህቴ ናት ብዬ ፎዙን ስልክ ለማዉራት ወደ ዉጪ ወጣሁ ሄለዉ አሰላም አለይኩም እህቴ አፉ በይኝ ጓደኛዬ ቤተሰቦቿን ለማስተዋወቅ ይዛኝ ሄዳ ነዉ ግን ጨንቆኛል ታዉቂያለሽ ከቤተሰቦቼ ተነጥዬ ይህዉ አልናገር አልጋገርኮ ተቸገርኩ
<ወአሌይኩም ወሰላም እረ ልጄ እኔ እናትሽ ነኝ ምክንያትሽኮ በዝቶ ካርድ ከሚዘጋ ብዬ ነዉ
<<ኡሚዬ ፎዙ መስላኝኮ ነዉ እስቲ ድምጿን ልስማዉ አገናኚኝ
<እንዴ ምነዉ ዛሬ አላወራቹሁምንዴ
<<አይ እሱማ እሷ ሁለት ጊዜ ደዉላ እኔ አንዴ ደዉዬላት ነበር ግን ደሞ አሁን በጣም ነዉ የናፈቀችኝ
<እዲያ የእናንተስ በዛ እሷ ዘሙ ካልመጣች አልበላም ብላ ተኝታለች አሁን አንቺ ተቆጪልኝና እስቲ እንድትበላ አድርጊ
<<ኡሚዬ አሁን ለሷ ስጪልኝ ጭራሽ ከላበዛችዉምንዴ ቆይ ቢያማትስ
<እሺ መቼ ነዉ የምትመጪዉ ደሞ እንደማልበላ ታዉቂ የለ
<<ፎዙ ቆይ እየቀለድሽ ነዉ ከመቼዉ ከኡሚ ጆሮ ነጠቅሻት ደሞ
<እህቴ ናፍቀሽኛል ነይ በቃ እኔ አልቻልኩም
<<እሺ እመጣለሁ ግን ሰዎቹ ይከብዳሉ
<ምነዉ እህቴ ችግር አለንዴ
<<አይ የለም ግን በቃ ስመጣ አወራሻለሁ
<እሺ ዘሙዬ ደሞ ምግብ በደንብ ቢ በቃ እናም ተጫዉተሽ ቀስ ብለሽ ነይ
<<እሺ እህቴ ብዬ ስልኩን ተሰናብቼአት ዘጋሁትና ወደነ ፈዱ ቤት ተመለስኩ ይገርማል ሁሉም እንደ ብርቅዬ ሰዉ አጅበዉኝ ይመለከቱኛል እኔ እያንዳንዳቸዉን ለማየት ቀና ስል አይን ለአይን እየተገጣጠምን እኔ አቀረበርኩ የፈዱ እናት ታወራኝ ጀመር
<እኔ ምልሽ ልጄ ከመጣሽ ጀምሮ እኛ ሰንጫወት ስናወራ አንቺ ግን ዝም ብለሽ እንደተቀመጥሽ ነዉ ተጫወቺ አትፍሪ
<<እሺ እማማ እጫወታለሁ
<የምን እማማ ነዉ እናቴ በይኝ እንጂ
<<እሺ ኡሚ
<እኔ ምለዉ ተማሪ ነሽ
<<ነበርኩ
<ነበርኩ ማለት
<<አይ ኒቃብ ስለብስ ከትምርት ቤት ተባርሬ ነዉ
<ጥሩ ነዉ ለዲንሽ ይህን ዋጋ በመክፈልሽ እና በወጣትነትሽ ጥሩ ስርአት ያላት ልጅ በመሆንሽ እድለኛ እንደሆንሽ ሊሰማሽ ይገባል
<<ጀዛከላህ ኡሚ
<እና ፈዱ እንዴት ናት ጓደኝነት ላይ
<<ጥሩና ደስ የምትል ትልቅ እዉቀት የምትፈልግ ምርጥ ሴት ናት

"""አባቴ እረ በቃ እንመለስ አሁን ምን እናረጋለን ብሎ አባቱን እየለመነ ነዉ አባቱን: ኻሊድ ተወኝ እሱ ምን ቢደፍረኝ ነዉ በኔ ላይ ፈርቅ ሚይዝብኝ እኔ የአንተ አባት ማንም ሸዉዶኝኮ አያዉቅም ብሎ ብሎ እኔ ሙስጠፋን ለመሸወድ ይሞክራልንዴ እኔኮ ማን እንደሆንኩ አላወቀም እያሉ ........
"የፈዲላ አባት እየተናደዱ ነዉ የፈዲላ ወንድም "ኻሊድ" ደሞ እየለመናቸዉ ነዉ እሳቸዉ እንደዚ እያሉ ያስቡት እራሳቸዉን ስተዉ ወደቁ...
በዚ መሀል መተንፈስም እያቃታቸዉ ስለነበር ኻሊድ በድንጋጤ ጮሆ ወደ ኦስፒታል ይዘዋቸዉ መጟዝ ጀመሩ.....

┏•━•━•━ ❷ ━•━•━•┓
#ክፍል_ሁለት[❷]
┗•━•━•━ ❷ ━•━•━•┛

ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!

جمعية المشاريع الخيرية الإسلامية
https://t.me/joinchat/R_QhFIbufEC65ol6
775 views16:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 19:38:37
#የጠቢባን_ንግግር_ክፍል_2

ክፍል ሁለት

* كن في حياتك مثل رقم واحد في جدول الضرب، مهما قابل أرقام كبيرة أو صغيرة لا يعطي أحد أكثر من حجمه.
በማባዛት ሠንጠረዥ ውስጥ ሚገኘው 1 ቁጥር ትልቅም ሆነ ትንሽ ቁጥር ቢመጣ ለማንም ከመጠኑ በላይ እንደማይሰጥ ሁሉ አንተም በህይወትህ እንደዚ ሁን

*إذا كان الإنسان ذا أخلاق فهو= 1، فإذا كان الإنسان ذا جمال فأضف إلى الواحد صفرا=10، وإذا كان الإنسان ذا مال فأضف صفرا آخر=100، وإذا كان الإنسان ذا حسب ونسب فأضف صفرا آخر=1000، فإذا ذهب العدد (1) وهو الأخلاق ذهبت قيمة الإنسان وبقيت الأصفار التي لا قيمة لها».
አንድ ሰው ስነ- ምግባር ካለው እሱ = 1፤
ውብ ከሆነ በ1 ቁጥር ላይ ዜሮ ጨምር = 10፤
ባለሀብት ከሆነ ሌላ ዜሮ ጨምር = 100፤
የተከበረና የዘር ሀረጉ ጥሩ ከሆነ ሌላ ዜሮ ጨምር = 1000፤ ....ነገር ግን1 ቁጥር ማለትም ስነ-ምግባር ከነዚህ ከተነሳ የሰው ልጅ ዋጋ ይሄድና ዋጋ የሌላት ዜሮ ብቻዋን ትቀራለች።

*ليس من الصعب أن تضحي من أجل صديق ولكن من صعب أن تجد الصديق الذي يستحق التضحية.
ከባዱ ነገር ለጓደኛ ዋጋ መክፈል ሳይሆን ዋጋ ሊከፈልለት የሚገባውን ጓደኛ ማግኘት ነው።

*ليس كل سقوط نهاية فسقوط المطر أجمل البداية
ሁሉም ውድቀት የመጨረሻ አይደለም፣ የዝናብ መውደቅ ጥሩ ጀማሬ ነው።


جمعية المشاريع الخيرية الإسلامية
https://t.me/joinchat/R_QhFIbufEC65ol6
952 views16:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