Get Mystery Box with random crypto!

'. #ልጅነቴ '. . ልብ አንጠልጣይ ታሪክ. ይከታተሉ ይማሩበታል ┏•━•━ | ትዳር እና ጥበባዊ ቃላቶች

". #ልጅነቴ ".

. ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.
ይከታተሉ ይማሩበታል
┏•━•━•━ ❷ ━•━•━•┓
#ክፍል_ሁለት[❷]
┗•━•━•━ ❷ ━•━•━•┛
""በዚ መሀል መተንፈስም እያቃታቸዉ ስለነበር ኻሊድ በድንጋጤ ጮሆ ወደ ኦስፒታል ይዘዋቸዉ መጟዝ ጀመሩ

"ፈዲላና ዘምዘም" ስለሚቀሩት ቁረአን የተነጋገሩ ሳያዉቁት እቤት ገቡ ገና ከመድረሳቸዉ በዝግታ ዘምዘም አሰላም አለይኩም ብላ ሳትጨርስ አባትየዉና እናቷ ዋአሌይኩም ወሰላም ጥቡቛና ትሁቷ ልጄ ብለዉ ተቀበሏት ፈዲላ በዘምዘም ቤተሰቦች ከልቧ ትቀናለች ምናለ የነሱ ልጅ በሆንኩኝ እያለች ትመኛለች ገብተዉ ዘምዘም የራሷ ክፍል ገብተዉ ተቀመጡ ዘምዘምም መጣዉ ብላ ከክፍሏ ወጣች ና ኡሚ ብላ በዝግታ ጠራቻትና
<ወዬ የኔ ልጅ
<<ፎዙ የለችምንዴ
<አይ አንቺ እንደዉ ያለሷ አይሆንልሽም አይደል መቼስ የእህትሽ ነገር አይሆንልሽም ከእንግዳ ጋር ሆነሽ አይደል
<< እረ ኡሚዬ ከጓደኛዬ ጋርኮ ላስተዋዉቃት ነበር
<እሷኮ አንቺ ከመግባትሽ ቀደም ብላ ነበር ስልክ ሲደወልላት እያወራች የወጣችዉ
<<አይ በቃ ሜካፕ ኖሮባት ይሆናል ኡሚዬ በቃ ጓደኛዬን እንዳይደብራት ኩኪስ ነገር ልወስድም ነበር የመጣሁት ብዬ ለሻይ ዉሀ ጥጄ ወደ ክፍሌ ስመለስ ፈዱ ከቦታዋ የለችም ግራ በመጋባት ወደ ዉጪ ወጣች የዘሙ አባት ዉጪ ቁጭ ብለዉ ፂማቸዉን እየነካኩ በአንድ እጃቸዉ ደሞ ተስቢ ይዘዉ ከሆነ ጥላ ስር ተቀምጠዋል
<<አቢ አብራኝ የገባችዉ ልጅስ
<የኔ ልጅ አሁንኮ እየተቻኮለች ወጣች
<<እሺ አባዬ በቃ እደዉልላታለሁ ብዬ ወደ ክፍሌ ተመልሼ ገባሁ ልደዉል ስልኩን ሳነሳ ፈዲ ቀድማኝ ደዉች የኔ ዉድ ጓደኛ ከእህቴ ዉጪ የምወዳትና የምቀርባት ጓደኛዬ ብትኖር ፈዲላ ናት ስወዳትኮ ስልኩን አነሳሁት
<<ሄለዉ አሰላም አለይኩም ፈዱ
<ወአሌይኩም ወሰላም ዘሙዬ በጣም ይቅርታ ሳልነግርሽ በመሄዴ
ምነዉ በሰላም ነዉ የተፈጠረ ችግር አለንዴ ብላ ዘምዘም በቀዘቀዘ ድምፅ ጠየቀቻት?: ፈዲላም ቀጠል አድርጋ አባቴ ታሞ ወንድሜ ደዉሎልኝ ነዉ ብላ ልትሰዘጋዉ ስትል ዘምዘም ቆይ መጣዉ የት ነሽ ስትላት ከእናንተ ሰፈር መዉጫ ላይ ነኝ ታክሲ እየጠበኩ ነዉ።
በቃ ፈዱ ጠብቂኝ እመጣለዉ ብላት ለባብሳ ለቤተሰቦቿ ነግራት ወጣች
በመዉጣት ላይ እንዳለች ወደ በር አካባቢ ስትደርስ ፎዚያ ወደ ግቢ ስትገባ ተገናኙ ፎዚያ ፊቷ የደነገጠና ያዘነ ይመስል ነበር ዘምዘምም ምነዉ እህቴ ብላት አቀፈቻት ፎዙም ቀጠል አድርጋ አይ እንዲዉ ነዉ ብላት ወዴት ነዉ ምትሄጅዉ በማለት ጠየቀቻት ዘምዘምም አይ ጟደኛዬ ቤተሰቦቿ ቲኒሽ ታመዉ ነዉ እናም እሷ እየጠበቀችኝ ስለሆነ ነዉ ብላት ከአጠገቧ ተሰናብታ ወጣች

