Get Mystery Box with random crypto!

ቅዱስ ድልድይ/kidus bridge

የቴሌግራም ቻናል አርማ thorniter — ቅዱስ ድልድይ/kidus bridge
የቴሌግራም ቻናል አርማ thorniter — ቅዱስ ድልድይ/kidus bridge
የሰርጥ አድራሻ: @thorniter
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 343
የሰርጥ መግለጫ

public channel

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-29 15:00:54
የመኖሪያ ቤት ሽልማት ለባለ እድለኞች ከአማራ ባንክ፡፡
ሰላም ፍቅር ጤና እንዲሆንላቹ እየተመኘን የባንኩ ቦርድ ሊቀመንበር አቶ መላኩ ፋንታ ሀገራዊ ለዉጡን ተከትሎ ሀገራዊ ኢኮኖሚዉን ለማሳደግ የተከፈተ ባንኩ ሲሆን በሀገሪቱ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ አስተዋጽዎ ለማድረግ የተጀመረ ባንክ ነዉ ብለዋል። በዚህም ባንካችን ስራ በመጀመሩ ምክንያት ለመላው ኢትዮጵያውያን መልካም ስጦታ ይዘን ቀርበናል እናም እድለኛ ለሆኑ 3 የአዲስ አበባ ወይም ከአዲስ አበባ ውጪ ለሚኖሩ ነዋሪዎች የመኖርያ ቤት አፓርታማ ልንሸልምዎ ዝግጅታችንን ጨርሰናል፡፡
1ኛ እጣ ባለ 3 መኝታ ከነሙሉ እቃው፡፡
2ኛ እጣ ባለ 2 መኝታ ከነሙሉ እቃው፡፡
3ኛ እጣ ባለ 1 መኝታ ከነሙሉ እቃው፡፡
ቀጥሎ ላሉ 100 እድለኞች የ1000 ብር ያልተገደበ የኢንተርኔት አገልግሎት ሽልማት ይኖረዋል፡፡ ይህ እጣ የሚቆየው እስከ ሰኔ 30 ሲሆን ሰኔ 30 ላይ በኮምፒዩተር እጣ አወጣጥ ዘዴ በመታገዝ እድለኞችን ሰኔ 30 ላይ በዚ ቻናል ላይ ይፋ የምናደርግ ይሆናል፡፡
ከእናንተ ሚጠበቀው ቻናላችንን መቀላቀል እንዲሁም ደግሞ ለዘመድ አዝማድዎ ለወዳጅዎ ለግሩፖች እድላቸውን እንዲሞክሩ ቢያንስ ለ60 ሰዎች ሼር በማረግ እንዲቀላቀሉ መጋበዝ ብቻ ነው፡፡ ከ 60 ሰው በላይ መጋበዝ እድልዎን ያሰፋል፡፡

መልካም እድል ከ አማራ ባንክ፡፡

@Amharabankb
@Amharabankb
@Amharabankb
51 viewsKidus torniter, 12:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-24 17:36:24
" ኢትዮጵያዊ ነኝ"

ኑሮ ቢገፋኝ ፥ የማልወድቅለት
እንዳክሱም ድንጋይ ፥ እንደ ሮሐ አለት
የግዜ ሞገድ ፥ ያላደቀቀኝ
የመከራ ዶፍ ፥ ያልነቀነቀኝ
ለሙሾ ሲያጩኝ ፥ ቅኔ የምቀኝ
በግራ ሲሉኝ ፥ የምገኝ በቀኝ
ኢትዮጵያዊ ነኝ፤

ከዋርካ ባጥር ፥ ከምቧይ ተልቄ
ከፀሐይ ባንስም ፥ ከኩራዝ ልቄ
ተምድረ በዳ ፥ ጅረት አፍልቄ
ጥሜን የምቆርጥ ፥ በፍኝ ጠልቄ
ኢትዮጵያዊ ነኝ፤

ግትር ጠላቴን ፥ ባጭር አንካሴ
ራስ ምታቴን ፥ በዳማከሴ
ነቅየ ምጥል
ነገር በነገር ፥ የማብጠለጥል
ለወዳጆቼ ፥ ዓደይ ምነቅል
በጠላቴ ፊት ፥ ቀንድ የማበቅል
ልክ እንደዋልያ ፥ ተራራ መራጭ
ልክ እንዳሞራ ፥ ብርንዶ ቆራጭ
ኢትዮጵያዊ ነኝ

