2022-08-22 16:00:28
Anti madhabs part two
ጥያቄ ①① ስለ ሰላተተስቢህ አንድ በሉን ?
ኢብኑ ባዝ ⇢ ሰላተተስቢህ መስገድ አይፈቀድም
ለምን በዛ የመጡት ሁላ ሀዲሶች
የተፈበረኩ(መውዱዕ) ናቸው
ኢብኑ ኡሰይሚን ⇥ መስገድ ክልክል ነው
ምክንያቱም ሀዲሶቹ ሰሂህ
አይደሉም
አልባኒ ↣ ስለ ሰላተተስቢህ የመጡት ሀዲሶች
በሁሉም ጠሪቆች ሰሂህ ናቸው
ጥያቄ ①② አንድ ሰው ሙሳፊር ለመባል ምን
ምን ያክል ርቀት ነው መሄድ ያለበት?
ኢብኑ ባዝ ⇢አብዛኛው ኡለማ የተስማሙበት
80 km ነው
ኡሰይሚን ⇥ ትክክለኛው ራዕይ በርቀት
እንደማይገደብ ነው ጉዞ ተብሎ
በተለምዶ ሚጠራ ሁሉ ሙሳፊር
ነው
አልባኒ ↣ በተለምዶ ጉዞ ሚባል ሁላ የተጓዘ
ሙሳፊር ነው
ጥያቄ ①③ የጀምዐ ሰላት ለመቋቋም ስንተ ሰው
ሰው ነው ሚያስፈልገው ?
ኢብኑ ባዝ ⇢ ቢያንስ 3 ሰውና ከዛ በላይ መኖር
አለበት
ኡሰይሚን ⇥ በ3ና ከዛ በላይ ይቻላል
አልባኒ ↣ ለጀመዐ ሰላት የሚያስፈልገው ቁጥር
ያክል ለጁምዐም እንደዛ መሆን አለበት
ጥያቄ ①④ በጁምዐ ቀን የረሱል ﷺ ስም ሲነሳ
ምን እናርግ?
ኢብኑ ባዝ ⇢ሳይጮኽ ሰላዋት ማረግ ይፈቀዳል
ኡሰይሚን ⇥ ሀራም የለውም ሳይጮኽ ከተረገ
አልባኒ ↣ ሰለዋት ማረግ ለግው የተባለው ውስጥ
ይገባል ( ለዛ ሰለዋት ማረግ አይቻልም)
ጥያቄ ①⑤ ሰላተል ኹሱፍ መስገድ ሁክሙ
ምንድን ነው ?
ኢብኑ ባዝ ⇢ ሱና ሙዐከዳ ነው
ኡሰይሚን ⇥ ፈርዱ ኪፉያ (ከፊሉ ማህበረሰብ
ከሰራው በሌላው ላይ የሚወድቅ)
አልባኒ ↣ ግዴታ ነው (በሁሉም)
ፆም
ጥያቄ ①⑥ ለሞተ ሰው መፆም እንዴት ይታያል ?
ኢብኑ ባዝ ⇢ከፉራ፣ ነዝርና የረመዳን ያለበት
መፆም ይቻላል
ኡሰይሚን ⇥ የነዝርና የረመዳን ነው ሚቻለው
አልባኒ ↣ የነዝር ብቻ ነው ሚቻለው ሌላ
ሌሎቹን መፆም አይበቃም
ጥያቄ ①⑦ አንድ ሰው ስራዬ ብሎ የረመዳን ወር
ካሳለፈ ምን ማረግ አለበት?
ኢብኑ ባዝ ⇢ያለ ኡዙር ያሳለፈ ተውበት አርጎ
ቀዳ ማውጣት አለበት
ኡሰይሚን ⇥ ቀዳ ማውጣት አይወጅብበትም
አልባኒ ↣ ስራዬ ብሎ የፈታ ቀዳ ማውጣት
የለበትም ቀዳ ያለበት በግብረ ስጋ
ፆሙን የፈታ ብቻ ነው ግዴታ ሚሆንበት
ጂሀድ
ጥያቄ ①⑧ ካፊሮችን ለመዋጋት ሌላ ካፊርን
እገዛ መጠየቅ ይቻላል ወይ?
ኢብኑ ባዝ ⇢ ይቻላል
ኡሰይሚን ⇥ ይፈቀዳል
አልባኒ ↣ ክልክል ነው አይፈቀድም
ማል
ጥያቄ ①⑨ ቁርዐን የሚያስቀራ ሰው ገንዘብ
መቀበል ይፈቀድለታል?
ኢብኑ ባዝ ⇢ምንም ችግር የለውም
ኡሰይሚን ⇥ ይፈቀዳል
አልባኒ ↣ አይፈቀድም
ኒካህ
ጥያቄ ⑳ አንዲት ሴትን ጠሀራ ሳትሆን መፍታት
ይቻላል?
ኢብኑ ባዝ ⇢ እንደአብዛኛው እይታና ትክክለኛው
ቀውል አይቻልም
ኡሰይሚን ⇥ አይቻልም
አልባኒ ↣ ይቻላል
ማጠቃለያ
እሺ የየትኛውን ፈትዋ እንውሰድ? ይህኛው ትክክል ያኛው ስህተት ነው የምንልበት ሙስተዋ ላይ ደርሰናል? ወይስ የአንዳቸውን እውቀት በመተማመን የሱን እንከተል? እንደዛ ካረግን 5ተኛ መዝሀብ አይሆንም? ታዲያ ከ 4ቱ አኢማዎች አንዱን ከመከተል ጋር ምን አለያየው(እቺ ተቅሊድ ሀራም ለሚሉት ነው እንጂ እነዛ ጋር አይወዳደሩም) ?
.......መልሱን ለናንተ.........
Reference
who is Right
According to the quran and sunnah
Ibn baaz, Ibn utaymeen or albani ?
Translated the portion of a book called al- Eejaaz fi badi ......by Dr. Saed bin abdullah al- bareek by Dr. S. Kose 2016
https://t.me/sufiyahlesuna
1.5K viewsedited 13:00