2022-09-28 07:16:54
#ሼር_ፖስት ማዲንጎ አፈወርቅ የባለሀብቶች ቁማር ሰለባ ሆኖ ይሆን? ኢትዮጵያ ውስጥ በ700,000 ብር 'በዚህ አንድ ወር ታዋቂ ሰው ይሞታል አይሞትም' የሚል ውርርድ አለ አሉ? አሌክስ አብርሀም ከ13 ቀን በፊት የጻፈው መረጃ ብዙ ጥያቄ ፈጥሮብኛል። አሌክስ ከመሬት ተነስቶ እንደዚህ ያለ ነገር እንደማይጽፍ አውቃለሁ፤ የሆነ የሰማው ወይንም የሚያውቀው መረጃ አለ። ጽሁፉ እንዲህ ይላል፣
"ገፊ ሁሉ!....በአገራችን ቁማር አደገኛ ደረጃ ላይ ደርሷል ጓዶች! ይሄው ብራቸውን መጣያ ያጡ የአዲስ አበባ ሀብታሞች በየምሽቱ ሚሊየኖች እያስያዙ የሚቆምሩባቸው ቤቶች መኖራቸውን ሰማሁ ! ደግሞኮ ቁማሩ ...ካርታ ምናምን እንዳይመስላችሁ! ለምሳሌ የዛሬ ወር አካባቢ 'በዚህ አንድ ወር ታዋቂ ሰው ይሞታል አይሞትም' በሚል በሰባት መቶ ሽ ብር መወራረዳቸውን ሰማሁ ! ገፊ ሁሉ.... እኛ እዚህ በነብስ ይማር ስንጠመድ በአንዱ ታዋቂ ነፍስ ህልፈት የሚጨፍር ሀብታም ተፈጠረ? የሰው አገር ሀብታም ሆስፒታል ገንብቶ ከሞት ይታደጋል የኛዎቹ..... ነገሩን ገፋ አድርገን ካየነውኮ እነዚህ ሰዎች ይሄን ያህል ብር ለመብላት አንዱን ሚስኪን አርቲስት ደመከልብ የሚያደርግ ገዳይ ከኋላ እንደማይልኩስ ምን ማረጋገጫ አለ?"
አዲስአበባ የሚኖሩ ሀብታሞች ከአርቲስቶች ውስጥ እከሌ በዚህ ወር ይሞታል አይሞትም እያሉ ገንዘብ እያሲያዙ ቁማር እንደሚጫወቱ ነው አሌክስ የነገረን። ማዲንጎስ የዚህ ቁማር ሰለባ ስላለመሆኑ ምን ማረጋገጫ አለ?
ልክ እንደ ማዲንጎ ብዙ አርቲስቶች በድንገት ህይወታቸው አልፏል። ለምሳሌ፣ ኢዮብ መኮንን ድንገት ልቤን አለ ወዲያው ሞተ። ተወዳጁ ታምራት ደስታ ልክ እንደ ማዲንጎ መኪናውን እያሽከረከረ ክሊኒክ ሄደ እዚያው ሞተ። ባለፈው ዓመት የሞተው የሰው ለሰው ድራማ አዘጋጅ የነበረው አርቲስት መስፍን ጌታቸው ኮረና መጣ ተባለ አጣድፈው ካምፕ አስገቡት በዛው ሞተ። እነ ታምራት ሞላ፣ ኃብተ ሚካኤል ደምሴ፣ ማናለሞሽ ዲቦ፣ አለባቸው ተካ፣ ሱራፌል ደምሴ፣ ወዘተ አብዛኞቹ በድንገተኛ መንገድ ነው ህይወታቸው ያለፈው።
"ቬሮኒካ" በሚል ዝነኛ የብዕር ስሙ የምናውቀው
ጋዜጠኛ ደምስ መኮንን ከ30 ዓመት በኋላ ለውጥ መጣ ብሎ ኢትዮጵያ ገባ። ታላቅ ወንድሜ ዘመድኩ በቀለ እንዳለው፣ "በብዕር ስሙ ሲያቆስላቸው የኖሩት አሰፍስፈው ጠበቁት። ከሆነ ሰው ጋር ሻይ ጠጥቶ ወደ ቤቱ ገባ። ደም ሲተፋ አመሸ። ሆስፒታል ገባ። አጣድፈው አፀዱት። ሳይመረመር አካልበው ቀበሩት። የዐማራ ድምጽ ሬድዮም ተዘጋ። የቬሮኒካም ብዕር አብሮ ተቀበረ።"
ኢንጂነር ስመኘው በቀለንም መኪና ውስጥ እንዳለ ነው የገደሉት። ደራሲ ይስማዕከ ወርቁ በተደጋጋሚ በመኪና ገጭተው ለመግደል ሞክረዋል። ትናንት ዳኜ ዋለ ከማዲንጎ አፈወርቅ ቤት ለቅሶ ቆይቶ ከምሽቱ 3:00 ወደቤቱ እየሄደ ከፊት እና ከኋላ በፓትሮል መኪና መንገድ ዘግተው በሰደፍ ደብድበውታል። ሁለት ስልኩን ሌሎች ፋይሎቹን ጭምር በመዝረፍ ሳሪስ አካባቢ እሱን ከነመኪናው ጥለውት ሄደዋል።
የዐማራን ኤሊት ቀስ በቀስ እያፀዱት ነው። ኤሊት ፖለቲከኛ ብቻ አይደለም፣ ዘፋኙንም፣ ዶክተሩንም፣ ኢንጂነሩንም፣ ቄሱም፣ ሼኩም፣ አትሌቱም፣ ወዘተ ኤሊት ነው። አሌክስ አብረሃም ያለው እውነት ከሆነ ራሴን፣ ሆዴን...እያሉ የሚሞቱ ወይንም በመኪና ተገጭተው የሚገደሉ በዝርዝራቸው ውስጥ አይኖርም ማለት አይቻልም!
15.9K viewsTadele Tibebu, edited 04:16