Get Mystery Box with random crypto!

ኡለሞችን መከተል ግዴታ ነው ማንኛውም ሙስሊም የኢጅቲሃድ ደረጃ እስካልደረሰ | ሱፊይ አሕለሱና ወልጀመዐህ

ኡለሞችን መከተል ግዴታ ነው


ማንኛውም ሙስሊም የኢጅቲሃድ ደረጃ እስካልደረሰ ኡለሞችን የመከተልና የመጠየቅ ግዴታ አለበት ፣ ኡለሞችን ፈትዋ ሲጠይቅ በቅድሚያ በኢልማቸውና በተቅዋቸው እስከተማመነ ድረስ እነርሱ ፈትዋቸውን የገነቡበትን " ማስረጃ " የመጥቀስ ግዴታ የለባቸውም ምክንያቱም አንድ ሸሪአን በጥልቀት ያልተማረ ሰው ማስረጃ ሰጠነውም አልሰጠነውም ምንም ለውጥ የለውም ። እርሱ ዘንድ የግንዛቤ መርጃ እውቀቶች ስለሌሉ ማስረጃ ምንም አያደርግለትም ፣ ሰሂህ ሀዲስን ከደካማው ለይቶ የማያውቅ ሰው በሀዲስ እንዲህ ተብሏል ተብሎ ማስረጃ ቢቀርብለት ምን ይጠቅመዋል ምናልባት ማስረጃ አቅራቢው ሰሂህነቱን ደዒፍነቱን ሊያብራራለት ይገባል ልንል እንችላለን ነገር ግን ጥያቄያችን ይህ ማስረጃ አቅራቢ ደካማውን ሃዲስ ሰሂህ ነው ብሎ ቢያቀርብለትስ ይህ ሸሪአ ያልተማረ ሰው መለየት ይችላልን የሚል ነው ስለዚህ ለዚህ ሰው ማስረጃ ማቅረብ ፋይዳ የለውም።

አሏህም ሱብሃነሁ ወተአላ ተራው ህዝብ ላይ ኡለሞችን ፈትዋ መጠየቅን ነው ግዴታ ያደረገው
وَمَآ أَرْسَلْنَا قَبْلَكَ إِلَّا رِجَالًۭا نُّوحِىٓ إِلَيْهِمْ ۖ فَسْـَٔلُوٓا۟ أَهْلَ ٱلذِّكْرِ إِن كُنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ
ከአንተም በፊት ወደእነሱ የምናወርድላቸው የኾነን ሰዎችን እንጂ ሌላን አላክንም፡፡ የማታውቁም ብትኾኑ የመጽሐፉን ባለቤቶች ጠይቁ፡፡

አልአንቢያእ

https://t.me/sufiyahlesuna