Anti madhabs part two ጥያቄ ①① ስለ ሰላተተስቢህ አንድ በሉን ? ኢብኑ ባዝ ⇢ ሰላተተስቢህ መስገድ አይፈቀድም ለምን በዛ የመጡት ሁላ ሀዲሶች የተፈበረኩ(መውዱዕ) ናቸው ኢብኑ ኡሰይሚን ⇥ መስገድ ክልክል ነው ምክንያቱም ሀዲሶቹ ሰሂህ አይደሉም አልባኒ ↣ ስለ ሰላተተስቢህ የመጡት ሀዲሶች በሁሉም ጠሪቆች ሰሂህ ናቸው ጥያቄ ①② አንድ ሰው ሙሳፊር ለመባል ምን ምን ያክል ርቀት ነው መሄድ ያለበት? ኢብኑ ባዝ ⇢አብዛኛው ኡለማ የተስማሙበት 80 km ነው ኡሰይሚን ⇥ ትክክለኛው ራዕይ በርቀት እንደማይገደብ ነው ጉዞ ተብሎ በተለምዶ ሚጠራ ሁሉ ሙሳፊር ነው አልባኒ ↣ በተለምዶ ጉዞ ሚባል ሁላ የተጓዘ ሙሳፊር ነው ጥያቄ ①③ የጀምዐ ሰላት ለመቋቋም ስንተ ሰው ሰው ነው ሚያስፈልገው ? ኢብኑ ባዝ ⇢ ቢያንስ 3 ሰውና ከዛ በላይ መኖር አለበት ኡሰይሚን ⇥ በ3ና ከዛ በላይ ይቻላል አልባኒ ↣ ለጀመዐ ሰላት የሚያስፈልገው ቁጥር ያክል ለጁምዐም እንደዛ መሆን አለበት ጥያቄ ①④ በጁምዐ ቀን የረሱል ﷺ ስም ሲነሳ ምን እናርግ? ኢብኑ ባዝ ⇢ሳይጮኽ ሰላዋት ማረግ ይፈቀዳል ኡሰይሚን ⇥ ሀራም የለውም ሳይጮኽ ከተረገ አልባኒ ↣ ሰለዋት ማረግ ለግው የተባለው ውስጥ ይገባል ( ለዛ ሰለዋት ማረግ አይቻልም) ጥያቄ ①⑤ ሰላተል ኹሱፍ መስገድ ሁክሙ ምንድን ነው ? ኢብኑ ባዝ ⇢ ሱና ሙዐከዳ ነው ኡሰይሚን ⇥ ፈርዱ ኪፉያ (ከፊሉ ማህበረሰብ ከሰራው በሌላው ላይ የሚወድቅ) አልባኒ ↣ ግዴታ ነው (በሁሉም) ፆም ጥያቄ ①⑥ ለሞተ ሰው መፆም እንዴት ይታያል ? ኢብኑ ባዝ ⇢ከፉራ፣ ነዝርና የረመዳን ያለበት መፆም ይቻላል ኡሰይሚን ⇥ የነዝርና የረመዳን ነው ሚቻለው አልባኒ ↣ የነዝር ብቻ ነው ሚቻለው ሌላ ሌሎቹን መፆም አይበቃም ጥያቄ ①⑦ አንድ ሰው ስራዬ ብሎ የረመዳን ወር ካሳለፈ ምን ማረግ አለበት? ኢብኑ ባዝ ⇢ያለ ኡዙር ያሳለፈ ተውበት አርጎ ቀዳ ማውጣት አለበት ኡሰይሚን ⇥ ቀዳ ማውጣት አይወጅብበትም አልባኒ ↣ ስራዬ ብሎ የፈታ ቀዳ ማውጣት የለበትም ቀዳ ያለበት በግብረ ስጋ ፆሙን የፈታ ብቻ ነው ግዴታ ሚሆንበት ጂሀድ ጥያቄ ①⑧ ካፊሮችን ለመዋጋት ሌላ ካፊርን እገዛ መጠየቅ ይቻላል ወይ? ኢብኑ ባዝ ⇢ ይቻላል ኡሰይሚን ⇥ ይፈቀዳል አልባኒ ↣ ክልክል ነው አይፈቀድም ማል ጥያቄ ①⑨ ቁርዐን የሚያስቀራ ሰው ገንዘብ መቀበል ይፈቀድለታል? ኢብኑ ባዝ ⇢ምንም ችግር የለውም ኡሰይሚን ⇥ ይፈቀዳል አልባኒ ↣ አይፈቀድም ኒካህ ጥያቄ ⑳ አንዲት ሴትን ጠሀራ ሳትሆን መፍታት ይቻላል? ኢብኑ ባዝ ⇢ እንደአብዛኛው እይታና ትክክለኛው ቀውል አይቻልም ኡሰይሚን ⇥ አይቻልም አልባኒ ↣ ይቻላል ማጠቃለያ እሺ የየትኛውን ፈትዋ እንውሰድ? ይህኛው ትክክል ያኛው ስህተት ነው የምንልበት ሙስተዋ ላይ ደርሰናል? ወይስ የአንዳቸውን እውቀት በመተማመን የሱን እንከተል? እንደዛ ካረግን 5ተኛ መዝሀብ አይሆንም? ታዲያ ከ 4ቱ አኢማዎች አንዱን ከመከተል ጋር ምን አለያየው(እቺ ተቅሊድ ሀራም ለሚሉት ነው እንጂ እነዛ ጋር አይወዳደሩም) ? .......መልሱን ለናንተ......... Reference who is Right According to the quran and sunnah Ibn baaz, Ibn utaymeen or albani ? Translated the portion of a book called al- Eejaaz fi badi ......by Dr. Saed bin abdullah al- bareek by Dr. S. Kose 2016 https://t.me/sufiyahlesuna 1.5K viewsedited 13:00