Get Mystery Box with random crypto!

ልብ አንጠልጣይ የሆነ ታሪክ ነው ይከታተሉት ይማሩበታል جمعية المشاريع الخيرية الإ | ትዳር እና ጥበባዊ ቃላቶች

ልብ አንጠልጣይ የሆነ ታሪክ ነው ይከታተሉት ይማሩበታል

جمعية المشاريع الخيرية الإسلامية
https://t.me/joinchat/R_QhFIbufEC65ol6
{እዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ማለትም ሙሉ ታሪኩ ሳይሆን እዉነተኛ የተወሰነዉ ክፍሉ የእዉነተኛ ነዉ በዚ ታሪክ ላይ ፎዚያ ብዬ ለመጥቀስ የሞከርኩት ያዉ የባለታሪኳን ስምና ቦታ ቀይሬ ነዉ የፃፍኩት እኔ ፀሀፊ ፎዚያ ፈይሳ ወይም ፀሀፊ በፎዚያ አይደለሁም የታሪኩ ባለቤት እናም የኔ ስራ ፅፎ ማስተላለፍ ብቻ ነዉ እናም ለድህንነት ሲባል የታሪኩ ቦታና ስም ተቀይሯል}

┏•━•━•━ ❶ ━•━•━•┓
#ክፍል_አንድ[❶]
┗•━•━•━ ❶ ━•━•━•┛

"ልጅነት ግን ደስ ሲል ወላሂ ደስ ይላል እህቴ ጋር እስከምደርስ ድረሽ ቸኩያለሁ አዎ በጣም ነዉ የናፈቀችኝ ግን ቤት ደርሼ ሳያት የለችም እህ ቆይ አሁን እኔ ካለሷ ምግብ እንደማልበላ ታዉቅ የለንዴ አቦ በቃ ቁጭ ብዬ ልጠብቃአትአ ኡፍ ደሞ በጣም ነዉ የምትናፍቀኝ ግን እኔ ግርም የሚለኝ አንድ ነገር አለ አሁን አግብቼ ስወጣ እንዴት ልንሆን ነዉ።
""ስሜ ፎዚያ ይባላል የአስራ አንደኛ ክፍል ተማሪ ነኝ የምኖረዉ አዲስ አበባ ነዉ ከኔ በእድሜ የምታንስ እህትም አለችኝ ዘምዘም ትባላለች እሷ በአሁን ሰአት ትምርት አቋርጣ ሙተነቂብ ሆናለች እናም በቃ በጣም ነዉ የምወዳት ወላሂ ስለሷ ሳስብ እኔንጃ አንዳንዴ ሁሉም ነገር ደስ ይላል ግን ምን ያረጋል አሁን አጠገቤ የለችም እኔ እረሀቡ ሊፈጀኝ ነዉ
<<ኡሚዬ ዘሙ አሁን አትመጣም
<እቆያለሁ ብላኛለች ወይም ካልሆነ ለምን አትደዉይላትም
<<ኡሚዬ ደዉዬ ካስጨነኳት ደሞ ሀጃዋን ጥላ ትመጣለች እናም በድጋሚ ጥላኝ መሄዷ ነዉ
<የእናንተ ፍቅር ደሞ ማሻአላህ ነበር አሁን ግን በዛ እዲያ ቆይ ምንድ ነዉ አንቺ እሷ ከሌለች አልበላም እሷ ደሞ ፎዙ ከሌለች አልበላም ቆይ ቢያምሽስ
<<ልታመማ ዘሙን ምግብ ጥያት ከምበላ ብታመም እመርጣለዉ