እንደመሀረብ ፥ ቤቴን በኪሴ
እንደንቅሳት ፥ ተስፋን በጥርሴ
ይዤ የምዞር ከቦታ ቦታ
በዘብ በኬላ የማልገታ
ኢትዮጵያዊ ነኝ።

ገጣሚ:-በውቀቱ ስዩም
312 viewskidus Ayalneh, 14:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-20 19:59:40
፡፡፡፡፡፡፡እባክህን ይህ ሰዉ አንተ ሁን፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ፈጣሪን በጉልበቱና በእዉቀቱ የሚያግዝ፥ የሱ የሆነዉን ድርሻ ያለፍርድ የማያስነካ፥ የዋህነትንና ሞኝነትን የማይቀላቅል፥ ዝምታንና ቸልተኝነትን የማያደባልቅ፥ የራሱን ስንፈት በፈጣሪ ፈቃድ ስም የማይተካ፥ ዉሸትን በግላጭ የሚጠላ፥ ለሰዎች ይሁንታ የማይኖር፥ በእምነትም በህግም ልክ ያልሆነዉን ነገር ከመቃወም የማይቆጠብ፥ የአምላክ ፈቃድ ቢሆን ነዉ እያለ እድሜ ልኩን ባለበት የማይረግጥ ፥ ያለበትን ሁለንተናዊ እዉነታ ለምን ብሎ የሚጠይቅ፥ የመሪ እንጂ የተመሪ ስነልቦና የሌለዉ ለሃገርም ለፈጣሪም የተመቸ ሰዉ።
..................ቶ..............................
እባክህን ይህ ሰዉ አንተ ሁን። የነገዉን ህይወትህን ቁመህ አትጠብቅው። ያሉብህን የስነልቦና ክፍተቶች በሙሉ አርመህ ተነስ። ከልብ ከሆነ አንድ ሰዉ ተአምር መፍጠር ይችላል። አንድ ክርስቶስ፥ አንድ መሃመድ፥ እንድ ፕላቶ፥ አንድ ቅድስት ድንግል ማርያም፥ አንድ ማር ይስሃቅ፥ አንድ ፍሬዉድ፥ አንድ ቋረኛ፥ አንድ ቅድሱ ያሬድ ብቻዉን ተአምር ሰርቷል። አንተ ካመንክ ፈጣሪም ያምንሃል። አንተ ራስህን ካላመንከዉ ማንም አያምንህም።
ራሳችንን እንመልከት!
@stay home #stop hande shake
:::::::::::::::::::::::ቶ:::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
ቶርኔተር@ like, invite ,share በማድረግ የቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ቴሌግራም፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡:::::::::::::::::::
Share ande join https://t.me/thorniter
373 viewskidus Ayalneh, 16:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-20 19:28:58 Channel name was changed to «ቅዱስ ድልድይ/kidus bridge»
16:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-20 19:28:19 Channel name was changed to «ቅዱስ ድልድይ»
16:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-11 12:38:09
አንድአንድ ጊዜ በህይወት መንገድህ ላይ ነገሮች ከቁጥ ጥርህ ዉጭ ይሆኑብሀል ያወክቡሃል፣ያሰሙሙሃል፣ያስጨንኩሃል ፣ ያደክሙሃል።
ከመዛልህ ፣ ከመድከምህ የተነሳ ልክ የሆነዉና ያልሆነዉ እንኳ ከህሊናህ ይጠፋል ።
ከስቃይህ ብዛት እንቅልፍህ የሞት ያህል ይከብድሃል
አለኝ የምትለዉ ጠንካራ ማንነት ካንተ ሸሽቶ ጉረገኛ ብሎ ይሞግተሃል ብህልምህ በጥረትህ ሳይሆን ባለህብት ሁኔታ ይዳኛሃል ባዶ ሜዳ ላይ ጥሎ ባህር ላይ እንደዉደቀች ኩበት ግራ እና ቀኝ እያወከበ ያዋልልሃል እምነት:ጥንካሬህን:ተስፋህን ይፈትንሃል የመኖር ትረጉም ጣእሙን ያጠፋብሃል ያስጨንቅካል
ህይወት የምትደስተባት ፣ታግለህ የምታሸንፋት ፣ህልመህን የምታሳካባት ፣የምትፈልገዉን የምትኖርባት አንተነትክን የምታነግስባት ሳትሆን ...................................................................
...................................................................
.................................................................
በደራሲዉ(እግዚአብሔር )የተፃፈልክን ተዉነህ የምታልፈባት የቲያትር መድረክ እንደሆነች እንዲሰማህ ያደርግካል
840 viewskidus Ayalneh, 09:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-03-04 13:49:34
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ትዕግስት፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ጨርሶ በማታውቀው ምክንያት መኖርህን የሚፈታተኑ አበሳዎች ፤መከራወች፤ችግሮች ብዙ ናቸው፡፡ በየጊዜው ፊታቸውን እየለዋወጡ ይፋለሙሃል፤ያሳዝኑሀል፤ያስጨንቁሀል፤ያስለቅሱሀል:: ዘመንህን ሁሉ መከራን እያስተናገድክ “እንድትኖር” የተፈጠርክ ይመስል… ትበሳጫለህ፣ ተስፋ ትቆርጣለህ ፤ነገን መናፈቅ ታቆማለህ፤ዛሬ ይሰለችሀል ፤ህልምህ፤ ዓላማህ፤ ምኞትህ ከሀሳብህ ብን ብለው ይጠፉብሀል...........ባላሰብክበት ሰዓት ድንገት ተንደርድረው በመምጣት ወደ ሞትህ የሚገፈትሩ ንዴትና ብስጭቶች ስሜትህ ውስጥ ብቅ፣ ጥልቅ ማለታቸውም አይቀርም
ያኔ ታድያ አትኩሮትህን ሁሉ ትዕግስት ላይ በመሰብሰብ፣ በውስጥህ የሚንፈራገጠውን አውሬ “እረፍ” ማለት መቻል አለብህ፡፡ ትዕግስት ራስን ከመረዳት ይወለዳል:: ራስህን ስትረዳ ስሜትህን መግራት አያዳግትም:: ያኔ ንዴትና ብስጭት በለኮሱት የእሳት ነበልባል በሚፈጠር ብርሃን አካባቢህን ለማየት ትችላለህ:: መቻል ከሙከራ፣ ሙከራም ተስፋ ካለመቁረጥ የሚገኝ በረከት ነው፡፡
...''እውነት ነው መኖር ለብዞወቻችን ፈተና ነው''....
1.4K viewskidus Ayalneh, 10:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-22 11:16:59 ::::::::የቱ ነው ትክክል??????:::::::::::
ለትክክለኛነት እና ለስህተተኝነት ጥያቄዎቻችንን መልስ እንደመስጠት፤ ለእውነት እና ለሃሰት መለኪያችን መስፈርትን እንደማግኘት፤ ለማንነታችን  ትርጉምን እንደመፈልግ ህሊናን የሚረብሽ ምን ነገር አለ? ልብ እና አይምሮ ሲቃረኑ፤ እምነት እና ፍላጎት ሲጣሉ፤ ግለኝነትና ማህብረሰብ መስመር ሲለዩ ምን ማድረግ እንችላለን?በመንታ መንገድ ላይ ቆመው እንደመዋዥቅ ምን የሚያስጨንቅ ነገር አለ?