""""ኻሊድ በጣም ደንግጦ አባቱ ድንገተኛ ክፍል እንደገቡ እሱ ከበሩ በተስፋ እይታ ቆሟል ኻሊድ የቤቱ ብቸኛ ወንድ ሲሆን ብዙም በእምነቱ ጎበዝ አደለም በአባቱ ድርጅት ዉስጥ አባቱን በማገዝ ነዉ ብዙ ጊዜዉን ሚያሳልፈዉ ግን የሱ ጟደኞች በጣም መጥፎ ከመሆናቸዉ ጋር ተያይዞ እሱንም ወደ እማይሆን ነገር ነዉ ሚወስዱት ኻሊድ ዩንቨርስቲ ገብቶ ዊዝድሮ ሞልቶ ነዉ አባቱን ለማገዝ ሲል የወጣዉ እናም አባቱ ወርዶም ከነጋዴዎች ጋርም በመስራት እራሳቸዉን ከሰዉ በላይ ማድረግ አይወዱም።
<<ኻሊድ በሀሳብ እንደ ተዋጠ እናትና እህቶቹ መተዉ ማልቀስ ጀመሩ እሱም ከሀሳቡ ያነቃዉ የእናቱ የለቅሶ ድምፅ ነበር እናም የመጀመሪያ ልጅ እንደመሆኑ መጠን እንደምንም እህቶቹ ስለሚፈሩት ተቆጥቶ ዝም ካሰኛቸዉ ቡሀላ
እናቱን እንደምንም አቅፎ አባብሏት የአባታቸዉን ጤና ለመከታተል ከዲንገተኛ ክፍል አጠገብ ተቀምጠዉ
የዶክተሩን መዉጣት እየተጠባበቁ ነዉ
""ፈዲላና ዘምዘም ተገናኝተዉ በመኪና
እየሄዱ ሳለ በመሀል መንገድ ተዘጋግቶ ብዙ ቆሙ ፈዲላ የአባቷ ነገር እያስለቀሳት ነዉ ከቤተሰቦቿ በበለጠ ለአባቷ ቶሎ ነዉ ምትደነግጠዉ ነገር ግን ሀኪም ቤት እስከምትደርስ ድረስ በጣም እያለቀሰች ነዉ ዘሙ ደሞ.አቅፋ እያባበለቻት የተነገራት ሆስፒታል ደረሱ ዘሙ ፈዲላ እንዳትሮጥባት በማሰብ እጇን አጥብቃ ያዘቻትና ሂሳብ ከፍለዉ ወረዱና ወደ ዉስጥ ገቡ ቲኒሽ ገባ ብለዉ እንደተጟዙ
ፈዲላ ታላቅ እህቷን ስታያት እጇን ለዘሙ አንስታ አቅጣጫዉን ጠቆመቻት ዘሙም ፈዲላን አቅፋት ወደ ነሱ መሄድ ጀመሩ አጠገባቸዉ እንደደረሱም ፈዱ ወንድሟን ምን አገኘብኝ አባቴን ብላ በጥያቄ ማፋጠጥ ጀመረች በዚ ጊዜ ወንድሟ እንድትረጋጋ ቢነግራትም አልሰማ ብላዉ ማልቀስ ጀመረች ይሄ ሁሉ ሲሆን ዘሙ ኻሊድን አንዴም ቀና ብላአልተመለከተችዉም ነበር
እስከዛ ድረስ አይኗን ሰብራ ነበር
ኻሊድ ዲንገት ፈዲላን በጥፊ ሲመታት ዘሙ በድንጋጤ ስትመለከተዉ በሂወቷ
እንደዛ ሆና ሰዉን ተመልክታ አታዉቅም
""ዘምዘም በሂወቷ ሰዉን እንደዚ አይታና አፍጥጣ አታዉቅም በጣም ደነገጠች
የደነገጠችበት ምክንያትም አልገባትም ነገር ግን ድንጋጤዋን ቻል አድርጋ ወደ ፈዲላ በመጠጋት አቅፋት በዝግታ ታባብላት ጀመር ፈዲላ ወደ መረጋጋት ላይ ስትሆን ዘምዘምም አልሀምዱሊላህ በማለት አቀረቀረች ነገር ግን አቀርቅራም አልቻለችም ኻሊድን ሳታስበዉ ዲንገት እየተመለከተችዉ ነዉ
ቲኒሽ ታየዉና እስትግፋር ታረጋለች
ሀኪም ቤት ከገባችበት ደቂቃ ጀምሮ በተደጋጋሚ አይኗ ፊትና ዉስጥ ከቷታል የራሷ ሁኔታ ለራሱሷ ትንግርት ሆኖባታል።