"ይገርማል የሚገርሙ ቤተሰብ ናቸዉ ዉይ በአላህ ቆይ ሙስሊሞች ሆነዉ እንኳን የአላህን ሰላምታ ለመመለስ እንዴት ይከብዳቸዋል ያአሏህ ዛሬ ምን ሲያቀብጠኝ ነዉ እህቴን ሳልጠብቅ የወጣሁት ደሞ
<ዘሙ ስልክሽን እንኪ My life የሚል ስልክ ተደዉሎብሻል
<<እሺ ፈዱዬ ስጪኝና አንዴ እኔ አዉርቼ ልመለስ
<እሺ ግን ወንድ ነዉዴ ብላኝ በሹክሹክታ ፈዱ ጠየቀችኝ አንቺ ቀዉስ እረ እህቴ ናት ብዬ ፎዙን ስልክ ለማዉራት ወደ ዉጪ ወጣሁ ሄለዉ አሰላም አለይኩም እህቴ አፉ በይኝ ጓደኛዬ ቤተሰቦቿን ለማስተዋወቅ ይዛኝ ሄዳ ነዉ ግን ጨንቆኛል ታዉቂያለሽ ከቤተሰቦቼ ተነጥዬ ይህዉ አልናገር አልጋገርኮ ተቸገርኩ
<ወአሌይኩም ወሰላም እረ ልጄ እኔ እናትሽ ነኝ ምክንያትሽኮ በዝቶ ካርድ ከሚዘጋ ብዬ ነዉ
<<ኡሚዬ ፎዙ መስላኝኮ ነዉ እስቲ ድምጿን ልስማዉ አገናኚኝ
<እንዴ ምነዉ ዛሬ አላወራቹሁምንዴ
<<አይ እሱማ እሷ ሁለት ጊዜ ደዉላ እኔ አንዴ ደዉዬላት ነበር ግን ደሞ አሁን በጣም ነዉ የናፈቀችኝ
<እዲያ የእናንተስ በዛ እሷ ዘሙ ካልመጣች አልበላም ብላ ተኝታለች አሁን አንቺ ተቆጪልኝና እስቲ እንድትበላ አድርጊ
<<ኡሚዬ አሁን ለሷ ስጪልኝ ጭራሽ ከላበዛችዉምንዴ ቆይ ቢያማትስ
<እሺ መቼ ነዉ የምትመጪዉ ደሞ እንደማልበላ ታዉቂ የለ
<<ፎዙ ቆይ እየቀለድሽ ነዉ ከመቼዉ ከኡሚ ጆሮ ነጠቅሻት ደሞ
<እህቴ ናፍቀሽኛል ነይ በቃ እኔ አልቻልኩም
<<እሺ እመጣለሁ ግን ሰዎቹ ይከብዳሉ
<ምነዉ እህቴ ችግር አለንዴ
<<አይ የለም ግን በቃ ስመጣ አወራሻለሁ
<እሺ ዘሙዬ ደሞ ምግብ በደንብ ቢ በቃ እናም ተጫዉተሽ ቀስ ብለሽ ነይ
<<እሺ እህቴ ብዬ ስልኩን ተሰናብቼአት ዘጋሁትና ወደነ ፈዱ ቤት ተመለስኩ ይገርማል ሁሉም እንደ ብርቅዬ ሰዉ አጅበዉኝ ይመለከቱኛል እኔ እያንዳንዳቸዉን ለማየት ቀና ስል አይን ለአይን እየተገጣጠምን እኔ አቀረበርኩ የፈዱ እናት ታወራኝ ጀመር
<እኔ ምልሽ ልጄ ከመጣሽ ጀምሮ እኛ ሰንጫወት ስናወራ አንቺ ግን ዝም ብለሽ እንደተቀመጥሽ ነዉ ተጫወቺ አትፍሪ
<<እሺ እማማ እጫወታለሁ
<የምን እማማ ነዉ እናቴ በይኝ እንጂ
<<እሺ ኡሚ
<እኔ ምለዉ ተማሪ ነሽ
<<ነበርኩ
<ነበርኩ ማለት
<<አይ ኒቃብ ስለብስ ከትምርት ቤት ተባርሬ ነዉ
<ጥሩ ነዉ ለዲንሽ ይህን ዋጋ በመክፈልሽ እና በወጣትነትሽ ጥሩ ስርአት ያላት ልጅ በመሆንሽ እድለኛ እንደሆንሽ ሊሰማሽ ይገባል
<<ጀዛከላህ ኡሚ
<እና ፈዱ እንዴት ናት ጓደኝነት ላይ
<<ጥሩና ደስ የምትል ትልቅ እዉቀት የምትፈልግ ምርጥ ሴት ናት

"""አባቴ እረ በቃ እንመለስ አሁን ምን እናረጋለን ብሎ አባቱን እየለመነ ነዉ አባቱን: ኻሊድ ተወኝ እሱ ምን ቢደፍረኝ ነዉ በኔ ላይ ፈርቅ ሚይዝብኝ እኔ የአንተ አባት ማንም ሸዉዶኝኮ አያዉቅም ብሎ ብሎ እኔ ሙስጠፋን ለመሸወድ ይሞክራልንዴ እኔኮ ማን እንደሆንኩ አላወቀም እያሉ ........
"የፈዲላ አባት እየተናደዱ ነዉ የፈዲላ ወንድም "ኻሊድ" ደሞ እየለመናቸዉ ነዉ እሳቸዉ እንደዚ እያሉ ያስቡት እራሳቸዉን ስተዉ ወደቁ...
በዚ መሀል መተንፈስም እያቃታቸዉ ስለነበር ኻሊድ በድንጋጤ ጮሆ ወደ ኦስፒታል ይዘዋቸዉ መጟዝ ጀመሩ.....

┏•━•━•━ ❷ ━•━•━•┓
#ክፍል_ሁለት[❷]
┗•━•━•━ ❷ ━•━•━•┛

ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!

جمعية المشاريع الخيرية الإسلامية
https://t.me/joinchat/R_QhFIbufEC65ol6