አንዳንዴ በውስጣችን ልክ የሚመስለንን ነገር እንዳናደርግ፤ ፍላጎታችንን እንዳንኖር፤ እውነተኛ ማንነታችንን እንዳናወጣ የሚያስፈሩን ብዙ ነገሮች አሉ። ልማድ እና የማህበረሰብ መስፈርት ዋነኞቹ ናቸው። ለምሳሌ በእውነተኛ ፍቅር ማንም ሰው ክርክር የለውም፤ ነገር ግን እውነተኛ ፍቅር በሚይዛቸው ሰዎች ላይ ግን ጥያዎች ይኖራሉ። በእድሜ የሚለያዩ ሰዎች ሲዋደዱ፤ በሃይማኖት የሚለያዩ ሰዎች ሲዋደዱ፤ በዘር የማይገናኙ ሰዎች በፍቅር ሲወድቁ፤ የእውነተኛ ፍቅር ትክክለኛነት በማህበረሰቡ ዘንድ ጥያቄ ወስጥ ይወድቃል።

ውሸትን እንውሰድ፤ የትኛውንም ሃይማኖት ብንከተል ውሸት ከሌሎች ሃጥያቶች እኩል ሃጥያት ነው። ነገር ግን ውሸት ቅዱስ የሚሆንባቸው አጋጣሚዎች አሉ፤ ሰዎችን ከጥፋት ለማዳን ወይም ሰዎችን ለማስታረቅ እንዋሻለን። ታዲያ ትክክለኛ እና ስህተት የምንላቸው ነገሮች እንደየሁኔታው ይለያዩ ይሆን?
1.2K viewskidus Ayalneh, 08:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-08-03 21:51:49
"የምንሰጠውን ነገር ልብ በእንበል”
። እንካችሁ የምንለውን ጥበብ፤ ምክር፤ ፍቅርና እምነት እኛ ጋር ብቻ ባለው ዋጋ ብንመዝነው፤ ለሰጠነው ሰው ዋጋው በዝቶ ሊያስደስተው ወይም አንሶ ሊያስከፋው ይችላል ፡፡
ለሰው እጅ መንሻ የገበርነው ግብር
እውቀት፤ ጥበብ፤ ፍቅር፤ ሙገሳና ክብር
ለእኛ ውድ ሆኖ እጅግ አግዝፈነው
ተቀባዩ እጅ’ላይ ፤ ተራ ኢምንት ሆኖ፤ ሲረክስ አየተነዋል!!!
ወርቅ ለተረፈው ወርቅ ሰጥተን እንዲገረም መጠበቅ ሞኝነት ነው ። ለእኛ ውድ የሆነው ነገር ለሌላውም ሰው ውድ እየመሰለን ስንቴ ተሸውደን ይሆን? ብዙ የምናውቅ መስሎን ከእኛ በላይ ለሚያውቅ ብዙ አውርተን፤ ከእኛ በላይ ለኖረ ስለኑሮ ሰብከን፤ ከእኛ በላይ ለታገለ ስለ ትግል አስረድተን፤ ከእኛ በላይ ለሚያምን ስለ እምነት ሞግተን፤ ወርቅ ለተረፈው ወርቅ ሰጥተን አናውቅም?
1.8K viewskidus Ayalneh, 18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-07-31 05:03:42
1.6K viewskidus Ayalneh, 02:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