""""ፎዚያ" ስልዃን በእጇ ይዛ ትደዉላለች ግን የደወለችበት ሰዉ ስልዃን አይመልስም አሁንም በተደጋጋሚ ትደዉላለች ግን የደወለችበት ሰዉ አይመልስላትም በጣም ተጨናንቃለች
የምትሄድበት ሁሉ ያጣች እስኪመስላት ድረስ ተከፍታለች የመከፋቷ ምክንያት ደሞ( በጣም የምቶደዉ የፍቅር ጟደኛዋ ነዉ የፍቅር ጟደኛዋ ብዙ ጊዜ ለሷ ቦታ ሰቷት አያዉቅም) ዛሬ እሱን ለማግኘት ቀጠሮ ነበራት ነገር ግን እሱ አደለም በሰአቱ ልታገኘዉ ስልዃንም በቅጡ ማንሳት እምቢ ብሏል. ፎዙ በጣም እያለቀሰች ነዉ አጠገቧ ማንም የለም ክፍሏን በራሷ ላይ ቆልፋለች
ስልዃን አሁንም እየሞከረች ነዉ ግን አይነሳም እሷ ተስፋ መቁረጥ አልቻለችም
በዚ ጊዜ ዘምዘም ደወለችላት ቶሎ አንስታ. ማልቀስ ጀመረች ዘምዘምም ልታረጋጋት እየሞከረች አሁን እመጣለዉ ብላት ዘጋችዉ

<<ዃሊድ በጣም ከመጨነቁ የተነሳ ደንዝዟል የፈዲላ ሁኔታም ሲያስተዉል አብራት የነበረችዉን ልጅ አያት እሷ ግን እሱ ሲመለከታት አይኗን ትሰብራለች በጭንቀት መሀል ተገረመ
ፈዲላን ሲመለከታት ተረጋግታለች
ከዚ በፊት እህቱ በቶሎ ስትረጋጋ አይቶ ስለማያዉቅ እህቴ እያደገች ነዉ መሰለኝ ብሎ ለራሱ ከልቡ ፈገግ አለ.
ዘምዘም ለፈዲላ በጆሮዋ የሆነ ነገር ነግራት ለመዉጣት ስትጣደፍ ፈዲላ ቆይ ለብቻሽ አትሄጅም ብላት ልትሸኛት ስትወጣ ዃሊድ ፈዲላን ጠራትና ሰፈሯ ቅርብ ከሆነ እኔ አደርሳታለዉ ብሎ ፈዲላን ወደ ዉስጥ ሲያስመልሳት

<ዘምዘም አይ እኔ እሷ ከተመለሰች ለብቻዬ ሄዳለዉ ጀዛከላህ ብላዉ መዉጣት ስትጀምር
<አብሽሪ አትፍሪ ብሎ የጋቢናዉን በር በመክፈት ሲጋብዛት እሷ መንገድ ቀይራ መሄድ ጀመረች
"ኻሊድ" የዘምዘም ሁኔታ ቢያስገርመዉም እህቱን ጠርቷት ሁለቱንም ከዋላ ጭኖአቸዉ ወደ ነ ዘምዘም ሰፈር መጟዝ ጀመሩ